የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ትኩረት መስጠት
    ንቁ!—2005 | መጋቢት 8
    • ልጆቻችሁን ሳታስቆጡ አሠልጥኗቸው

      የታወቁ አስተማሪና የአእምሮ ሐኪም የሆኑት ዶክተር ሮበርት ኮልስ በአንድ ወቅት “በልጅ ውስጥ በማደግ ላይ ያለ የሥነ ምግባር ስሜት አለ። እኔ እንደሚመስለኝ ይህ የሥነ ምግባር ስሜት አምላክ የሰጣቸው ሲሆን ልጆች ደግሞ የሥነ ምግባር መመሪያ ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው” ሲሉ ተናግረዋል። ታዲያ ይህን የሥነ ምግባር መመሪያ የማግኘት ረሃባቸውንና ጥማታቸውን ማርካት ያለበት ማን ነው?

      መጽሐፍ ቅዱስ በኤፌሶን 6:4 ላይ “አባቶች ሆይ፤ እናንተም ልጆቻችሁን አታስቈጧቸው፤ ነገር ግን በጌታ ምክርና ተግሣጽ አሳድጓቸው” የሚል ማሳሰቢያ ይሰጣል። ይህ ጥቅስ በልጆች ልብ ውስጥ ለአምላክ ፍቅርና ለመለኮታዊ የአቋም ደረጃዎች ጥልቅ አድናቆት የመትከል ዋና ኃላፊነት የሰጠው በተለይ ለአባት መሆኑን አስተውለሃል? በኤፌሶን ምዕራፍ 6 ቁጥር 1 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ልጆች ‘ለወላጆቻቸው መታዘዝ’ እንዳለባቸው ሲናገር ሁለቱንም ማለትም አባትንም እናትንም ጠቅሷል።a

      እርግጥ ነው፣ አባት በማይኖርበት ጊዜ እናት ይህንን ኃላፊነት የመቀበል ግዴታ አለባት። ብዙ ነጠላ እናቶች ልጆቻቸውን በይሖዋ አምላክ ምክርና ተግሣጽ በማሳደግ ረገድ ተሳክቶላቸዋል። ነገር ግን እናትየዋ ክርስቲያን የሆነ ባል ካገባች ግንባር ቀደም መሆን ያለበት እሱ ነው። በዚህ ጊዜ እናት ልጆቻቸውን በመገሠጹና በማሠልጠኑ ረገድ የአባትየውን አመራር በፈቃደኝነት መከተል ይኖርባታል።

      ልጆቻችሁን ‘ሳታስቈጧቸው’ ማሠልጠን ወይም መገሠጽ የምትችሉት እንዴት ነው? እያንዳንዱ ልጅ የተለያየ እንደመሆኑ መጠን ለሁሉም የሚሆን አንድ ደንብ ማውጣት አይቻልም። ያም ሆነ ይህ ወላጆች ተግሣጽ የሚሰጡበትን መንገድ በጥንቃቄ ማሰብና ሁልጊዜ ለልጆቻቸው ፍቅርና አክብሮት ማሳየት ይኖርባቸዋል። የሚያስገርመው ነገር ልጆችን ያለማስቆጣት ጉዳይ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በቆላስይስ 3:21 ላይም በድጋሚ ተገልጿል። እዚያ ላይ “ተስፋ እንዳይቈርጡ ልጆቻችሁን አታስመርሯቸው” ሲል አባቶችን ያሳስባቸዋል።

      አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸው ላይ ይጮኹባቸዋል። ይህ ደግሞ ልጆችን ያበሳጫቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ግን “መራርነትና ንዴት ቊጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ” ሲል አጥብቆ ያሳስባል። (ኤፌሶን 4:31 የ1954 ትርጉም) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ “የጌታም አገልጋይ ሊጣላ አይገባውም፤ ይልቁን ለሰው ሁሉ ገር፣ ለማስተማር ብቃት ያለው፣ ትዕግሥተኛም መሆን ይገባዋል” ይላል።—2 ጢሞቴዎስ 2:24

  • ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ትኩረት መስጠት
    ንቁ!—2005 | መጋቢት 8
    • a እዚህ ላይ ጳውሎስ የተጠቀመበት የግሪክኛ ቃል ጎነፍሲን የሚል ሲሆን ይህም ጎነስ ከተባለው ቃል የመጣ ነው። ትርጉሙም “ወላጅ” ማለት ነው። በቁጥር 4 ላይ ግን “አባቶች” የሚል ትርጉም ያለውን ፓተረስ የተባለ የግሪክኛ ቃል ተጠቅሟል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ