የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 1
    • ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ “ድል ሰልፍ” ሲናገር በአእምሮው ምን ይዞ ሊሆን ይችላል?

      ▪ ጳውሎስ እንዲህ ሲል ጽፏል፦ “[አምላክ] በድል ሰልፍ ከክርስቶስ ጋር አብረን እንድንጓዝ በማድረግ [ይመራናል]፤ የእውቀቱ ሽታ በእኛ አማካኝነት በሁሉም ቦታ እንዲናኝ [ያደርጋል]። ምክንያቱም እኛ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ባሉት መካከልና ወደ ጥፋት እያመሩ ባሉት መካከል ለአምላክ የክርስቶስ መዓዛ ነን፤ ወደ ጥፋት እያመሩ ላሉት ሞት የሚያስከትል የሞት ሽታ፣ ወደ መዳን በሚወስደው ጎዳና ላይ ላሉት ደግሞ ሕይወት የሚያስገኝ የሕይወት ሽታ ነን።”—2 ቆሮንቶስ 2:14-16

      ሐዋርያው፣ በሮማውያን ልማድ መሠረት አንድ ጄኔራል በአገሩ ጠላቶች ላይ ድል ሲቀዳጅ ለጄኔራሉ ክብር ለመስጠት ሲባል የሚደረገውን የድል ሰልፍ እየጠቀሰ ነበር። በዚህ ጊዜ ምርኮውም ሆነ የጦር እስረኞቹ ለሕዝብ እይታ የሚቀርቡ ሲሆን በሬዎች መሥዋዕት ወደሚደረጉበት ስፍራ ይነዳሉ፤ ድል አድራጊው ጄኔራልና ሠራዊቱ ደግሞ ከሕዝቡ አድናቆትና ውዳሴ ይጎርፍላቸዋል። በሰልፉ መገባደጃ ላይ በሬዎቹ መሥዋዕት ይደረጋሉ፤ እንዲሁም አብዛኞቹ እስረኞች ይገደላሉ።

      ለአንዳንዶች ሕይወትን ለሌሎች ደግሞ ሞትን የሚያመለክተው “የክርስቶስ መዓዛ” የሚለው ተለዋጭ ዘይቤ “ምናልባት ሮማውያን የድል ሰልፉ በሚካሄድበት ጊዜ ያከናውኑት ከነበረው ዕጣን የማጨስ ልማድ የመጣ ሊሆን ይችላል” በማለት ዚ ኢንተርናሽናል ስታንዳርድ ባይብል ኢንሳይክሎፒዲያ ይገልጻል። “ላሸነፉት ሰዎች ድልን የሚያመለክተው መዓዛ ለምርኮኞቹ ደግሞ የሚጠብቃቸውን የሞት ቅጣት ያስታውሳቸዋል።”a

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
    መጠበቂያ ግንብ—2010 | ነሐሴ 1
    • a ጳውሎስ የተናገረውን ምሳሌ መንፈሳዊ ትርጉም በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት የኅዳር 15, 1990 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 27⁠ን ተመልከት።

      [በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

      የሮማውያንን የድል ሰልፍ የሚያሳይ ምስል፣ ሁለተኛ መቶ ዘመን ዓ.ም.

      [ምንጭ]

      Photograph taken by courtesy of the British Museum

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ