-
ይሖዋ የሚሰጠውን ማጽናኛ ማካፈልመጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
-
-
“የመጽናናትም ሁሉ አምላክ”
5. ጳውሎስ ከደረሱበት ብዙ ፈተናዎች ጎን ለጎን ምን አስደሳች ተሞክሮ አጋጥሞታል?
5 አምላክ የሚሰጠውን ማጽናኛ እጅግ ካደነቁት ሰዎች አንዱ ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። በእስያና በመቄዶንያ ለየት ያለ ፈታኝ ሁኔታ ካጋጠመው በኋላ የቆሮንቶስ ጉባኤ ክርስቲያኖች ጽፎላቸው ለነበረው ወቀሳ አዘል ደብዳቤ ጥሩ ምላሽ እንደሰጡ በመስማቱ ትልቅ እፎይታ አግኝቷል። ይህም የሚከተለውን ምስጋና ያዘለ ሁለተኛ ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው ገፋፍቶታል፦ “የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ። እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።”—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4
6. በ2 ቆሮንቶስ 1:3, 4 ላይ ከሚገኙት የጳውሎስ ቃላት ምን እንማራለን?
6 እነዚህ በመንፈስ አነሳሽነት የተነገሩ ቃላት ብዙ ትርጉም ያዘሉ ናቸው። እስቲ እንመርምራቸው። ጳውሎስ በደብዳቤዎቹ ላይ አምላክን ሲያወድስ ወይም ሲያመሰግን ወይም ደግሞ አምላክን ሲለምን ብዙውን ጊዜ የክርስቲያን ጉባኤ ራስ ለሆነው ለኢየሱስ ያለውን የጠለቀ አድናቆት ይገልጻል። (ሮሜ 1:8፤ 7:25፤ ኤፌሶን 1:3፤ ዕብራውያን 13:20, 21) በመሆኑም ጳውሎስ ይህን የውዳሴ ቃል ያሰማው ‘ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት’ ነው። ከዚያም ጳውሎስ እሱ በጻፋቸው ጽሑፎች ውስጥ “ርኅራኄ” ተብሎ የተተረጎመውን የግሪክኛ ስም ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠቅሟል። ይህ ስም የመጣው በሌላ ሰው ላይ በደረሰ መከራ ሳቢያ ማዘንን ከሚገልጽ ቃል ነው። ስለዚህ ጳውሎስ የገለጸው መከራ ለሚደርስባቸው ታማኝ አገልጋዮቹ ሁሉ አምላክ የሚሰማውን የርኅራኄ ስሜት ነው። በምሕረት መንፈስ እነርሱን ለመርዳት እርምጃ እንዲወስድ የሚገፋፋውን የርኅራኄ ስሜት ገልጿል። በመጨረሻም፣ ጳውሎስ “የርኅራኄ አባት” ብሎ በመጥራት ይሖዋን የዚህ ጥሩ ባሕርይ ምንጭ አድርጎ ተመልክቶታል።
7. ይሖዋ “የመጽናናትም ሁሉ አምላክ” ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው?
7 የአምላክ “ርኅራኄ” መከራ የሚደርስበትን ሰው እፎይታ ያስገኝለታል። በዚህም ምክንያት ጳውሎስ በመቀጠል ይሖዋን “የመጽናናትም ሁሉ አምላክ” ብሎ ገልጾታል። ስለዚህ ከመሰል አማኞች ደግነት ምንም ዓይነት ማጽናኛ ብናገኝ የማጽናኛው ምንጭ ይሖዋ እንደሆነ አድርገን ልንመለከት እንችላለን። ምንጩ አምላክ ያልሆነ ማጽናኛ እውነተኛና ዘላቂ ሊሆን አይችልም። በተጨማሪም ሰውን በራሱ መልክ የፈጠረው እሱ ስለሆነ አጽናኞች እንድንሆን የሚያስችለን እሱ ነው። አገልጋዮቹ ማጽናኛ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ርኅራኄ እንዲያሳዩ የሚያነሳሳቸውም የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ነው።
-
-
ይሖዋ የሚሰጠውን ማጽናኛ ማካፈልመጠበቂያ ግንብ—1996 | ኅዳር 1
-
-
8. የፈተናዎቻችን ምንጭ አምላክ ባይሆንም እንኳ በመከራ መጽናታችን ምን ጠቃሚ ውጤት ሊያስገኝልን ይችላል?
8 ምንም እንኳ ይሖዋ አምላክ በታማኝ አገልጋዮቹ ላይ የተለያዩ ፈተናዎች እንዲደርሱ ቢፈቅድም የእነዚህ ፈተናዎች ምንጭ ግን እሱ አይደለም። (ያዕቆብ 1:13) ይሁን እንጂ መከራ ሲደርስብን የሚሰጠን ማጽናኛ የሌሎች ሰዎች ችግር ቶሎ የሚሰማን እንድንሆን ሊያሠለጥነን ይችላል። ይህ ምን ውጤት አለው? “እኛ ራሳችን በእግዚአብሔር በምንጽናናበት መጽናናት በመከራ ሁሉ ያሉትን ማጽናናት እንችላለን።” (2 ቆሮንቶስ 1:4) በመሆኑም የክርስቶስን ምሳሌ በመከተል ‘የሚያለቅሱትን ሰዎች ሁሉ ስናጽናና’ ማጽናኛውን ለመሰል አማኞችና በመስክ ለምናገኛቸው ሰዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ እንድናካፍል ይሖዋ ያሠለጥነናል።—ኢሳይያስ 61:2፤ ማቴዎስ 5:4
-