የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከሮማ ታሪክ የሚገኝ ትምህርት
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • ከሮማ ታሪክ የሚገኝ ትምህርት

      “እንደ ሰው በኤፌሶን ከአውሬ ጋር [ታገልሁ።]” አንዳንዶች በ1 ቆሮንቶስ 15:​32 ላይ የሚገኙት እነዚህ የሐዋርያው ጳውሎስ ቃላት ጳውሎስ በሮማ የትግል ሜዳ ውስጥ እንዲታገል ተፈርዶበት እንደነበር ያሳያሉ በማለት ይናገራሉ። ጳውሎስ ቃል በቃል ይህ ፍርድ ተበይኖበት ይሁን አይሁን ምንም የሚታወቅ ነገር ባይኖርም በወቅቱ እንዲህ በመሰሉ የመወዳደሪያ ሥፍራዎች ውስጥ እስከሞት ድረስ መፋለም የተለመደ ነበር። ስለ መወዳደሪያ ሥፍራውና በዚያ ይከናወኑ ስለነበሩት ነገሮች ታሪክ ምን ይነግረናል?

  • ከሮማ ታሪክ የሚገኝ ትምህርት
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • ‘ግላዲያተሮቹ እነማን ነበሩ?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። ግላዲያተሮቹ ባሮች፣ የሞት ፍርድ የተበየነባቸው ወንጀለኞች፣ የጦር እስረኞች ወይም በፍላጎት አሊያም ዝና እና ሃብት እናገኛለን በሚል የመጡ ነጻ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም እስር ቤት በመሰሉ ማሠልጠኛዎች ውስጥ ይሰለጥናሉ። ጆኪ ኤ ስፔታኮሊ (ጨዋታዎችና ትርኢቶች) የተባለው መጽሐፍ እንደዘገበው በሥልጠና ላይ ያሉት ግላዲያተሮች “ሁልጊዜ በጠባቂዎቹ እይታ ሥር ናቸው። ጥብቅ ለሆነ ዲሲፕሊንና መመሪያ መገዛት የነበረባቸው ሲሆን ስህተት ከሠሩ ከባድ ቅጣት ይደርስባቸው ነበር። . . . እንዲህ ያለው ሁኔታ ብዙውን ጊዜ ራሳቸውን እንዲገድሉና ረብሻና ዓመፅ እንዲያነሳሱ ያደርጋቸው ነበር።” በሮም የሚገኘው ትልቁ የግላዲያተር ማሰልጠኛ ቢያንስ ለአንድ ሺህ ሰልጣኞች የሚሆኑ ክፍሎች ነበሩት። እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ችሎታ ነበረው። አንዳንዶች ከብረት የተሠራ መከላከያ አጥልቀውና ጋሻና ጎራዴ ታጥቀው ሲፋለሙ ሌሎቹ መረብና ሦስት አንጓ ያለው መንሽ የመሰለ ጦር ይዘው ይፋለማሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ በሆነው የአደን ትርዒት ከዱር አውሬዎች ጋር ለመፋለም የሚያስችላቸውን ሥልጠና ይወስዳሉ። ጳውሎስ የተናገረው ይህንን ውድድር አስመልክቶ ይሆን?

  • ከሮማ ታሪክ የሚገኝ ትምህርት
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • በፍልሚያ ሜዳው ውስጥ የጠዋቱ ክፍለ ጊዜ ለአደን የተመደበ ነው። የተለያየ ዓይነት ዝርያ ያላቸው የዱር እንስሳት ወደ ፍልሚያ ሜዳው እንዲገቡ ይደረጋል። አብዛኛው ተመልካች በተለይ በጎሽና በድብ መካከል የሚደረገውን ፍልሚያ መመልከት ያስደስተዋል። ብዙውን ጊዜ ሁለቱም አንድ ላይ ይታሠሩና አንደኛው ወገን እስኪሞት ድረስ እንዲፋለሙ ይደረጋል። በመጨረሻም በሕይወት የተረፈው በአዳኝ ይገደላል። ከሌሎች ታዋቂ ግጥሚያዎች መካከል በአንበሳና በነብር ወይም በዝሆንና በድብ መካከል የሚደረጉት ይገኙበታል። አዳኞች ከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸውም ቢሆን ከሁሉም የአገሪቱ ግዛቶች የመጡትን እንደ ነብር፣ አውራሪስ፣ ጉማሬ፣ ቀጭኔ፣ ጅብ፣ ግመል፣ ተኩላ፣ ከርከሮና ድኩላ የመሳሰሉ ብርቅዬ እንስሳት በመግደል የአዳኝነት ችሎታቸውን ያሳያሉ።

      አካባቢውን ከጫካ ጋር ለማመሳሰል ሲባል በፍልሚያ ሜዳው አለቶች፣ ኩሬዎችና ዛፎች እንዲኖሩ መደረጉ ትርኢቱ በተመልካቾቹ ላይ የማይረሳ ትዝታ ጥሎ እንዲያልፍ አድርጓል። በአንዳንድ የፍልሚያ ሜዳዎች የዱር አራዊቱ መሬት ውስጥ በተሠሩ አሳንሰሮች አማካኝነት ከያሉበት ብቅ ሲሉ በአንድ ምትሃታዊ ኃይል ሜዳው ውስጥ የገቡ ይመስላል። እንስሳቱ የሚያሳዩት እንግዳ የሆነ ባሕርይም ለውድድሩ ድምቀት ሰጥቶታል። ይሁን እንጂ ተመልካቹን ይበልጥ የሚያስደስተው በትርኢቱ ላይ የሚንጸባረቀው ጭካኔ ነበር።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ