-
“ሙታን የሚነሱት እንዴት ነው?”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ታኅሣሥ
-
-
3. በ1 ቆሮንቶስ 15:30-32 ላይ እንደተገለጸው ጳውሎስ በትንሣኤ ላይ ያለው እምነት ምን እንዲያደርግ ረድቶታል?
3 ጳውሎስ በትንሣኤ ተስፋ ላይ ያለው እምነት የተለያዩ መከራዎችን በጽናት ለመወጣት ረድቶታል። (1 ቆሮንቶስ 15:30-32ን አንብብ።) ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች “እኔ በየቀኑ ሞትን እጋፈጣለሁ” ብሏቸዋል። ጳውሎስ “በኤፌሶን ከአውሬዎች ጋር [ታገልኩ]” በማለትም ጽፏል። ይህን ሲል ምናልባት በኤፌሶን በሚገኝ ስታዲየም ውስጥ ቃል በቃል ከእንስሳት ጋር እንደታገለ መግለጹ ሊሆን ይችላል። (2 ቆሮ. 1:8፤ 4:10፤ 11:23) ወይም ደግሞ እንደ “አውሬ” ጨካኝ የሆኑ አይሁዳውያን ወይም ሌሎች ሰዎች ያደረሱበትን ተቃውሞ እየገለጸ ሊሆን ይችላል። (ሥራ 19:26-34፤ 1 ቆሮ. 16:9) ሁኔታው ምንም ይሁን ምን፣ ጳውሎስ ከባድ መከራዎችን ተጋፍጧል፤ ይሁን እንጂ ስለ ወደፊቱ ጊዜ አዎንታዊ አመለካከት ይዞ ቀጥሏል።—2 ቆሮ. 4:16-18
-
-
“ሙታን የሚነሱት እንዴት ነው?”መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020 | ታኅሣሥ
-
-
5. በትንሣኤ ተስፋ ላይ ያለንን እምነት የሚያዳክመው የትኛው አደገኛ አመለካከት ነው?
5 ጳውሎስ በዘመኑ የሚኖሩ አንዳንድ ሰዎች የነበራቸውን “ነገ ስለምንሞት እንብላ፣ እንጠጣ” የሚል አደገኛ አመለካከት አስመልክቶ ወንድሞቹን አስጠንቅቋቸዋል። ይህ አመለካከት ከጳውሎስ ዘመን በፊትም ነበር። ምናልባትም ጳውሎስ እስራኤላውያን የነበራቸውን ዝንባሌ የሚገልጸውን ኢሳይያስ 22:13ን እየጠቀሰ ሊሆን ይችላል። እስራኤላውያን ወደ አምላክ ከመቅረብ ይልቅ ተድላን በማሳደድ ላይ ያተኮረ ሕይወት ይመሩ ነበር። በሌላ አባባል እነዚህ እስራኤላውያን “ሺህ ዓመት አይኖር” ያሉ ያህል ነው፤ እንዲህ ያለው አመለካከት ዛሬም በስፋት ይታያል። ሆኖም ይህ አመለካከት በእስራኤላውያን ላይ ያስከተለውን መዘዝ ከታሪካቸው መመልከት ይቻላል።—2 ዜና 36:15-20
6. የትንሣኤ ተስፋ በጓደኛ ምርጫችን ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይገባል?
6 ይሖዋ ሙታንን እንደሚያስነሳ ማወቃችን በጓደኛ ምርጫችን ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚገባ ጥርጥር የለውም። በቆሮንቶስ ይኖሩ የነበሩ ወንድሞች ትንሣኤን ከሚክዱ ሰዎች ጋር ወዳጅነት ላለመመሥረት መጠንቀቅ ነበረባቸው። ከዚህ ግሩም ትምህርት እናገኛለን፤ ለዛሬ ብቻ የሚኖሩ ሰዎችን ጓደኛ አድርገን መምረጣችን ጎጂ ነው። አንድ እውነተኛ ክርስቲያን እንዲህ ካሉ ሰዎች ጋር ብዙ ጊዜ ማሳለፉ በአመለካከቱና በሥነ ምግባሩ ላይ መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድርበት ይችላል፤ ይባስ ብሎም አምላክ የሚጠላውን ዓይነት ሕይወት እንዲከተል ማለትም በኃጢአት ጎዳና እንዲመላለስ ሊያደርገው ይችላል። በመሆኑም ጳውሎስ “ጽድቅ የሆነውን በማድረግ ወደ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአት መሥራትን ልማድ አታድርጉ” የሚል ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።—1 ቆሮ. 15:33, 34
-