የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሥራችሁ እሳቱን ይቋቋም ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 1
    • 5. የክርስቲያን ጉባኤ መሠረት ማን ነው? ይህስ በትንቢት የተነገረው እንዴት ነበር?

      5 ጳውሎስ “ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፣ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ሲል ጽፏል። (1 ቆሮንቶስ 3:​11) ኢየሱስ ከመሠረት ጋር ተመሳስሎ ሲጠቀስ ይህ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም። እንዲያውም ኢሳይያስ 28:​16 እንደሚከተለው በማለት ተንብዮአል:- “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል:- እነሆ፣ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፣ የከበረውን፣ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ።” ይሖዋ ከጥንት ጀምሮ ልጁ የክርስቲያን ጉባኤ መሠረት እንዲሆን የማድረግ ዓላማ ነበረው።​—⁠መዝሙር 118:​22፤ ኤፌሶን 2:​19–22፤ 1 ጴጥሮስ 2:​4–6

      6. ጳውሎስ በቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ላይ ትክክለኛውን መሠረት የጣለው እንዴት ነበር?

      6 የግለሰብ ክርስቲያኖች መሠረት ምንድን ነው? ጳውሎስ እንዳለው ለአንድ እውነተኛ ክርስቲያን በአምላክ ቃል ላይ ከተገለጸው ከኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ምንም መሠረት የለም። ጳውሎስ እንዲህ ያለውን መሠረት መጣሉ የተረጋገጠ ነው። ለፍልስፍና ከፍተኛ ግምት የሚሰጡ ሰዎች በነበሩባት በቆሮንቶስ ከተማ ሰዎች ዘንድ ዓለማዊ ጥበብ በማንጸባረቅ ልቆ ለመታየት አልሞከረም። ከዚህ ይልቅ ጳውሎስ አሕዛብ “ሞኝነት” በማለት ያጣጣሉትን “የተሰቀለውን ክርስቶስን” ሰብኳል። (1 ቆሮንቶስ 1:​23) ጳውሎስ በይሖዋ ዓላማ ውስጥ ቁልፍ ሚና የሚጫወተው ኢየሱስ መሆኑን አስተምሯል።​—⁠2 ቆሮንቶስ 1:​20፤ ቆላስይስ 2:​2, 3

  • ሥራችሁ እሳቱን ይቋቋም ይሆን?
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 1
    • 8. ወደፊት ደቀ መዛሙርት ሊሆኑ ለሚችሉ ሰዎች ክርስቶስን መሠረት አድርገን ልናስቀምጥ የምንችለው እንዴት ነው?

      8 ክርስቶስን መሠረት አድርገን ስናስቀምጥ በግርግም እንደሚገኝ አቅመ ቢስ ሕፃን ወይም ከይሖዋ ጋር እንደሚተካከል የሥላሴ ክፍል አድርገን እናስተምራለን ማለት አይደለም። እንዲህ ያለው ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆነ እምነት የሐሰተኛ ክርስቲያኖች መሠረት ነው። ከዚህ ይልቅ በምድር ላይ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ሰው መሆኑን፣ ፍጹም ሕይወቱን ለእኛ ሲል መስጠቱንና በአሁኑ ጊዜ በይሖዋ የተሾመ በሰማይ ሆኖ የሚገዛ ንጉሥ መሆኑን እናስተምራለን። (ሮሜ 5:​8፤ ራእይ 11:​15) በተጨማሪም ተማሪዎቻችን የኢየሱስን ፈለግ እንዲከተሉና ባሕርያቱን እንዲኮርጁ ልናነሳሳቸው እንጥራለን። (1 ጴጥሮስ 2:​21) ኢየሱስ ለአገልግሎቱ በነበረው ቅንዓት፣ ለተናቁና በግፍ ለተደቆሱ ሰዎች ባሳየው ርኅራኄ፣ በጥፋተኝነት ስሜት ቅስማቸው ለተሰበረ ሰዎች ባሳየው ምሕረትና ፈተና ሲደርስበት ባሳየው የማይናወጥ አቋም ተማሪዎቻችን በጥልቅ እንዲነኩ እንፈልጋለን። በእርግጥም ኢየሱስ ዕጹብ ድንቅ መሠረት ነው። ሆኖም የሚቀጥለው ምንድን ነው?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ