-
ታዛዥነት—በልጅነት ሊሰጥ የሚገባ አስፈላጊ ትምህርት ነውን?መጠበቂያ ግንብ—2001 | ሚያዝያ 1
-
-
“መልካም እንዲሆንልህ”
ጳውሎስ ታዛዥነት የሚያስገኘውን ሌላ ጥቅም ሲጠቅስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “መልካም እንዲሆንልህ ዕድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም አባትህንና እናትህን አክብር፤ እርስዋም የተስፋ ቃል ያላት ፊተኛይቱ ትእዛዝ ናት።” (ኤፌሶን 6:2, 3፤ ዘጸአት 20:12) አንድ ልጅ ወላጆቹን በመታዘዙ መልካም የሚሆንለት በምን መንገድ ነው?
በመጀመሪያ ደረጃ ወላጆች በዕድሜና በተሞክሮ ብልጫ ያላቸው መሆኑ እውነት አይደለምን? ምንም እንኳ ስለ ኮምፒውተር ወይም በትምህርት ቤት ስለሚሰጡ አንዳንድ ትምህርቶች ሰፊ እውቀት ላይኖራቸው ቢችልም ስለ ኑሮ እና በኑሮ ውስጥ የሚያጋጥሙ ችግሮችን መወጣትን በተመለከተ ከፍተኛ እውቀት አላቸው። በአንጻሩ ደግሞ ወጣቶች ከጉልምስና ጋር የሚመጣው ሚዛናዊ አስተሳሰብ ይጎድላቸዋል። በመሆኑም በችኮላ የመወሰን ዝንባሌ ስለሚኖራቸው አብዛኛውን ጊዜ ለእኩዮች ጎጂ ተጽእኖ በመሸነፍ ራሳቸውን ለጉዳት ይዳርጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ “ስንፍና በሕፃን ልብ ታስሮአል” ብሎ መናገሩ በጣም ትክክል ነው። ታዲያ መፍትሄው ምንድን ነው? “የተግሣጽ በትር ግን ከእርሱ ያርቃታል።”—ምሳሌ 22:15
ታዛዥነት የሚያስገኘው ጥቅም በወላጅና በልጅ መካከል ካለው ዝምድና አልፎ ይሄዳል። የሰው ልጅ ኅብረተሰብ በተቃናና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንዲንቀሳቀስ ትብብር አስፈላጊ ነው። ይህ ደግሞ ታዛዥነትን ይጠይቃል። ለምሳሌ ያህል፣ በትዳር ውስጥ ሰላም፣ ስምምነትና ደስታ እንዲሰፍን የሚያስችለው ለራስ ጥቅም መቆምና ለሌሎች መብትና ስሜት ግድ የለሽ መሆን ሳይሆን ሌላውን ለመጥቀም ፈቃደኛ መሆን ነው። በሥራው ዓለም ሠራተኞች ተገዢ መሆናቸው ለማንኛውም ሥራ ወይም ውጥን ስኬት አስፈላጊ ነገር ነው። መንግሥት በሚያወጣቸው ሕጎችና መመሪያዎች ረገድ ታዛዥነት ማሳየት አንድን ሰው እንዲያው ከቅጣት ማዳን ብቻ ሳይሆን በተወሰነ መጠን ደኅንነትና ጥበቃ ያስገኝለታል።—ሮሜ 13:1-7፤ ኤፌሶን 5:21-25፤ 6:5-8
ለሥልጣን የማይገዙ ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ በኅብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያጣሉ። በአንጻሩ ደግሞ አንድ ሰው በልጅነቱ ታዛዥነትን መማሩ በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ሊጠቅመው ይችላል። ታዛዥነትን በልጅነት መማር ምንኛ ጠቃሚ ነው!
-
-
ታዛዥነት—በልጅነት ሊሰጥ የሚገባ አስፈላጊ ትምህርት ነውን?መጠበቂያ ግንብ—2001 | ሚያዝያ 1
-
-
ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገለጸው ወላጆቻችሁን ታዘዙ የሚለው መመሪያ ድርብ ተፈጻሚነት ያለው ተስፋ ይዟል። ይህም “መልካም እንዲሆንልህ እድሜህም በምድር ላይ እንዲረዝም” እንደሚል አስታውሱ። በምሳሌ 3:1, 2 ላይ ይህን ተስፋ የሚያጠናክር ሐሳብ እናገኛለን:- “ልጄ ሆይ፣ ሕጌን አትርሳ፣ ልብህም ትእዛዛቴን ይጠብቅ። ብዙ ዘመናትና ረጅም ዕድሜ ሰላምም ይጨምሩልሃልና።” ታዛዥ የሆኑ ሰዎች በአሁኑ ጊዜ ከይሖዋ ጋር የግል ዝምድና የሚመሠርቱ ሲሆን ሰላም በሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ ደግሞ የዘላለም ሕይወትን ታላቅ ወሮታ ያገኛሉ።—ራእይ 21:3, 4
-