የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክርስቶስ የደረሰበት የጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ እየተጣጣራችሁ ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መስከረም 15
    • 2 አንድ ሰው ራሱን ወስኖ ከተጠመቀም በኋላ እድገት ማድረጉን ይቀጥላል። ግቡ የጎለመሰ የአምላክ አገልጋይ መሆን ነው። እዚህ ላይ እየተናገርን ያለነው ስለ አካላዊ ጉልምስና ሳይሆን ስለ መንፈሳዊ ጉልምስና ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ በኤፌሶን ያሉ ክርስቲያኖች በመንፈሳዊ እድገት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ጽፎላቸዋል። “በእምነትና ስለ አምላክ ልጅ ትክክለኛ እውቀት በመቅሰም ወደሚገኘው አንድነት እንዲሁም ሙሉ ሰው ወደ መሆን ይኸውም እንደ ክርስቶስ የተሟላ የጉልምስና ደረጃ ላይ” ለመድረስ እንዲጣጣሩ አበረታቷቸዋል።—ኤፌ. 4:13

      3. በኤፌሶን ጉባኤና በዛሬው ጊዜ በሚገኙት የይሖዋ ሕዝቦች መካከል ምን ተመሳሳይ ሁኔታ ይታያል?

      3 ጳውሎስ ደብዳቤውን በጻፈበት ወቅት የኤፌሶን ጉባኤ ከተቋቋመ የተወሰኑ ዓመታት አልፈው ነበር። በዚያ የሚገኙ በርካታ ደቀ መዛሙርት ከፍ ያለ መንፈሳዊ የእድገት ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር። አንዳንዶቹ ግን አሁንም ወደ ጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋቸው ነበር። በዛሬው ጊዜ በይሖዋ ምሥክሮች መካከል ያለው ሁኔታ ተመሳሳይ ነው። ብዙዎቹ ወንድሞችና እህቶች አምላክን ረዘም ላሉ ዓመታት ሲያገለግሉ የቆዩና በመንፈሳዊ የጎለመሱ ናቸው። ሆኖም ሁሉም የጉልምስና ደረጃ ላይ ደርሰዋል ማለት አይደለም። ለምሳሌ ያህል፣ በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አዳዲስ ሰዎች ይጠመቃሉ፤ እነዚህ ሰዎች ደግሞ መንፈሳዊ ጉልምስና ላይ ለመድረስ ጥረት ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። አንተስ እድገት ማድረግ ያስፈልግህ ይሆን?—ቆላ. 2:6, 7

  • ክርስቶስ የደረሰበት የጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ እየተጣጣራችሁ ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መስከረም 15
    • 5 አንድ የጎለመሰ የይሖዋ አገልጋይ በአኗኗሩ ኢየሱስን ለመምሰልና ‘የእሱን ፈለግ በጥብቅ ለመከተል’ ጥረት ያደርጋል። (1 ጴጥ. 2:21) ኢየሱስ ይበልጥ አስፈላጊ እንደሆነ አድርጎ የገለጸው ነገር ምንድን ነው? ይሖዋን በሙሉ ልብ፣ ነፍስና አእምሮ መውደድ እንዲሁም ባልንጀራን እንደ ራስ መውደድ ነው። (ማቴ. 22:37-39) አንድ የጎለመሰ ክርስቲያን ይህን ምክር ተግባራዊ ለማድረግ ይጥራል። አኗኗሩ ከይሖዋ ጋር ለመሠረተው ዝምድና ቅድሚያ እንደሚሰጥና ለሌሎች የራስን ጥቅም መሥዋዕት የሚያደርግ ፍቅር እንዳለው ያሳያል።

  • ክርስቶስ የደረሰበት የጉልምስና ደረጃ ላይ ለመድረስ እየተጣጣራችሁ ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | መስከረም 15
    • 8. ኢየሱስ ቅዱሳን መጻሕፍትን በተመለከተ ስለነበረው እውቀትና ግንዛቤ ምን ማለት ይቻላል?

      8 ኢየሱስ ክርስቶስ የአምላክን ቃል በሚገባ ያውቅ ነበር። ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ በቤተ መቅደሱ ካሉ አስተማሪዎች ጋር ቅዱሳን መጻሕፍትን እየጠቀሰ ይወያይ ነበር። “በዚያ የነበሩት ሰዎችም ሁሉ በመረዳት ችሎታውና በመልሱ ተደንቀው ያዳምጡት ነበር።” (ሉቃስ 2:46, 47) ከጊዜ በኋላ ምድራዊ አገልግሎቱን ባከናወነበት ወቅት ከአምላክ ቃል ላይ ተስማሚ የሆኑ ሐሳቦችን በመጥቀስ ተቃዋሚዎቹን አፋቸውን አስይዟቸዋል።—ማቴ. 22:41-46

      9. (ሀ) መንፈሳዊ እድገት ማድረግ የሚፈልግ ሰው መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ረገድ ምን ዓይነት ልማድ ማዳበር ይኖርበታል? (ለ) መጽሐፍ ቅዱስን የምናጠናበት ዓላማ ምንድን ነው?

      9 በመንፈሳዊ እድገት ማድረግ የሚፈልግ ክርስቲያን ኢየሱስ የተወውን ምሳሌ በመከተል ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ጥልቅ ግንዛቤ እንዲኖረው የተቻለውን ጥረት ያደርጋል። ‘ጠንካራ ምግብ ለጎልማሳ ሰዎች’ እንደሆነ በመገንዘብ በየጊዜው ቃሉን በጥልቀት ይቆፍራል። (ዕብ. 5:14) አንድ ጎልማሳ ክርስቲያን “ስለ አምላክ ልጅ ትክክለኛ እውቀት” መቅሰም እንደሚፈልግ የታወቀ ነው። (ኤፌ. 4:13) በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን የምታነብበት ፕሮግራም አለህ? የግል ጥናት የምታደርግበትስ ቋሚ ፕሮግራም አለህ? በየሳምንቱ የቤተሰብ አምልኮ ለማድረግ ጊዜ መድበሃል? የአምላክን ቃል ስታጠና የይሖዋን አመለካከትና ስሜት ይበልጥ እንድትረዳ የሚያስችሉህን ቅዱስ ጽሑፋዊ መሠረታዊ ሥርዓቶች ለማግኘት ጥረት አድርግ። ከዚያም በመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ላይ ተመሥርተህ ውሳኔ አድርግ፤ እንዲህ የምታደርግ ከሆነ ይበልጥ ወደ ይሖዋ እየቀረብክ ትሄዳለህ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ