የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | መስከረም 1
    • በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን እንደ መከራ፣ ችግርና ብቸኝነት ያሉ ሁኔታዎች እንድናዝን አልፎ ተርፎም ተስፋ እንድንቆርጥ ሊያደርጉን ይችላሉ። በእነዚህ ጊዜያት፣ ‘ማን ሊረዳኝ ይችላል?’ በማለት ትጠይቅ ይሆናል። ሐዋርያው ጳውሎስ በ2 ቆሮንቶስ 1:3, 4 ላይ ያሰፈረው ሐሳብ ይሖዋ አምላክ የማይነጥፍ የመጽናናት ምንጭ መሆኑን ይጠቁማል።

      በቁጥር 3 ላይ አምላክ “የርኅራኄ አባት” ተብሎ ተጠርቷል። ይህ ምን ማለት ነው? “ርኅራኄ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪከኛ ቃል መከራ ለደረሰባቸው ሰዎች መራራትን ያመለክታል።a አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ማመሳከሪያ ይህን ቃል አስመልክቶ “ሐዘኔታ ማሳየት” ወይም “ከልብ ማሰብ” ተብሎ ሊተረጎም እንደሚችል ገልጿል። አምላክ ‘ርኅሩኅ’ መሆኑ እርምጃ እንዲወስድ ያነሳሳዋል። አምላክ እንዲህ ያለ ባሕርይ እንዳለው ማወቃችን ወደ እሱ እንድንቀርብ አይገፋፋንም?

      በተጨማሪም ጳውሎስ፣ ይሖዋን ‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’ በማለት ጠርቶታል። ጳውሎስ እዚህ ላይ የተጠቀመበት ቃል “ችግር ወይም ሐዘን የደረሰበትን ሰው ማጽናናት ብሎም ማበረታቻ ወይም እርዳታ መስጠት” የሚል ሐሳብ ይዟል። ዚ ኢንተርፕሪተርስ ባይብል እንዳለው ከሆነ “መከራ የደረሰበት ሰው ችግሩን መቋቋም እንዲችል ማበረታቻ ስንሰጠው እያጽናናነው ነው።”

      ‘አምላክ የሚያጽናናን እና ችግራችንን ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት የሚሰጠን እንዴት ነው?’ በማለት ትጠይቅ ይሆናል። አምላክ በዋነኝነት እንዲህ የሚያደርገው በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስና በሰጠን የጸሎት መብት አማካኝነት ነው። ጳውሎስ “ቅዱሳት መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ እንዲኖረን” ሲል አምላክ በፍቅር ተነሳስቶ ቃሉን እንደሰጠን ነግሮናል። በተጨማሪም ከልብ የመነጨ ጸሎት በማቅረብ ‘ከማስተዋል በላይ የሆነውን የአምላክን ሰላም’ ማግኘት እንችላለን።—ሮሜ 15:4፤ ፊልጵስዩስ 4:7

  • ‘የመጽናናት ሁሉ አምላክ’
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | መስከረም 1
    • a አምላክ “የርኅራኄ አባት [ወይም የርኅራኄ ምንጭ]” ተብሎ ተጠርቷል። ምክንያቱም ርኅራኄ ከአምላክ የሚመነጭ ሲሆን ከባሕርያቱም መካከል አንዱ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ