የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 4 | በአምላክ እርዳታ ጥላቻን ድል አድርግ
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022 | ቁጥር 1
    • የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት፦

      “የመንፈስ ፍሬ ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ደግነት፣ ጥሩነት፣ እምነት፣ ገርነት፣ ራስን መግዛት ነው።”—ገላትያ 5:22, 23

      ምን ማለት ነው?

      በአምላክ እርዳታ የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ እንችላለን። የአምላክ ቅዱስ መንፈስ በራሳችን ልናዳብር የማንችላቸውን ግሩም ባሕርያት እንድናፈራ ያስችለናል። ስለዚህ በራሳችን ኃይል ጥላቻን ለማሸነፍ ከመሞከር ይልቅ በአምላክ እርዳታ መታመናችን የተሻለ ነው። እንዲህ ካደረግን የሐዋርያው ጳውሎስ ዓይነት ስሜት ይኖረናል፤ ጳውሎስ “ኃይልን በሚሰጠኝ በእሱ አማካኝነት ለሁሉም ነገር የሚሆን ብርታት አለኝ” በማለት ጽፏል። (ፊልጵስዩስ 4:13) በእርግጥም “እኔን የሚረዳኝ . . . ይሖዋ ነው” ማለት እንችላለን።—መዝሙር 121:2

  • 4 | በአምላክ እርዳታ ጥላቻን ድል አድርግ
    መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2022 | ቁጥር 1
    • ዎልዶ ባለቤቱ መጽሐፍ ቅዱስን ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር ማጥናት ስትጀምር አልተደሰተም ነበር። እንዲህ ብሏል፦ “የይሖዋ ምሥክሮችን እጠላቸው ስለነበር ብዙ ጊዜ መጥፎ ስድብ ሰድቤያቸዋለሁ። እነሱ ግን ምንጊዜም በሰላማዊ መንገድ ያናግሩኝ ነበር።”

      ውሎ አድሮ ዎልዶም መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመረ። ዎልዶ “የምማረውን ነገር በሥራ ላይ ማዋል ቀላል አልነበረም። የግልፍተኝነት ጠባዬን መቆጣጠር ፈጽሞ እንደማይሳካልኝ ተሰምቶኝ ነበር” ብሏል። ሆኖም ከመጽሐፍ ቅዱስ ያገኘው አንድ ትምህርት በሕይወቱ ላይ ትልቅ ለውጥ አምጥቷል።

      ዎልዶ እንዲህ ብሏል፦ “መጽሐፍ ቅዱስን የሚያስጠናኝ አሌሃንድሮ፣ አንድ ቀን ገላትያ 5:22, 23⁠ን እንዳነብብ ጠየቀኝ። . . . አሌሃንድሮ እነዚህን ባሕርያት ማዳበር የምችለው በራሴ ጥንካሬ ሳይሆን በአምላክ ቅዱስ መንፈስ እርዳታ እንደሆነ ገለጸልኝ። ይህ እውነት አመለካከቴን ሙሉ በሙሉ ለወጠው!”

      ዎልዶ በአምላክ እርዳታ በመታመን የጥላቻን ሰንሰለት መበጠስ ችሏል። እንዲህ ብሏል፦ “ዘመዶቼና የቀድሞ ጓደኞቼ ያደረግሁትን ለውጥ ማመን ያቅታቸዋል።” አክሎም “ግልፍተኛ የነበርኩት ሰው ተለውጬ ሰላማዊ እንድሆን ይሖዋ ረድቶኛል” ብሏል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ