የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “ከኤፊቆሮሳውያን” ተጠንቀቁ
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ኅዳር 1
    • ኤፊቆሮስ ከሞት በኋላ ሕይወት ሊኖር አይችልም ብሎም አስተምሯል። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ትንሣኤ ከሚያስተምረው ጋር በእርግጥ የሚጋጭ ነው። እንዲያውም ሐዋርያው ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ ባስተማረበት ወቅት በትንሣኤ መሠረተ ትምህርት ላይ ከእርሱ ጋር ካልተስማሙት መካከል ኤፊቆሮሳውያን ሳይኖሩበት አይቀሩም።​—⁠ሥራ 17:​18, 31, 32፤ 1 ቆሮንቶስ 15:​12-14

      በጣም አደገኛውና የረቀቀው የኤፊቆሮስ ፍልስፍና ይህ ሳይሆን አይቀርም። ኤፊቆሮስ ከሞት በኋላ እንደገና ሕይወት መኖሩን አለመቀበሉ ሰው በምድር ላይ በሕይወት ሳለ በሚያሳልፈው አጭር ጊዜ በተቻለው መጠን መደሰት መቻል አለበት ወደሚል መደምደሚያ መርቶታል። ከላይ እንደተመለከትነው የእርሱ አመለካከት በኃጢአተኝነት ለመኖር ሳይሆን ከዚያ ይልቅ ያለን የአሁኑ ጊዜ ብቻ በመሆኑ ጊዜያችንን በአግባቡ እንድናጣጥም ነው።

      ይህም በመሆኑ እያዛለሁ በሚል ፍራቻ በስውር የሚሰራ ክፉ ድርጊት ላሁኑ ጊዜ ደስታ አደገኛ በመሆኑ ኤፊቆሮስ አውግዞታል። አሁን ሊገኝ ለሚችለው ደስታ እንቅፋት የሚሆነው ሌላው ነገር ከመጠን በላይ መብላትና መጠጣት ስለሆነ ኤፊቆሮስ በዚህም ረገድ ልከኝነትን አበረታቷል። በተጨማሪም ውለታ ሊመልሱልን ስለሚችሉ፣ ለሌሎች ሰዎች መልካም ማድረግ ጥሩ እንደሆነ ይናገራል። እርግጥ ነው በስውር መጥፎ ነገር አለመስራት፣ ልከኛ መሆን እና ለሌሎች መልካም ማድረግ ምንም ክፋት የሌለባቸው ነገሮች ናቸው። ታዲያ የኤፊቆሮስ ፍልስፍና ለአንድ ክርስቲያን አደገኛ የሆነው ለምንድን ነው? ምክንያቱም የእርሱ ምክር የተመሰረተው እምነት የለሽ በሆነ “ነገ እንሞታለንና እንብላና እንጠጣ” በሚል አመለካከት ላይ ስለሆነ ነው።​—⁠1 ቆሮንቶስ 15:​32

      መጽሐፍ ቅዱስ ባሁኑ ጊዜ በደስታ መኖር የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል። ሆኖም “ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሕረት ስትጠባበቁ በእግዚአብሔር ፍቅር ራሳችሁን ጠብቁ” ብሎ ይመክረናል። (ይሁዳ 21) አዎን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጠው ለወደፊቱ ዘላለማዊ ሕይወት እንጂ ብን ብሎ ለሚጠፋው ለአሁኑ ሕይወት አይደለም። የአንድ ክርስቲያን ዋና ፍላጎት አምላክን ማገልገል ነው። አምላክን በአንደኛ ደረጃ ሲያስቀምጥ ደስታና እርካታ ያገኛል። በተመሳሳይም ኢየሱስ በራሱ የግል ፍላጎቶች ከመጠመድ ይልቅ ጉልበቱን ይሖዋን ከራስ ወዳድነት ነፃ በሆነ ሁኔታ ለማገልገልና ሰዎችን ለመርዳት ተጠቅሞበታል። ውለታ ይመለስልኛል ብለው በመጠበቅ ሳይሆን ለሰዎች ካላቸው እውነተኛ ፍቅር በመነሳት ለሌሎች ጥሩ እንዲያደርጉ ደቀ መዛሙርቱን አስተምሯል። በግልጽ እንደሚታየው የኤፊቆሮሳውያን ትምህርትና የክርስትና እምነት መሠረታዊ ግፊቶች ፈጽሞ የተለያዩ ናቸው።​—⁠ማርቆስ 12:​28-​31፤ ሉቃስ 6:​32-36፤ ገላትያ 5:​14፤ ፊልጵስዩስ 2:​2-4

  • “ከኤፊቆሮሳውያን” ተጠንቀቁ
    መጠበቂያ ግንብ—1997 | ኅዳር 1
    • ምንም እንኳ የኤፊቆሮሳውያን ትምህርት በአራተኛው መቶ ዘመን እዘአ ቢጠፋም በአሁኑ ሕይወታችን እንደሰት የሚል ተመሳሳይ አመለካከት የያዙ ሰዎች ዛሬም አሉ። እነዚህ ሰዎች አምላክ ተስፋ በሰጠው የዘላለም ሕይወት ላይ ትንሽ እምነት ይኖራቸው ወይም ምንም እምነት አይኖራቸው ይሆናል። ሆኖም አንዳንዶቹ ከሌሎች አንፃር ሲታዩ ከፍተኛ የሥነ ምግባር አቋም ይኖሯቸው ይሆናል።

      አንድ ክርስቲያን እነዚህ ሰዎች ያላቸውን ጥሩ ሥነ ምግባር እንደ ማሳበቢያ በማድረግ ከእነርሱ ጋር የጠበቀ ቅርርብ ለመመስረት ይፈተን ይሆናል። ራሳችንን ከሌሎች አስበልጠን የምንመለከት ባይሆንም እንኳ በረቀቀ መንገድ ተጽእኖ የሚያሳድሩብንን ሰዎች ጨምሮ “መጥፎ ባልንጀሮች” ሁሉ “መልካሙን አመል” እንደሚያጠፉ ማስታወስ አለብን።

      ሕይወት የአሁኑ ብቻ ነው የሚለው ፍልስፍና በአንዳንድ የንግድ ሴሚናሮች፣ በራስ አገዝ መጻሕፍት፣ በልብ ወለድ መጻሕፍት፣ በፊልሞች፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞችና በሙዚቃዎች በኩል ብቅ ይላል። ምንም እንኳ በቀጥታ የኃጢአተኝነት ባሕርይ ባያስፋፋም ይህ እምነት የለሽ አመለካከት በረቀቀ ሁኔታ ተጽእኖ ሊያሳድርብን ይችል ይሆን? ለምሳሌ ያህል ስለ ይሖዋ ሉዓላዊነት የተነሳው አከራካሪ ጥያቄ ጨርሶ እስኪዘነጋን ድረስ የራሳችንን ጉዳዮች በማሳደድ እንጠመድ ይሆን? ‘ሁልጊዜ የጌታ ሥራ የበዛልን’ ከመሆን ይልቅ በአገልግሎቱ ‘ጥቂት በመሥራት’ ተዘናግተን ይሆን? ወይም የይሖዋን የአቋም ደረጃዎች ትክክለኛነትና ጠቃሚነታቸውን በመጠራጠር አቅጣጫችንን ስተን ይሆን? ከሥነ ምግባር ብልግና፣ ከዓመፅና ከመናፍስትነት እንዲሁም ዓለማዊ አመለካከቶች ተጽእኖ ካሳደሩባቸው ሰዎች ራሳችንን መጠበቅ ያስፈልገናል!​—⁠1 ቆሮንቶስ 15:​58፤ ቆላስይስ 2:​8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ