የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘ሽማግሌዎችን ጥራ’
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | ግንቦት 15
    • 18, 19. ከገላትያ 6:​2, 5 ጋር በተያያዘ ሁኔታ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ምን ሚና ይጫወታሉ?

      18 ክርስቲያን ሽማግሌዎች የአምላክን መንጋ በተመለከተ ያለባቸውን ኃላፊነት መወጣት አለባቸው። ሽማግሌዎች ድጋፍ ሰጪዎች መሆን አለባቸው። ለምሳሌ ያህል ጳውሎስ እንዲህ ብሏል:- “ወንድሞች ሆይ፣ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፣ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ። ከእናንተ እያንዳንዱ የአንዱን ሸክም ይሸከም እንዲሁም የክርስቶስን ሕግ ፈጽሙ።” በተጨማሪም ሐዋርያው ጳውሎስ “እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ሊሸከም ነውና” ሲል ጽፏል። — ገላትያ 6:​1, 2, 5

      19 የራሳችንን ሸክም እየተሸከምን የሌላውንም ጭምር መሸከም የምንችለው እንዴት ነው? በእንግሊዝኛ “በርደን” (ጭነት) እና “ሎድ” (ሸክም) ተብለው በተተረጎሙት የግሪክኛ ቃላት መካከል ያለው የትርጉም ልዩነት መልሱን ይሰጠናል። አንድ ክርስቲያን መንፈሳዊ ችግር ውስጥ ቢገባና ይህ ችግር ለእሱ ከባድ ጭነት ቢሆንበት ሽማግሌዎችና ሌሎች መሰል አማኞች ይረዱታል። በዚህ መንገድ “ሸክሙን” (በእንግሊዝኛው “በርደን”) በመሸከም ያግዙታል። ነገር ግን ግለሰቡ ለአምላክ ያለበትን የኃላፊነት “ሸክም” (በእንግሊዝኛው “ሎድ”) ራሱ መሸከም አለበት።a ሽማግሌዎች ማበረታቻና ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክር በመስጠት እንዲሁም በጸሎት የወንድሞቻቸውን “ጭነት” በደስታ ይሸከማሉ። ይሁን እንጂ ሽማግሌዎች የግላችንን መንፈሳዊ የኃላፊነት “ሸክም” ሊያወርዱልን አይችሉም። — ሮሜ 15:​1

  • ‘ሽማግሌዎችን ጥራ’
    መጠበቂያ ግንብ—1993 | ግንቦት 15
    • a በፍሪትስ ረንከር የተዘጋጀው ኤ ሊንጉስቲክ ኪ ቱ ዘ ግሪክ ኒው ቴስታመንት የተባለው መጽሐፍ ፎርቲዎን ለተባለው ቃል ፍቺ ሲሰጥ “አንድ ሰው መሸከም ያለበት ሸክም” ይላል። አክሎም:- “ቃሉ የአንድን ሰው ጓዝ ወይም የአንድን ወታደር ትጥቅና ስንቅ ለመግለጽ የሚያገለግል ወታደራዊ ቃል ነው” ይላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ