-
በጋብቻ ውስጥ መገዛት ማለት ምን ማለት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1991 | ታኅሣሥ 15
-
-
አምባገነን መሆን የለበትም
ባል ሥልጣኑን እንዴት ሊጠቀምበት ይገባል? የአምላክን ልጅ መልካም ምሳሌ በመከተል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “ክርስቶስ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ራስ እንደሆነ እርሱም አካሉን የሚያድን እንደሆነ ባል የሚስት ራስ ነውና። ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ” ይላል። (ኤፌሶን 5:23, 25) የኢየሱስ ክርስቶስ የራስነት ሥልጣን ለጉባኤው በረከት አስገኝቶ ነበር። አምባገነን አልነበረም። ቁጥጥር በማብዛት እንዲሸማቀቁ ወይም እንዲጨቆኑ አላደረገም። ከዚህ ይልቅ ለሁሉም ባደረገው ፍቅራዊ ርኅራኄ የተሞላበት አያያዙ የሁሉንም አክብሮት አግኝቷል። ይህ ባሎች ለሚስቶች ማድረግ ላለባቸው አያያዝ ግሩም ምሳሌ ነው!
ቢሆንም ይህን ግሩም ምሳሌ የማይከተሉ ባሎች አሉ። ከአምላክ የተሰጣቸውን ራስነት ለሚስቶቻቸው ጥቅም በማዋል ፈንታ በራስ ወዳድነት ይጠቀሙበታል። ፍጹም የሆነ ታዛዥነት በመጠየቅና በራሳቸው ምንም ዓይነት ውሳኔ እንዲያደርጉ ባለመፍቀድ በአምባገነንነት ሚስቶቻቸውን ይጫኗቸዋል። መረዳት እንደሚቻለው እንደዚህ ያሉት ባሎች ሚስቶች የሆኑ ሴቶች አብዛኛውን ጊዜ የሚኖሩት የማያስደስት ሕይወት ነው። እንዲህ ዓይነቱ ባልም የሚስቱን ፍቅራዊ አክብሮት ሳያገኝ ስለሚቀር ችግር ይደርስበታል።
እውነት ነው፣ አንዲት ሚስት ባሏ የቤተሰቡ ራስ በመሆን የያዘውን ቦታ እንድታከብር አምላክ ይፈልግባታል። ነገር ግን ባልየው የሷን ልባዊ አክብሮት እንዲያገኝ ከፈለገ በጥሩ ስብእናው ክብር የሚገባው መሆኑን ማሳየት አለበት። ይህን ለማግኘት ከሁሉ የተሻለው መንገድ ኃላፊነቱን በብቃት በመፈጸምና በቤተሰብ ራስነቱም ጥሩና አምላካዊ ባሕርያትን በመኮትኮት ነው።
መገዛት አንጻራዊ ነው
ባል በሚስቱ ላይ ያለው ሥልጣን ፍጹም አይደለም። በአንዳንድ መንገዶች ሚስቶች በሚስትነታቸው ረገድ የሚያሳዩት መገዛት ክርስቲያኖች ለዓለማዊ ገዥዎች ከሚያሳዩት መገዛት ጋር ሊመሳሰል ይችላል። ክርስቲያን “ለበላይ ባለ ሥልጣኖች መገዛት” እንዳለበት አምላክ ደንግጓል። (ሮሜ 13:1) ሆኖም ይህ መገዛት አምላክ ከሚፈልግብን ነገር ጋር መመዛዘን አለበት። ኢየሱስ “የቄሳርን ለቄሳር የእግዚአብሔርንም ለእግዚአብሔር አስረክቡ” ብሏል። (ማርቆስ 12:17) ቄሳር (ዓለማዊ መንግሥት) ለአምላክ የሚገባውን እንድንሰጠው ከጠየቀ ሐዋርያው ጴጥሮስ “ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባናል” ሲል የተናገረውን እናስታውሳለን።—ሥራ 5:29
-
-
በጋብቻ ውስጥ መገዛት ማለት ምን ማለት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1991 | ታኅሣሥ 15
-
-
እውነት ነው ጳውሎስ ለኤፌሶን ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “ዳሩ ግን ቤተ ክርስቲያን ለክርስቶስ እንደምትገዛ እንዲሁ ሚስቶች ደግሞ በሁሉ ለባሎቻቸው ይገዙ” ብሏል። (ኤፌሶን 5:24) ሐዋርያው “በሁሉ” የሚለውን ቃል መጠቀሙ ለሚስት መገዛት ገደብ የለውም ማለት አይደለም። “ቤተ ክርስቲያን (ጉባኤ) ለክርስቶስ እንደምትገዛ” የሚለው ቃል ጳውሎስ በአእምሮው ይዞት የነበረው ምን እንደሆነ ያመለክታል። ክርስቶስ ከጉባኤ የሚፈልግባት ነገር ሁሉ ጻድቅና ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚስማማ ነው። ስለዚህ ጉባኤ በቀላሉና በደስታ በሁሉ ነገር ልትገዛለት ትችላለች። በተመሳሳይም የኢየሱስን ምሳሌ ለመከተል ከልብ የሚጥር ክርስቲያን ባል ያላት ሚስት በሁሉ ልትገዛለት ደስ ይላታል። ለሷ ስለሚሻላት ነገር እንደሚያስብ ታውቃለች። ከአምላክ ፈቃድ ጋር የማይስማማ ነገር እያወቀ እንድታደርግ አይጠይቃትም።
-
-
በጋብቻ ውስጥ መገዛት ማለት ምን ማለት ነው?መጠበቂያ ግንብ—1991 | ታኅሣሥ 15
-
-
በጉባኤ ውስጥ ባሉ ወንዶችና ሴቶች መካከል ያለው ዝምድና ይህ ከሆነ አንድ ክርስቲያን ባል መንፈሳዊ እኅቱ በሆነችው በሚስቱ ላይ ፈላጭ ቆራጭ ለመሆኑ ምን ምክንያት ሊሰጥ ይችላል? ሚስትስ ራስ ለመሆን ከባሏ ጋር ለመፎካከር ምን ምክንያት ልታቀርብ ትችላለች? ከዚህ ይልቅ እርስ በርሳቸው ሊተያዩ የሚገባቸው ጴጥሮስ የጉባኤውን አባሎች በሙሉ “ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ። የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፤ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ” ብሎ እንደመከራቸው ነው። (1 ጴጥሮስ 3:8) ጳውሎስም “ምሕረትን፣ ርኅራኄን፣ ቸርነትን፣ ትሕትናን፣ የዋህነትን፣ ትዕግሥትን ልበሱ። እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ። ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ” በማለት መክሯል።—ቆላስይስ 3:12, 13
ይህ ዓይነቱ መንፈስ በጉባኤው ውስጥ ሊዳብር ይገባል። በተለይም ደግሞ በክርስቲያን ቤት ውስጥ ባሉ ባልና ሚስት መካከል መዳበር ይኖርበታል። አንድ ባል ርኅራኄውንና የዋህነቱን ከሚስቱ የሚቀርበውን ሐሳብ በማዳመጥ ሊያሳይ ይችላል። ቤተሰቡን የሚነካ ውሳኔ ከማድረጉ በፊት የሚስቱን አስተያየት ከግምት ማስገባት ይኖርበታል። ክርስቲያን ሚስቶች ባዶ ጭንቅላቶች አይደሉም። ሣራ ለባሏ ለአብርሃም እንዳደረገችው ክርስቲያን ሚስቶችም አብዛኛውን ጊዜ ለባሎቻቸው ጠቃሚ ሐሳቦችን ሊሰጡ ይችላሉ። (ዘፍጥረት 21:12) በሌላ በኩል አንዲት ክርስቲያን ሚስት ምክንያታዊ ባልሆነ መንገድ ባሏን እኔ ያልኩት ይሁን የምትል አትሆንም። የባሏ ውሳኔዎች አንዳንዴ ከራሷ ምርጫ የሚለዩ ቢሆንም እንኳ አመራሩን በመከተልና ውሳኔዎቹን በመደገፍ ደግነቷንና ትሕትናዋን ልታሳይ ትችላለች።
-