-
በጋብቻ ውስጥ መገዛት ማለት ምን ማለት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1991 | ታኅሣሥ 15
-
-
አንዲት ክርስቲያን ሴት ስታገባ በሕይወትዋ ውስጥ ብዙ ለውጥ ለማድረግ ትገደዳለች። ከእነዚህ ለውጦችና ማስተካከያዎች ሁሉ ከፍተኛ የሆነው የግል ነፃነቷን የሚነካ ነው። ነጠላ ሆና ትኖር በነበረችበት ጊዜ ማንንም ሳታማክር ብዙዎቹን ውሳኔዎቿን በራስዋ ለማድረግ ነፃ የነበረች ልትሆን ትችላለች። አሁን ግን ባል ስላላት እሱን የማማከርና በራሷ ውሳኔ ታደርጋቸው የነበሩትን ብዙ ነገሮች ከማድረግዋ በፊት የባልዋን ፈቃድ የመጠየቅ ግዴታ አለባት። ይህ የሆነው ለምንድን ነው?
ይህ የሆነው የሰው ልጆች ፈጣሪ የመጀመሪያዋን ሴት በጋብቻ ለመጀመሪያው ወንድ ሲሰጥ ወንዱን የሚስቱና ወደፊት የሚወለዱት ልጆች ራስ እንዲሆን ስላደረገው ነው። ይህም ምክንያታዊ ነገር ነው። በቡድን የተደራጁ ሰዎች ባሉበት ቦታ ሁሉ አንድ ሰው የመሪነት ቦታ እንዲወስድና የመጨረሻ ውሳኔዎችን እንዲያደርግ ያስፈልጋል። በጋብቻ ረገድ “ባል የሚስቱ ራስ” እንዲሆን ፈጣሪ ደንግጓል።—ኤፌሶን 5:23
መለኮታዊው ትእዛዝ ይህን በመደገፍ “ሚስቶች ሆይ፣ ለባሎቻችሁ ተገዙ” ይላል። (ኤፌሶን 5:22) ሚስት ለዚህ ዝግጅት የሚኖራት ዝንባሌ በሁለት ነገሮች ላይ የተመካ ነው። (1) ዝግጅቱን ለማክበር ምን ያህል ፈቃደኛ ናት? (2) ባሏስ ሥልጣኑን የሚጠቀምበት እንዴት ነው? ሐቁ ሁለቱም ተጋቢዎች በተገቢ ሁኔታ ከተመለከቱት ይህ ዝግጅት ለሚስት፣ ለባልና ለልጆቻቸው በረከት መሆኑ ነው።
-
-
በጋብቻ ውስጥ መገዛት ማለት ምን ማለት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1991 | ታኅሣሥ 15
-
-
መገዛት አንጻራዊ ነው
ባል በሚስቱ ላይ ያለው ሥልጣን ፍጹም አይደለም። በአንዳንድ መንገዶች ሚስቶች በሚስትነታቸው ረገድ የሚያሳዩት መገዛት ክርስቲያኖች ለዓለማዊ ገዥዎች ከሚያሳዩት መገዛት ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ክርስቲያን “ለበላይ ባለ ሥልጣኖች መገዛት” እንዳለበት አምላክ ደንግጓል። (ሮሜ 13:1) ሆኖም ይህ መገዛት አምላክ ከሚፈልግብን ነገር ጋር መመዛዘን አለበት። ኢየሱስ “የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” ብሏል። (ማርቆስ 12:17) ቄሳር (ዓለማዊ መንግሥት) ለአምላክ የሚገባውን እንድንሰጠው ከጠየቀ ሐዋርያው ጴጥሮስ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል” ሲል የተናገረውን እናስታውሳለን።—ሥራ 5:29
ከዚህ ጋር በሚመሳሰል መንገድ አንዲት ክርስቲያን ሴት ክርስቲያናዊ ሥነ ሥርዓቶችን የማይረዳ ወይም የማያከብር ሰው አግብታ ከሆነ እርግጥ ለሱ የመገዛት ግዴታ አለባት። በዚህ አምላክ ባዘዘው ዝግጅት ላይ ከማመፅ ይልቅ ፍቅርና አሳቢነት በማሳየት ብትታዘዝና እምነት እንዲያሳድርባት ለማድረግ ብትጥር መልካም ታደርጋለች። ምናልባትም ይህ ዓይነቱ መልካም ጠባይ ባሏን እንዲለወጥ ያደርገው ይሆናል። ወደ እውነት ሊስበው ይችል ይሆናል። (1 ጴጥሮስ 3:1, 2) ባሏ አንድ በአምላክ የተከለከለ ነገር እንድታደርግ ቢያዛት ዋናው ገዥዋ አምላክ መሆኑን ማስታወስ አለባት። ለምሳሌ ያህል ሚስት መለዋወጥን የመሰለ ከስነ ምግባር ውጭ የሆነ የጾታ ድርጊት እንድትፈጽም ቢጠይቃት ላለመታዘዝ ትገደዳለች። (1 ቆሮንቶስ 6:9, 10) ለባሏ የምታሳየውን ተገዢነት የሚወስነው ሕሊናዋና ከሁሉ በላይ ለአምላክ የምትገዛ መሆንዋ ነው።
በንጉሥ ዳዊት ዘመን አቢጋኤል አምላካዊ ስነ ሥርዓቶችን የማያከብርና ዳዊትንና ከእርሱ ጋር የነበሩትን ሰዎች ፍቅር በጐደለው ሁኔታ ያንቋሸሸ ናባል የሚባል ሰው አግብታ ነበር። ዳዊትና የዳዊት ሰዎች የናባልን በሺህ የሚቆጠሩ በጎችና ፍየሎች ይጠብቁለት ነበር። ነገር ግን ዳዊት የምግብ እርዳታ በጠየቀው ጊዜ ናባል ምንም ነገር ለመስጠት እምቢ አለ።
አቢጋኤል ባሏ ያሳየውን የንፉግነት ዝንባሌ በቤተሰቧ ላይ አደጋ እንደሚያመጣ ባወቀች ጊዜ ለዳዊት ምግብ ለመውሰድ ራሷ ወሰነች። “አቢጋኤልም ፈጥና ሁለት መቶ እንጀራ፣ ሁለት አቁማዳ የወይን ጠጅ፣ አምስትም የተዘጋጁ በጎች፣ አምስትም መስፈሪያ ጥብስ እሸት፣ አንድ መቶ ዘለላ ዘቢብ፣ ሁለት መቶም የበለስ ጥፍጥፍ ወሰደች። በአህዮችም ላይ አስጫነች ለብላቴኖቿም አስቀድማችሁ በፊቴ ሂዱ። እነሆም እከተላችኋለሁ አለች። ይህንም ለባሏ ለናባል አልነገረችውም።”—1 ሳሙኤል 25:18, 19
አቢጋኤል ከባሏ ፈቃድ ተቃራኒ የሆነ ነገር በማድረጓ ተሳስታ ነበር? በዚህ ረገድ አልተሳሳተችም ነበር። በተለይም ደግሞ የናባል ጥበብ የጐደለው መንገድ መላውን ቤተሰቧን በአደጋ ላይ ጥሎት ስለነበር አቢጋኤል ለባሏ መገዛትዋ እንደ ባሏ ለዳዊት ፍቅር የጐደለው ምላሽ እንድትሰጥ አይጠይቅባትም ነበር። ስለዚህ ዳዊት “ዛሬ እኔን ለመገናኘት አንቺን የሰደደ የእስራኤል አምላክ ይሖዋ ይመስገን! ወደ ደም እንዳልሄድ በእጄም በቀል እንዳላደርግ ዛሬ የከለከለኝ አእምሮሽ የተመሰገነ ይሁን” ብሏታል። (1 ሳሙኤል 25:32, 33) በተመሳሳይም በዛሬው ጊዜ ክርስቲያን ሚስቶች በባሎቻቸው ራስነት ላይ መነሣሣትና ማመፅ የለባቸውም። ነገር ግን ባሎቻቸው ክርስቲያናዊ ያልሆነ አካሄድ ከመረጡ ሚስቶቻቸው በዚህ ሊተባበሯቸው አይገባም።
እውነት ነው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ” ብሏል። (ኤፌሶን 5:24) ሐዋርያው “በሁሉ” የሚለውን ቃል መጠቀሙ ለሚስት መገዛት ገደብ የለውም ማለት አይደለም። “ቤተ ክርስቲያን (ጉባኤ) ለክርስቶስ እንደምትገዛ” የሚለው ቃል ጳውሎስ በአእምሮው ይዞት የነበረው ምን እንደሆነ ያመለክታል። ክርስቶስ ከጉባኤ የሚፈልግባት ነገር ሁሉ ጻድቅና ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚስማማ ነው። ስለዚህ ጉባኤ በቀላሉና በደስታ በሁሉ ነገር ልትገዛለት ትችላለች። በተመሳሳይም የኢየሱስን ምሳሌ ለመከተል ከልብ የሚጥር ክርስቲያን ባል ያላት ሚስት በሁሉ ልትገዛለት ደስ ይላታል። ለሷ ስለሚሻላት ነገር እንደሚያስብ ታውቃለች። ከአምላክ ፈቃድ ጋር የማይስማማ ነገር እያወቀ እንድታደርግ አይጠይቃትም።
-
-
በጋብቻ ውስጥ መገዛት ማለት ምን ማለት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1991 | ታኅሣሥ 15
-
-
በጉባኤ ውስጥ ባሉ ወንዶችና ሴቶች መካከል ያለው ዝምድና ይህ ከሆነ አንድ ክርስቲያን ባል መንፈሳዊ እኅቱ በሆነችው በሚስቱ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆኑ ምን ምክንያት ሊሰጥ ይችላል? ሚስትስ ራስ ለመሆን ከባሏ ጋር ለመፎካከር ምን ምክንያት ልታቀርብ ትችላለች? ከዚህ ይልቅ እርስ በርሳቸው ሊተያዩ የሚገባቸው ጴጥሮስ የጉባኤውን አባሎች በሙሉ “ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ። የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ” ብሎ እንደመከራቸው ነው። (1 ጴጥሮስ 3:8) ጳውሎስም “ምሕረትን፣ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ የዋህነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ። እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ። ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ” በማለት መክሯል።—ቆላስይስ 3:12, 13
ይህ ዓይነቱ መንፈስ በጉባኤው ውስጥ ሊዳብር ይገባል። በተለይም ደግሞ በክርስቲያን ቤት ውስጥ ባሉ ባልና ሚስት መካከል መዳበር ይኖርበታል። አንድ ባል ርኅራኄውንና የዋህነቱን ከሚስቱ የሚቀርበውን ሐሳብ በማዳመጥ ሊያሳይ ይችላል። ቤተሰቡን የሚነካ ውሳኔ ከማድረጉ በፊት የሚስቱን አስተያየት ከግምት ማስገባት ይኖርበታል። ክርስቲያን ሚስቶች ባዶ ጭንቅላቶች አይደሉም። ሣራ ለባሏ ለአብርሃም እንዳደረገችው ክርስቲያን ሚስቶችም አብዛኛውን ጊዜ ለባሎቻቸው ጠቃሚ ሐሳቦችን ሊሰጡ ይችላሉ። (ዘፍጥረት 21:12) በሌላ በኩል አንዲት ክርስቲያን ሚስት ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ባሏን እኔ ያልኩት ይሁን የምትል አትሆንም። የባሏ ውሳኔዎች አንዳንዴ ከራሷ ምርጫ የሚለዩ ቢሆንም እንኳ አመራሩን በመከተልና ውሳኔዎቹን በመደገፍ ደግነቷንና ትሕትናዋን ልታሳይ ትችላለች።
-