የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሁሉም በዓላት አምላክን ያስደስታሉ?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • ኤፌሶን 5:10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • አንድን በዓል ለማክበር ወይም ላለማክበር ስንወስን የትኛውን ነገር ማረጋገጥ ያስፈልገናል?

      • አንተ በምትኖርበት አካባቢ የትኞቹ በዓላት በስፋት ይከበራሉ?

      • እነዚህ በዓላት ይሖዋን የሚያስደስቱት ይመስልሃል?

      ለምሳሌ ያህል፣ አምላክ የልደት በዓልን ስለማክበር ምን እንደሚሰማው አስበህ ታውቃለህ? የይሖዋ አገልጋዮች ልደታቸውን እንዳከበሩ የሚገልጽ አንድም ሐሳብ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አይገኝም፤ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ልደታቸውን እንዳከበሩ የተገለጹት ሁለት ሰዎች ሲሆኑ እነሱም ይሖዋን የማያገለግሉ ናቸው። ዘፍጥረት 40:20-22⁠ን እና ማቴዎስ 14:6-10⁠ን አንብቡ። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • ሁለቱን የልደት በዓላት የሚያመሳስላቸው ምንድን ነው?

      • ከእነዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በመነሳት ይሖዋ ልደት ስለማክበር ምን የሚሰማው ይመስልሃል?

      ያም ሆኖ እንዲህ ብለህ ልታስብ ትችላለህ፦ ‘የልደት በዓልን ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ድጋፍ የሌላቸውን ሌሎች በዓላት ማክበሬ በእርግጥ ለይሖዋ ያን ያህል ግድ ይሰጠዋል?’ ዘፀአት 32:1-8⁠ን አንብቡ። ከዚያም ቪዲዮውን ተመልከቱና በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ ይሖዋን የማያስደስቱ ክብረ በዓላት (5:07)

      • በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ያለውን ነገር መርምረን ማረጋገጥ ያለብን ለምንድን ነው?

      • እንዲህ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?

      አምላክን የማያስደስቱ በዓላትን ለመለየት የሚረዱ ጥያቄዎች

      • ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በሚጋጭ ትምህርት ላይ የተመሠረተ ነው? ይህን ለማወቅ በበዓሉ አመጣጥ ላይ ምርምር አድርግ።

      • ለሰዎች፣ ለድርጅቶች ወይም ለብሔራዊ ዓርማዎች ከልክ ያለፈ ክብር የሚሰጥ ነው? ከማንም በላይ ክብር የምንሰጠው ለይሖዋ ነው፤ ደግሞም የዓለምን ችግሮች ሊፈታ የሚችለው እሱ ብቻ ነው።

      • በበዓሉ ወቅት የሚፈጸሙት ልማዶች ከመጽሐፍ ቅዱስ መሥፈርቶች ጋር የሚጋጩ ናቸው? በሥነ ምግባር ንጹሕ መሆን ያስፈልገናል።

  • የመዝናኛ ምርጫህ ይሖዋን የሚያስደስት ይሁን
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • ምዕራፍ 53. አንድ አባት፣ እናትና ልጅ ፈንዲሻ እየበሉ ቴሌቪዥን ሲመለከቱ

      ምዕራፍ 53

      የመዝናኛ ምርጫህ ይሖዋን የሚያስደስት ይሁን

      ይሖዋ ‘ደስተኛ አምላክ’ ነው። (1 ጢሞቴዎስ 1:11) እኛም ደስተኛ እንድንሆን እንዲሁም ከሥራ አረፍ ብለን ዘና የምንልበት ጊዜ እንድንመድብ ይፈልጋል። በዚህ ምዕራፍ ላይ ትርፍ ጊዜያችንን አስደሳች በሆነና ይሖዋን በሚያስደስት መንገድ መጠቀም የምንችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

      1. መዝናኛ ስንመርጥ ምን ማስታወስ ይኖርብናል?

      በትርፍ ጊዜህ ምን ማድረግ ያስደስትሃል? አንዳንዶች ቤታቸው ሆነው መጽሐፍ ማንበብ፣ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ፊልም ማየት ወይም ኢንተርኔት መቃኘት ያስደስታቸዋል። ሌሎች ደግሞ ከጓደኞቻቸው ጋር ሆነው ኳስ መጫወት ወይም በሌሎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች መካፈል ይመርጣሉ። የመዝናኛ ምርጫችን ምንም ሆነ ምን “በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ያለው” መሆኑን ማረጋገጥ አለብን። (ኤፌሶን 5:10) እንዲህ ማድረጋችን አስፈላጊ ነው፤ ምክንያቱም በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ በርካታ መዝናኛዎች እንደ ዓመፅ፣ የፆታ ብልግናና መናፍስታዊ ድርጊት ያሉ ይሖዋ የሚጠላቸውን ነገሮች ያካትታሉ። (መዝሙር 11:5⁠ን አንብብ።) ታዲያ ጥሩ መዝናኛ ለመምረጥ ምን ይረዳናል?

      ይሖዋን ከሚወዱ ሰዎች ጋር መቀራረባችን በእኛም ሆነ በመዝናኛ ምርጫችን ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል። ከዚህ በፊት እንደተመለከትነው “ከጥበበኞች ጋር የሚሄድ ጥበበኛ ይሆናል።” በሌላ በኩል ግን የአምላክን መሥፈርቶች ከማይወዱ ሰዎች ጋር የምንቀራረብ ከሆነ ‘ጉዳት ይደርስብናል።’—ምሳሌ 13:20

      2. በመዝናናት በምናሳልፈው ጊዜ ላይ ገደብ ማበጀታችን አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

      የምንመርጠው መዝናኛ ምንም ችግር ባይኖረው እንኳ በመዝናናት ከልክ ያለፈ ጊዜ እንዳናሳልፍ መጠንቀቅ ይኖርብናል። በመዝናናት ከልክ ያለፈ ጊዜ የምናሳልፍ ከሆነ ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች የምናውለው ጊዜ ላናገኝ እንችላለን። መጽሐፍ ቅዱስ ‘ጊዜያችንን በተሻለ መንገድ እንድንጠቀምበት’ ያበረታታናል።—ኤፌሶን 5:15, 16⁠ን አንብብ።

      ጠለቅ ያለ ጥናት

      ጥሩ መዝናኛ መምረጥ የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

      3. ከመጥፎ መዝናኛ ራቅ

      የምንዝናናበትን ነገር በጥንቃቄ መምረጥ ያለብን ለምንድን ነው? ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ ምን ዓይነት መዝናኛ መምረጥ ይኖርብኛል? (4:39)

      • በጥንቷ ሮም የነበሩ ጨዋታዎች በዘመናችን ካሉ አንዳንድ መዝናኛዎች ጋር የሚመሳሰሉት እንዴት ነው?

      • በቪዲዮው ላይ ዳኒ ከመዝናኛ ጋር በተያያዘ ምን ትምህርት አግኝቷል?

      ሮም 12:9⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ይህ ጥቅስ ጥሩ መዝናኛ ለመምረጥ የሚረዳህ እንዴት ነው?

      ይሖዋ የሚጠላቸው አንዳንድ ነገሮች ምንድን ናቸው? ምሳሌ 6:16, 17⁠ን እንዲሁም ገላትያ 5:19-21⁠ን አንብቡ። እያንዳንዱን ጥቅስ ካነበባችሁ በኋላ በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በዚህ ጥቅስ ላይ ከተዘረዘሩት ነገሮች መካከል በዘመናችን ባሉ መዝናኛዎች ላይ በስፋት የሚታዩት የትኞቹ ናቸው?

      ጥሩ መዝናኛ ለመምረጥ ምን ይረዳሃል?

      የሚከተሉትን ጥያቄዎች አስብባቸው፦

      • ምን? መዝናኛው ይሖዋ የሚጠላውን ነገር ያካትታል?

      • መቼ? ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑ ነገሮች ጊዜ ያሳጣኛል?

      • ማን? ይሖዋን ከማይወዱ ሰዎች ጋር እንድቀራረብ ወይም አዘውትሬ ጊዜ እንዳሳልፍ ያደርገኛል?

      አደጋ ከሚያስከትል ነገር የቻልነውን ያህል መራቃችን አስፈላጊ እንደሆነ ሁሉ ሊጎዳን ይችላል ብለን ከምናስበው ከማንኛውም መዝናኛ መራቃችንም አስፈላጊ ነው

      በተራራማ መንገድ ላይ ወደ ገደሉ ተጠግቶ እየሄደ ያለ መኪና። መኪናው ከኋላው በኩል ወደ ገደሉ መንሸራተት ጀምሯል

      4. ጊዜህን በጥበብ ተጠቀም

      ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ ጊዜያችሁን የሚይዝባችሁ ምንድን ነው? (2:45)

      • በቪዲዮው ላይ የታየው ወንድም መጥፎ ነገር ባይመለከትም ትርፍ ጊዜውን የሚጠቀምበት መንገድ ምን ተጽዕኖ አሳድሮበታል?

      ፊልጵስዩስ 1:10⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ይህ ጥቅስ በመዝናኛ ምን ያህል ጊዜ ማሳለፍ እንዳለብን ለመወሰን የሚረዳን እንዴት ነው?

      5. ጥሩ መዝናኛ ምረጥ

      አንዳንዶቹ መዝናኛዎች ይሖዋን አያስደስቱም፤ ሆኖም ይሖዋን የሚያስደስቱ በርካታ መዝናኛዎች አሉ። መክብብ 8:15⁠ን እና ፊልጵስዩስ 4:8⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • አንተን የሚያስደስትህ ጥሩ መዝናኛ ምንድን ነው?

      በተለያየ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎች ጤናማ በሆነ መዝናኛ ሲዝናኑ፦ 1. አንዲት ልጅ ሙዚቃ እያዳመጠች ሥዕል ስትሥል 2. ሦስት ወጣት ወንዶች ቅርጫት ኳስ ሲጫወቱ 3. ሁለት ልጆች ብስክሌት ሲነዱ 4. አንድ ልጅ የአሻንጉሊት መኪና ሲሠራ 5. አንድ ሰው ከበሮ ሲጫወት 6. አንድ ልጅ ከአባቱ ጋር ቪዲዮ ጌም ሲጫወት 7. አንዲት ሴት ፎቶግራፍ ስታነሳ

      ጥሩ በሆኑ መዝናኛዎች መደሰት ትችላለህ

      አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ራሴ እስካላደረግኩት ድረስ ዓመፅ፣ የፆታ ብልግና ወይም መናፍስታዊ ድርጊት በሚታይበት መዝናኛ ብዝናና ምንም ችግር የለውም።”

      • አንተ ምን ትላለህ?

      ማጠቃለያ

      ይሖዋ ጥሩ መዝናኛ እንድንመርጥ እና እንዲህ ባሉ መዝናኛዎች እንድንደሰት ይፈልጋል።

      ክለሳ

      • ክርስቲያኖች ከየትኞቹ መዝናኛዎች ሊርቁ ይገባል?

      • በመዝናናት በምናሳልፈው ጊዜ ላይ ገደብ ማበጀት ያለብን ለምንድን ነው?

      • ይሖዋን የሚያስደስት መዝናኛ መምረጥ የምትፈልገው ለምንድን ነው?

      ግብ

      ምርምር አድርግ

      የምንመርጠውን መዝናኛ ሊወስንልን የሚገባው ማን ነው?

      “የይሖዋ ምሥክሮች አንዳንድ ፊልሞችን፣ መጻሕፍትን ወይም ዘፈኖችን ይከለክላሉ?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

      ከመዝናኛዎችና ከትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ጋር በተያያዘ ጥሩ ውሳኔ ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

      “የምትመርጡት መዝናኛ ጠቃሚ ነው?” (መጠበቂያ ግንብ ጥቅምት 15, 2011)

      ‘የነበረኝን ጭፍን ጥላቻ አስወገድኩ’ የሚል ርዕስ ባለው የሕይወት ታሪክ ላይ አንድ ሰው በመዝናኛ ምርጫው ላይ ማስተካከያ ያደረገው ለምን እንደሆነ ተመልከት።

      “መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል” (መጠበቂያ ግንብ የካቲት 1, 2010)

      አንዲት እናት መናፍስታዊ ድርጊቶች የሚታዩባቸውን ፊልሞች በተመለከተ ጥሩ ውሳኔ እንድታደርግ የረዳት ምንድን ነው?

      መናፍስታዊ ድርጊቶች ከሚታዩባቸው መዝናኛዎች ራቁ (2:02)

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ