-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ታኅሣሥ
-
-
ሐዋርያው ጳውሎስ “ወደ ሦስተኛው ሰማይ” እንዲሁም “ወደ ገነት [የተነጠቀው]” በምን መንገድ ነው?—2 ቆሮ. 12:2-4
በ2 ቆሮንቶስ 12:2, 3 ላይ ጳውሎስ “ወደ ሦስተኛው ሰማይ [ስለተነጠቀ]” ሰው ተናግሯል። ይህ ሰው ማን ነው? ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ጉባኤ በጻፈው ደብዳቤ ላይ አምላክ እሱን ሐዋርያ አድርጎ እየተጠቀመበት እንዳለ በአጽንዖት ገልጿል። (2 ቆሮ. 11:5, 23) ከዚያም ‘ከጌታ ስለተቀበላቸው ተአምራዊ ራእዮችና ጌታ ስለገለጠለት መልእክቶች’ ተናግሯል። ጳውሎስ ከዚህ ራእይ ጋር በተያያዘ ሌሎች ወንድሞችን አልጠቀሰም። በመሆኑም ራእዮችና መልእክቶች እንደተቀበለ ሰው አድርጎ የተናገረው ስለ ራሱ ነው ብሎ መደምደም ምክንያታዊ ነው።—2 ቆሮ. 12:1, 5
ስለዚህ “ወደ ሦስተኛው ሰማይ” እንዲሁም “ወደ ገነት [የተነጠቀው]” ሰው ጳውሎስ ነው። (2 ቆሮ. 12:2-4) ጳውሎስ ‘የተገለጡልኝ መልእክቶች’ የሚለውን አገላለጽ መጠቀሙ የተመለከታቸው ነገሮች ወደፊት የሚፈጸሙ መሆናቸውን ያመለክታል።
ጳውሎስ “ሦስተኛው ሰማይ” በማለት የገለጸው ነገር ምንድን ነው?
በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ሰማይ” የሚለው ቃል ግዑዙን ሰማይ ሊያመለክት ይችላል። (ዘፍ. 11:4፤ 27:28፤ ማቴ. 6:26) ይሁን እንጂ “ሰማይ” ሌሎች ነገሮችን ለማመልከትም ተሠርቶበታል። አንዳንድ ጊዜ ሰብዓዊ አገዛዝን ያመለክታል። (ዳን. 4:20-22) አሊያም ደግሞ እንደ አምላክ መንግሥት ያለውን መለኮታዊ አገዛዝ ሊያመለክት ይችላል።—ራእይ 21:1
ጳውሎስ ‘ሦስተኛውን ሰማይ’ እንዳየ ተናግሯል። ይህ ምን ያመለክታል? አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ አንድን ሐሳብ ለማጉላት፣ አጽንዖት ለመስጠት ወይም ክብደት ለመጨመር ያንን ሐሳብ ሦስት ጊዜ ይደጋግመዋል። (ኢሳ. 6:3፤ ሕዝ. 21:27፤ ራእይ 4:8) ከዚህ አንጻር ጳውሎስ ስለ “ሦስተኛው ሰማይ” ሲናገር ከፍ ያለ ወይም የላቀ አገዛዝን ይኸውም በኢየሱስ ክርስቶስና በ144,000 ተባባሪ ገዢዎች የሚመራውን መሲሐዊ መንግሥት ማመልከቱ ሳይሆን አይቀርም። (የጥቅምት 15, 2004 መጠበቂያ ግንብ፣ ገጽ 8 አን. 5ን ተመልከት።) ሐዋርያው ጴጥሮስ አምላክ በገባው ቃል መሠረት “አዲስ ሰማያት” እንደምንጠባበቅ ሲገልጽ ስለ መሲሐዊው መንግሥት እየተናገረ ነበር።—2 ጴጥ. 3:13
-
-
የአንባቢያን ጥያቄዎችመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ታኅሣሥ
-
-
በ2 ቆሮንቶስ 12:2 ላይ የተጠቀሰው “ሦስተኛው ሰማይ” የሚያመለክተው “አዲስ ሰማያት” ተብለው የተገለጹት ኢየሱስ ክርስቶስና 144,000ዎቹ የሚያስተዳድሩትን መሲሐዊ መንግሥት ሳይሆን አይቀርም።—2 ጴጥ. 3:13
“ሦስተኛው ሰማይ” የተባለው ይህ መንግሥት ከፍ ያለ ወይም የላቀ አገዛዝ ስለሆነ ነው።
-