-
መጽሐፍ ቅዱስን መማርህን እንድትቀጥል ምን ሊረዳህ ይችላል?ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ቅድሚያ ስጥ
አንዳንዴ ጊዜያችን በጣም ከመጣበቡ የተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ለመማር በቂ ጊዜ እንደሌለን ይሰማን ይሆናል። ታዲያ ምን ሊረዳን ይችላል? ፊልጵስዩስ 1:10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
በሕይወታችን ውስጥ ‘ይበልጥ አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች’ አንዳንዶቹ የትኞቹ ይመስሉሃል?
ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ቅድሚያ ለመስጠት ምን ማድረግ ይኖርብሃል?
ሀ. ባልዲው ውስጥ መጀመሪያ ላይ አሸዋ ከጨመርክ በኋላ ድንጋዮቹን ለመጨመር ብትሞክር ለሁሉም ድንጋዮች የሚሆን በቂ ቦታ አታገኝም
ለ. አስቀድመህ ድንጋዮቹን ካስገባህ ግን አብዛኛውን አሸዋ ለማስገባት የሚያስችል ቦታ ታገኛለህ። በተመሳሳይም በሕይወት ውስጥ ‘ይበልጥ አስፈላጊ ለሆኑት ነገሮች’ ቅድሚያ ከሰጠህ ለሌሎች ነገሮችም የሚሆን ጊዜ ታገኛለህ
መጽሐፍ ቅዱስን መማራችን መንፈሳዊ ፍላጎታችንን ማለትም አምላክን የማወቅና እሱን የማምለክ ፍላጎታችንን ለማሟላት ያስችለናል። ማቴዎስ 5:3ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ቅድሚያ መስጠታችን ምን ጥቅም ያስገኝልናል?
-
-
የመዝናኛ ምርጫህ ይሖዋን የሚያስደስት ይሁንለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
-
-
4. ጊዜህን በጥበብ ተጠቀም
ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
በቪዲዮው ላይ የታየው ወንድም መጥፎ ነገር ባይመለከትም ትርፍ ጊዜውን የሚጠቀምበት መንገድ ምን ተጽዕኖ አሳድሮበታል?
ፊልጵስዩስ 1:10ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦
ይህ ጥቅስ በመዝናኛ ምን ያህል ጊዜ ማሳለፍ እንዳለብን ለመወሰን የሚረዳን እንዴት ነው?
-