የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማንኛውንም መንፈሳዊ ድካም ማወቅና ማሸነፍ የሚቻልበት መንገድ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሚያዝያ 15
    • የምናደርገው መንፈሳዊ ውጊያ የአንድን ክርስቲያን አእምሮና ልብ ለመማረክ የሚደረግ ጥረት የሚያካትት ፍልሚያ እንደመሆኑ መጠን አእምሯችንንም ሆነ ልባችንን ለመጠበቅ የሚቻለንን ሁሉ ማድረግ አለብን። ከመንፈሳዊ የጦር ትጥቃችን መካከል ልባችንን ለመጠበቅ የሚያገለግለው ‘የጽድቅ ጥሩር’ እና አእምሯችንን የሚጠብቅልን ‘የመዳን ራስ ቁር’ እንደሚገኙ አስ​ታውሱ። ድል ማድረጋችን ወይም አለማድረጋችን የተመካው እነዚህን መንፈሳዊ የጦር ትጥቆች ውጤታማ በሆነ መንገድ መጠቀም በመቻላችን ወይም ባለመቻላችን ላይ ነው።​—⁠ኤፌሶን 6:​14-17፤ ምሳሌ 4:​23፤ ሮሜ 12:​2

  • ማንኛውንም መንፈሳዊ ድካም ማወቅና ማሸነፍ የሚቻልበት መንገድ
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሚያዝያ 15
    • ‘የመዳንን ራስ ቁር’ መልበስ የዚህ ዓለም ብልጭልጭ መስህቦች እንዲያዘናጉን ላለመፍቀድ ከፊታችን ያሉትን ግሩም በረከቶች በአእምሯችን ብሩህ አድርጎ መያዝን ያጠቃልላል። (ዕብራውያን 12:​2, 3፤ 1 ዮሐንስ 2:​16) ይህ ዓይነቱን አመለካከት መያዛችን ከቁሳዊ ንብረት ወይም ከግል ጥቅም ይልቅ መንፈሳዊ ጉዳዮችን እንድናስቀድም ይረዳናል። (ማቴዎስ 6:​33) በመሆኑም ይህን የጦር ትጥቅ በአግባቡ መታጠቃችንን ለማረጋገጥ በሐቀኝነት ለራሳችን የሚከተሉትን ጥያቄዎች ማቅረብ አለብን:- ግብ አድርጌ የያዝኩት ነገር ምንድን ነው? የተወሰኑ መንፈሳዊ ግቦች አሉኝ? እነዚህ ግቦች ላይ ለመድረስ ምን እያደረግሁ ነው? ቅቡዓን ክርስቲያን ቀሪዎችም ሆንን ስፍር ቁጥር የሌላቸው ‘የእጅግ ብዙ ሰዎች’ ክፍል ጳውሎስ “እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፣ . . . ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ” ሲል የተናገረውን ልንኮርጅ ይገባል።​—⁠ራእይ 7:​9፤ ፊልጵስዩስ 3:​13, 14

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ