የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ቲቶ “ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ”
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 15
    • ጳውሎስ በመጀመሪያ ደረጃ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች የጻፈላቸው ‘ከሴሰኞች ጋር እንዳይተባበሩ’ መሆኑን መልእክቱ ያሳያል። ንስሐ ያልገባን ዘማዊ ከመካከላቸው እንዲያስወጡ መንገር የግድ አስፈልጎታል። አዎን፣ ጳውሎስ ከበድ ያለ መልእክት ያዘለ ደብዳቤ ጽፎላቸዋል፤ ይህንም ያደረገው ‘በብዙ እንባ’ ነበር። (1 ቆሮንቶስ 5:​9-13፤ 2 ቆሮንቶስ 2:​4) ይህ በእንዲህ እንዳለ ቲቶ ችግር ለደረሰባቸው የይሁዳ ክርስቲያኖች እየተካሄደ በነበረው እርዳታ የማሰባሰብ ሥራ ድጋፍ እንዲሰጥ ወደ ቆሮንቶስ ተልኳል። በተጨማሪም የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች ለጳውሎስ ደብዳቤ የሰጡትን ምላሽ እንዲያይ ሳይላክ አይቀርም።​—⁠2 ቆሮንቶስ 8:​1-6

  • ቲቶ “ስለ እናንተ አብሮኝ የሚሠራ ባልንጀራዬ”
    መጠበቂያ ግንብ—1998 | ኅዳር 15
    • ቲቶ በይሁዳ ለሚገኙ ቅዱሳን እርዳታ የማሰባሰቡን እንቅስቃሴ ለማደራጀት ወደ ቆሮንቶስ የተላከበት ሌላው ተልዕኮስ ምን ላይ ደርሶ ይሆን? በ2 ቆሮንቶስ ላይ ከሚገኘው ሐሳብ መረዳት እንደሚቻለው ቲቶ ይህንንም ጉዳይ ሲከታተል ቆይቷል። ይህ ደብዳቤ የተጻፈው ቲቶና ጳውሎስ ከተገናኙ በኋላ ብዙም ሳይቆይ በ55 እዘአ መጨረሻ ላይ በመቄዶንያ ሳይሆን አይቀርም። ቲቶ የጀመረውን እርዳታ የማሰባሰብ ሥራ እንዲያጠናቅቅ በስም ካልተጠቀሱ ሁለት ረዳቶቹ ጋር ተመልሶ እንደተላከ ጳውሎስ ጽፏል። ቲቶ ለቆሮንቶስ ሰዎች ልባዊ ፍቅር ስላለው ተመልሶ ለመሄድ በጣም ፈቃደኛ ነበር። ቲቶ ወደ ቆሮንቶስ ተመልሶ በሄደበት ወቅት ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በመንፈስ አነሳሽነት የጻፈላቸውን ሁለተኛውን ደብዳቤ ሳይዝ አይቀርም።​—⁠2 ቆሮንቶስ 8:​6, 17, 18, 22

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ