የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ከምታያቸው ነገሮች ባሻገር ተመልከት!
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | የካቲት 15
    • እነዚህ ሁሉ ሁኔታዎች ቢኖሩም ታማኞቹ ደቀ መዛሙርት የጸና አቋም ይዘው ነበር። በአምላክ ላይ ጠንካራ እምነት በማሳደር፣ “ተስፋ አንቆርጥም፣ ምንም እንኳ ውጫዊ ሰውነታችን ቢጠፋ፣ ውስጣዊ ሰውነታችን በየቀኑ ይታደሳል” በማለት እንደ ጳውሎስ ለመናገር ችለው ነበር። ሆኖም በየቀኑ እንዲታደሱ ያስቻላቸው ምንድን ነው? ቀጥሎ ጳውሎስ እንዲህ ብሏል፦ “ቀላልና ጊዜያዊ የሆነ መከራችን፣ ወደር የሌለውን እጅግ ታላቅ የሆነ ዘላለማዊ ክብር ያስገኝልናል። እኛ የምንመለከተው የማይታየውን ነው እንጂ የሚታየውን አይደለም፤ ምክንያቱም የሚታየው ነገር ጊዜያዊ ነው፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው።”—2 ቆሮንቶስ 4:16-18 የ1980 ትርጉም

  • ከምታያቸው ነገሮች ባሻገር ተመልከት!
    መጠበቂያ ግንብ—1996 | የካቲት 15
    • በአሁኑ ጊዜ ያሉትን መከራዎች ጊዜያዊ እንደሆኑ አድርገህ ተመልከታቸው!

      በየቀኑ ለማየት የማንፈልጋቸውን ነገሮች መመልከታችን አይቀርም። መስተዋት ስንመለከት የአካላችንን አለፍጽምና የሚጠቁሙ የማንፈልጋቸውን ጉድለቶች በአካላችን ላይ እናያለን። የአምላክን ቃል እንደ መስተዋት አድርገን በመጠቀም አተኩረን ስንመለከት በራሳችንም ሆነ በሌሎች ሰዎች ላይ መንፈሳዊ ጉድለቶችን እንመለከታለን። (ያዕቆብ 1:22-25) በተጨማሪም በየቀኑ በጋዜጣዎች ወይም በቴሌቪዥን ላይ ስለ ፍትሕ መጓደል፣ ጭካኔና አሠቃቂ ድርጊት የሚገልጹ ዘገባዎችን ስንመለከት እናዝናለን።

      ሰይጣን በምናያቸው ነገሮች ምክንያት ተስፋ እንድንቆርጥ ወይም እንድንዘናጋና በእምነታችን መወላወል እንድንጀምር ይፈልጋል። ይህ እንዳይደርስብን መከላከል የምንችለው እንዴት ነው? ሐዋርያው ጴጥሮስ “የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሏል” በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን ምሳሌ እንድንከተል የሰጠውን ምክር መቀበል ይኖርብናል። (1 ጴጥሮስ 2:21) ኢየሱስ በማናቸውም የክርስቲያናዊ ሕይወት ዘርፍ ፍጹም ምሳሌ ይሆነናል።

      ጴጥሮስ፣ ኢየሱስ ምሳሌያችን መሆኑን ሲያመለክት ኢየሱስ መከራ መቀበሉን ለየት አድርጎ ጠቅሷል። በእርግጥም ኢየሱስ በምድር ላይ በነበረበት ወቅት ከባድ መከራ ደርሶበታል። ኢየሱስ የሰው ልጆች ሲፈጠሩ የይሖዋ “ዋና ሠራተኛ” የነበረ እንደ መሆኑ መጠን አምላክ ለሰው ልጆች ምን ዓላማ እንደ ነበረው በትክክል ያውቅ ነበር። (ምሳሌ 8:30, 31) ወደ ምድር በመጣበት ወቅት ግን ኃጢአትና አለፍጽምና በሰው ልጆች ላይ ያስከተሉባቸውን ነገሮች በቀጥታ ተመልክቷል። በየቀኑ የሰዎችን አለፍጽምናና ድክመት ይመለከት ነበር። በተጨማሪም እነዚህ ነገሮች የሚያስከትሉትን አስቸጋሪ ሁኔታዎች መቋቋም ነበረበት። ይህ በጣም ፈታኝ ሆኖበት እንደ ነበር አያጠራጥርም።—ማቴዎስ 9:36፤ ማርቆስ 6:34

      ኢየሱስ ሌሎች ሰዎች ሲሠቃዩ ከማየቱም በላይ በራሱም ላይ መከራ ደርሶበታል። (ዕብራውያን 5:7, 8) ይሁን እንጂ ፍጹም የሆነ መንፈሳዊ የማየት ችሎታ ስለ ነበረው የጸና አቋም በመያዝ የሚያገኘውን የላቀ የማይጠፋ ሕይወት ሽልማት አሻግሮ ተመልክቷል። በዚያን ጊዜ መሲሐዊ ንጉሥ ሆኖ የተጨነቁት የሰው ልጆች ካሉበት ጎስቋላ ሁኔታ የይሖዋ የመጀመሪያ ዓላማ ወደ ነበረው ፍጽምና የመመለስ መብት ይኖረዋል። እነዚህን የማይታዩ የወደፊት ተስፋዎች በዓይነ ሕሊናው አተኩሮ በመመልከቱ የማያቋርጡ መከራዎች ቢያጋጥሙትም ከአምላክ አገልግሎት ደስታ እንዲያገኝ አስችሎታል። ጳውሎስ ከዚህ ቆየት ብሎ “እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል [“በመከራ እንጨት” አዓት] ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጧል” በማለት ጽፏል።—ዕብራውያን 12:2

      ኢየሱስ ችግሮችና ፈታኝ ሁኔታዎች ተስፋ እንዲያስቆርጡት፣ እንዲያዘናጉት ወይም እምነቱን እንዲያናጉበት አልፈቀደም። የእርሱ ደቀ መዛሙርት እንደ መሆናችን መጠን የእርሱን የላቀ ምሳሌ በቅርብ መከተል ይኖርብናል።—ማቴዎስ 16:24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ