የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክ ‘ከወዳጁ’ ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን በብዙ ሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ጠቃሚ ሆኖአል
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 11. ሐዋርያው ጳውሎስ የአብርሃም ሥጋዊ ዝርያዎች ምን እንደደረሰባቸው ያብራራው እንዴት ነው?

      11 ሐዋርያው ጳውሎስ ጉዳዩን እንዲህ በማለት ያብራራልናል:- “አንዱ ከባሪያይቱ (ከአጋር) አንዱም [ከነፃዋ (አዓት)] (ከሣራ) የሆኑ ሁለት ልጆች ለአብርሃም እንደነበሩት ተጽፎልናል። ነገር ግን የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዷል፣ [የነፃዋ ልጅ (አዓት)] ግን በተስፋው ቃል ተወልዷል። ይህም ነገር (ምሳሌያዊ ድራማ) ነው፤ እነዚህ ሴቶች እንደ ሁለቱ ኪዳኖች ናቸው። ከደብረ ሲና (ከሲና ተራራ) የሆነችው አንዲቱ ለባርነት ልጆችን ትወልዳለች፣ እርሷም አጋር ናት። ይህችም አጋር በዓረብ ምድር ያለችው ደብረሲና ናት፤ አሁንም ያለችውን ኢየሩሳሌምን ትመስላለች፣ ከልጆችዋ ጋር በባርነት ናትና። ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም ግን በነፃነት የምትኖር ናት እርሷም እናታችን ናት።”— ገላትያ 4:22–26

  • አምላክ ‘ከወዳጁ’ ጋር ያደረገው ቃል ኪዳን በብዙ ሚልዮን ለሚቆጠሩ ሰዎች ጠቃሚ ሆኖአል
    “የሰላሙ መስፍን“ ሲገዛ በምድር ዙሪያ የሚገኝ ዋስትና ያለው ሕይወት
    • 13. (ሀ) በአብርሃም ሚስት በሣራ የተመሰለችው ምንድን ናት? (ለ) “ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” “ነፃ” ናት ለማለት የሚቻለው ለምንድን ነው?

      13 በሌላው በኩል ግን “ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” የይሖዋ የማይታይ ሰማያዊት ድርጅት ነበረች። በተመሳሳይ መንገድ በአንዲት ሴት ማለትም የአብርሃም እውነተኛ ሚስት በነበረችው በሣራ ልትመሰል ችላለች። የሕጉ ቃል ኪዳን የተደረገው ከዚህች ድርጅት ጋር አልነበረም፤ በዚህም ምክንያት “ላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” እንደ ጥንትዋ ሣራ ነፃ ነበረች። የተስፋውን “ዘር” የምታስገኝ ድርጅት ይህች ነበረች። ሐዋርያው ጳውሎስ “እናታችን” ብሎ ሊጠራት የቻለውም ለዚህ ነው።

      14. የአብርሃም ቃል ኪዳን “ለላይኛይቱ ኢየሩሳሌም” ይሠራልን? ስለዚህ በመንፈስ የተዋጁት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት ምን ተብለው ሊጠሩ ይችላሉ?

      14 እንግዲያው በእርግጥም እርስዋ የታላቁ አብርሃም ምሳሌያዊት ሚስት እንደመሆንዋ የአብርሃም ቃል ኪዳን በእርስዋ ላይ ይሠራል። አዎ፤ በሰማያት ለምትገኘው የይሖዋ ጽንፈ ዓለማዊት ድርጅት ይሠራል። ይህ ከሆነ ደግሞ እንደ ሐዋርያው ጳውሎስ ያሉት በመንፈስ የተመረጡት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የአብርሃም ቃል ኪዳን ወንዶች ልጆች ወይም ልጆች ናቸው። ጳውሎስ እንደሚከተለው በማለት ጉዳዩን በዚህ መንገድ ማብራራቱን ይቀጥላል:-

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ