የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የመንግሥቱ ሥራዎች ወጪ የሚሸፈንበት መንገድ
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • 10 አንደኛ፣ ይሖዋን ስለምንወድና “በፊቱ ደስ የሚያሰኙትን ነገሮች” ማድረግ ስለምንፈልግ በፈቃደኝነት መዋጮ እናደርጋለን። (1 ዮሐ. 3:22) ይሖዋ፣ ከልቡ ተነሳስቶ ደስ እያለው በሚሰጥ አገልጋዩ ይደሰታል። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች ስለሚሰጡት ስጦታ የጻፈውን ሐሳብ እስቲ እንመርምር። (2 ቆሮንቶስ 9:7⁠ን አንብብ።) አንድ እውነተኛ ክርስቲያን የሚሰጠው ቅር እያለው ወይም ግድ ስለሆነበት አይደለም። ከዚህ ይልቅ ስጦታ የሚሰጠው ‘በልቡ ስላሰበ’ ወይም ልቡ ስለፈቀደ ነው።c በሌላ አባባል ልግስና የሚያደርገው ምን እንደሚያስፈልግና ይህንን ለማሟላት ምን ማድረግ እንደሚችል ካሰበበት በኋላ ነው። “አምላክ በደስታ የሚሰጠውን ሰው ስለሚወድ” እንዲህ ያለ ሰጪ በይሖዋ ዘንድ ተወዳጅ ነው። አንድ ሌላ ትርጉም “አምላክ መስጠት የሚወዱ ሰዎችን ይወዳል” ይላል።

  • የመንግሥቱ ሥራዎች ወጪ የሚሸፈንበት መንገድ
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • c አንድ ምሁር እንደተናገሩት እዚህ ጥቅስ ላይ “ያሰበውን” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “አስቀድሞ መወሰን የሚል ሐሳብ ያስተላልፋል።” አክለውም “መስጠት በማንኛውም ጊዜ ደስታ የሚያስገኝ ቢሆንም ስጦታው አስቀድሞ የታሰበበትና ዝግጅት የተደረገበት ሊሆን ይገባል” ብለዋል።—1 ቆሮ. 16:2

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ