የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የእርዳታ አገልግሎት
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • 6. (ሀ) ጳውሎስ እንደተናገረው የእርዳታ ሥራ የአምልኳችን ክፍል የሆነው ለምንድን ነው? (ለ) በዛሬው ጊዜ በዓለም ዙሪያ የእርዳታ ሥራ የምናከናውነው እንዴት እንደሆነ ግለጽ። (“አደጋ ሲከሰት!” የሚለውን በገጽ 214 ላይ የሚገኝ ሣጥን ተመልከት።)

      6 ጳውሎስ የእርዳታ ሥራ፣ ክርስቲያኖች የሚያከናውኑት አገልግሎትና ለይሖዋ የሚያቀርቡት አምልኮ ክፍል የሆነበትን ምክንያት እንዲገነዘቡ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን ረድቷቸዋል። ያቀረበውን ማስረጃ እንመልከት፦ እርዳታ የሚሰጡ ክርስቲያኖች ይህን የሚያደርጉት “ስለ ክርስቶስ ለሚገልጸው ምሥራች ተገዢዎች [ስለሆኑ]” እንደሆነ ተናግሯል። (2 ቆሮ. 9:13) ክርስቲያኖች የክርስቶስን ትምህርት በሥራ ማዋል ስለሚፈልጉ የእምነት ባልንጀሮቻቸውን ይረዳሉ። ጳውሎስ፣ ክርስቲያኖች ለወንድሞቻቸው ሲሉ የሚያከናውኑት የደግነት ተግባር “አምላክ [የሰጣቸው] የላቀ ጸጋ” መገለጫ እንደሆነ ተናግሯል። (2 ቆሮ. 9:14፤ 1 ጴጥ. 4:10) ከዚህ አንጻር፣ የታኅሣሥ 1, 1975 መጠበቂያ ግንብ (እንግሊዝኛ) የተቸገሩ ወንድሞቻችንን ስለማገልገል (የእርዳታ ሥራን ይጨምራል) የሚከተለውን ሐሳብ መስጠቱ የተገባ ነው፦ “ይሖዋ አምላክና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህ ዓይነቱ አገልግሎት ከፍ ያለ ቦታ እንደሚሰጡ ፈጽሞ ልንጠራጠር አይገባም።” በእርግጥም የእርዳታ ሥራ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ‘የቅዱስ አገልግሎት’ ክፍል ነው።—ሮም 12:1, 7፤ 2 ቆሮ. 8:7፤ ዕብ. 13:16

  • የእርዳታ አገልግሎት
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
    • 7, 8. የምናከናውነው የእርዳታ አገልግሎት የመጀመሪያ ዓላማ ምንድን ነው? አብራራ።

      7 የእርዳታ አገልግሎት የምንሰጥበት ዓላማ ምንድን ነው? ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው ሁለተኛ ደብዳቤ ላይ ለዚህ ጥያቄ መልስ ሰጥቷል። (2 ቆሮንቶስ 9:11-15⁠ን አንብብ።) ጳውሎስ “ሕዝባዊ አገልግሎት” ይኸውም የእርዳታ ሥራ የምናከናውንባቸውን ሦስት ዋና ዋና ዓላማዎች በዚህ ጥቅስ ላይ ጎላ አድርጎ ገልጿል። እስቲ እነዚህን ዓላማዎች አንድ በአንድ እንመልከታቸው።

      8 አንደኛ፣ የእርዳታ አገልግሎት መስጠታችን ለይሖዋ ክብር ያመጣል። ጳውሎስ ከላይ በተጠቀሱት አምስት ቁጥሮች ላይ ለወንድሞቹ ስለ ይሖዋ አምላክ ምን ያህል ደጋግሞ እንደተናገረ ልብ በል። ሐዋርያው ‘ለአምላክ ስለሚቀርብ ምስጋና’ እንዲሁም ‘ለአምላክ ስለሚቀርብ ብዙ ምስጋና’ ለወንድሞቹ ገልጾላቸዋል። (ቁጥር 11, 12) የእርዳታ ሥራ፣ ክርስቲያኖች “አምላክን እንዲያከብሩ” እንዲሁም ‘አምላክ የሰጣቸውን የላቀ ጸጋ’ እንዲያደንቁ እንደሚያደርግ ተናግሯል። (ቁጥር 13, 14) ጳውሎስ ስለ እርዳታ አገልግሎት የሰጠውን ሐሳብ የደመደመው “አምላክ የተመሰገነ ይሁን” በማለት ነው።—ቁጥር 15፤ 1 ጴጥ. 4:11

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ