የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • bsi08-1 ገጽ 28-29
  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 50—ፊልጵስዩስ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 50—ፊልጵስዩስ
  • “ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 16
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት
“ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ” ትክክለኛና ጠቃሚ ናቸው፣ ጥራዝ 16
bsi08-1 ገጽ 28-29

የመጽሐፍ ቅዱስ መጽሐፍ ቁጥር 50​—⁠ፊልጵስዩስ

ጸሐፊው:- ጳውሎስ

የተጻፈበት ቦታ:- ሮም

ተጽፎ ያለቀው:- ከ60–61 ከክ.ል.በኋላ ገደማ

ሐዋርያው ጳውሎስ ምሥራቹን ይዞ ወደ መቄዶንያ እንዲሻገር በራእይ ጥሪ በተደረገለት ጊዜ እሱና ጓደኞቹ ማለትም ሉቃስ፣ ሲላስ እና ወጣቱ ጢሞቴዎስ ፈጣን ምላሽ ሰጥተዋል። በትንሿ እስያ ከምትገኘው ከጢሮአዳ በመርከብ ተሳፍረው ወደ ናጱሌ ከተጓዙ በኋላ 15 ኪሎ ሜትር የሚሆነውን አቀበታማ መንገድ አቋርጠው ወደ ፊልጵስዩስ አቀኑ። ሉቃስ ከተማዋ “የመቄዶንያ ግዛት ዋና ከተማ” እንደሆነች ገልጿል። (ሥራ 16:12) ከተማዋ ፊልጵስዩስ ተብላ የተሰየመችው በ356 ከክርስቶስ ልደት በፊት ከተማዋን በተቆጣጠራት በመቄዶንያው ንጉሥ በፊሊፕ ዳግማዊ (በታላቁ እስክንድር አባት) ስም ነው። ከጊዜ በኋላ ከተማዋ በሮማውያን ቁጥጥር ሥር ሆነች። በ42 ከክርስቶስ ልደት በፊት የኦክታቪያንን (በኋላ ላይ አውግስጦስ ቄሳር ተብሏል) ይዞታ ለማጠናከር የረዱ ወሳኝ ውጊያዎች የተካሄዱት በዚህች ከተማ ነበር። ኦክታቪያን ለድሉ መታሰቢያ እንድትሆን በማለት ፊልጵስዩስን የሮም ቅኝ ግዛት አደረጋት።

2 ጳውሎስ ወደ አንድ አዲስ ከተማ ሲገባ በቅድሚያ ለአይሁዶች የመስበክ ልማድ ነበረው። ይሁን እንጂ በ50 ከክርስቶስ ልደት በኋላ አካባቢ ለመጀመሪያ ጊዜ ፊልጵስዩስ ሲደርስ በዚያ የነበረው የአይሁዶች ቁጥር አነስተኛ የነበረ ከመሆኑም በላይ ምኩራብ ስላልነበራቸው ሳይሆን አይቀርም ለጸሎት ይሰበሰቡ የነበሩት ከከተማው ውጪ በሚገኝ በአንድ ወንዝ ዳርቻ ነበር። የጳውሎስ ስብከት ወዲያውኑ ፍሬ አፈራ። ስለ ክርስቶስ የሚናገረውን እውነት በመቀበል ወደ ክርስትና ለመለወጥ የመጀመሪያ የነበረችው ወደ ይሁዲነት የተለወጠች ልድያ የተባለች ነጋዴ ነበረች። እሷም መንገደኞቹ በቤቷ እንዲቆዩ አጥብቃ ጠየቀቻቸው። ሉቃስ “አጥብቃ ለመነችን” ሲል ጽፏል። ይሁን እንጂ፣ ብዙም ሳይቆይ ጳውሎስና ሲላስ ተቃውሞ አጋጠማቸው። በዱላ ከተደበደቡ በኋላ ታሠሩ። በወኅኒ እያሉ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ። የወኅኒ ቤት ጠባቂውና ቤተሰቡ የጳውሎስንና የሲላስን ስብከት አዳምጠው አማኞች ሆኑ። በሚቀጥለው ቀን ጳውሎስና ሲላስ ከወኅኒ ቤት ተለቀቁ። ከተማውን ለቅቀው ከመሄዳቸው በፊት በልድያ ቤት ተገኝተው ወንድሞችን አበረታቷቸው። ጳውሎስ አዲሱ የፊልጵስዩስ ጉባኤ ሲቋቋም ስለነበሩት አስቸጋሪ ሁኔታዎች የማይረሱ ትዝታዎች አሉት።—ሥራ 16:9-40

3 ከጥቂት ዓመታት በኋላ ጳውሎስ በሦስተኛው የሚስዮናዊ ጉዞው ወቅት የፊልጵስዩስን ጉባኤ በድጋሚ መጎብኘት ችሎ ነበር። ከዚያም ጉባኤው ከተመሠረተ ከአሥር ዓመታት በኋላ የፊልጵስዩስ ወንድሞች ያሳዩት ልብ የሚነካ የፍቅር መግለጫ ጳውሎስ በመንፈስ አነሳሽነት የተጻፈ ደብዳቤ እንዲልክላቸው አነሳስቶታል። በዚያ ተወዳጅ ጉባኤ ስም የተሰየመው ይህ ደብዳቤ የቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል ሆኗል።

4 በመጀመሪያው ቁጥር ላይ እንደተገለጸው ደብዳቤውን የጻፈው ጳውሎስ ነው በሚለው ሐሳብ የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ይስማማሉ። ለዚህም ጥሩ ምክንያት አለ። ፖሊካርፕ (69?-155? ከክርስቶስ ልደት በኋላ) ለፊልጵስዩስ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ ላይ ጳውሎስ ደብዳቤ እንደጻፈላቸው ገልጿል። እንደ ኢግናትየስ፣ ኢረንየስ፣ ተርቱሊያን እና የእስክንድርያው ክሌመንት ያሉት የጥንት የመጽሐፍ ቅዱስ ተንታኞች ደብዳቤው በጳውሎስ የተጻፈ መሆኑን ጠቅሰዋል። በሁለተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ እንደተጻፈ በሚገመት የሙራቶሪ ቁርጥራጭ ላይና በሁሉም ጥንታዊ የቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ ተጠቅሶ የሚገኝ ሲሆን በ200 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ እንደተጻፈ በሚታመነው በቼስተር ቢቲ ፓፒረስ ቁጥር 2 (P46) ላይ ደግሞ ከሌሎች ስምንት የጳውሎስ ደብዳቤዎች ጋር አብሮ ይገኛል።

5 ደብዳቤው የተጻፈበትን ቦታና ጊዜ ማወቅ ይቻላል። ጳውሎስ ደብዳቤውን በጻፈበት ጊዜ በሮሙ ንጉሠ ነገሥት ወታደሮች ቁጥጥር ሥር የሚገኝ እስረኛ ነበር። እንዲሁም በአካባቢው ከፍተኛ የሆነ ክርስቲያናዊ እንቅስቃሴ ይደረግ ነበር። ደብዳቤውን የደመደመው የቄሳር ቤተሰብ ወገን የሆኑት የታመኑ ወንድሞች በላኩት ሰላምታ ነው። እነዚህ እውነታዎች ሁሉ ተሰባስበው ደብዳቤው የተላከው ከሮም መሆኑን ያሳያሉ።—ፊልጵ. 1:7, 13, 14፤ 4:22፤ ሥራ 28:30, 31

6 ይሁን እንጂ ደብዳቤው የተጻፈው መቼ ነው? ጳውሎስ ክርስቲያን በመሆኑ ምክንያት የመታሰሩ ዜና በንጉሠ ነገሥቱ ታማኝ ዘቦችና በሌሎችም ዘንድ በሰፊው ስለ ታወቀ ለረዥም ጊዜ በሮም ሳይቆይ አይቀርም። በተጨማሪም አፍሮዲጡ ከፊልጵስዩስ (ወደ 1,000 ኪሎ ሜትር ከሚጠጋ ርቀት ላይ) ለጳውሎስ ስጦታ ይዞለት እስኪመጣ፣ አፍሮዲጡ በሮም የመታመሙ ዜና ወደ ፊልጵስዩስ እስኪደርስና የፊልጵስዩስ ሰዎች የተሰማቸውን ሐዘን የሚገልጸው መልእክት ከፊልጵስዩስ ወደ ሮም ተመልሶ እስኪመጣ ድረስ ብዙ ጊዜ ያልፋል። (ፊልጵ. 2:25-30፤ 4:18) ጳውሎስ በመጀመሪያ በሮም የታሰረው ከ59-61 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ ስለሆነ ደብዳቤውን የጻፈው ለመጀመሪያ ጊዜ ሮም ከደረሰ ከአንድ ወይም ከሁለት ዓመት በኋላ ማለትም በ60 ወይም በ61 ከክርስቶስ ልደት በኋላ ገደማ መሆን ይኖርበታል።

7 እነዚህን በፊልጵስዩስ የሚገኙ ልጆች በእውነት ቃል ለመውለድ የነበረው ምጥ፣ ጳውሎስ ባደረጋቸው ጉዞዎችና በደረሱበት መከራዎች ሁሉ የፊልጵስዩስ ሰዎች የሚያስፈልገውን ነገር በመላክ ያሳዩት ፍቅር እና ልግስና እንዲሁም ለመጀመሪያ ጊዜ በመቄዶንያ ያደረገውን ሚስዮናዊ እንቅስቃሴ ይሖዋ እንደባረከለት የሚያሳዩት ሁኔታዎች አንድ ላይ ተዳምረው በጳውሎስና በፊልጵስዩስ ወንድሞች መካከል ጠንካራ የፍቅር ትስስር ፈጥረዋል። አሁን ደግሞ በደግነት የላኩለት ስጦታ፣ ስለ አፍሮዲጡ ተጨንቀው መጠየቃቸው እንዲሁም ምሥራቹ በሮም መስፋፋቱ ጳውሎስ ፍቅራዊ ስሜት የተንጸባረቀበትና ገንቢ ማበረታቻ ያዘለ ደብዳቤ እንዲጽፍላቸው አነሳስቶታል።

ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት

12 የፊልጵስዩስ መጽሐፍ ጠቃሚ ትምህርት ይዞልናል! የይሖዋን ሞገስ ብናገኝና ጳውሎስ ለፊልጵስዩስ ሰዎች ከተናገራቸው ጋር ተመሳሳይ የሆኑ የምስጋና ቃላት ከክርስቲያን የበላይ ተመልካቾቻችን ብንሰማ ደስ ይለናል። የፊልጵስዩስ ክርስቲያኖችን መልካም ምሳሌ ብንከተልና የጳውሎስን ፍቅራዊ ምክር በተግባር ብናውል ይህን ለማግኘት እንችላለን። ልክ እንደ ፊልጵስዩስ ሰዎች ለጋስነታችንን ማሳየት፣ ወንድሞቻችን ችግር ላይ በሚወድቁበት ጊዜ መርዳት እንዲሁም ለምሥራቹ ጥብቅና መቆምና የወንጌሉን ሥራ በሕግ በማስከበሩ ተግባር ላይ መካፈል ይገባናል። (1:3-7) በዚህ ጠማማና ክፉ ትውልድ መካከል ‘እንደ ከዋክብት’ በማብራት እንዲሁም ‘ለወንጌል እምነት እንደ አንድ ሰው ሆነን በመጋደል በአንድ መንፈስ ጸንተን መቆም’ አለብን። እነዚህን ነገሮች ካደረግንና በቁም ነገር ሊታዩ የሚገባቸውን ነገሮች ቅድሚያ ሰጥተን የምናስብባቸው ከሆነ የፊልጵስዩስ ሰዎች ለጳውሎስ የደስታ አክሊል እንደሆኑ ሁሉ እኛም ለወንድሞቻችን የደስታ ምንጭ እንሆንላቸዋለን።—1:27፤ 2:15፤ 4:1, 8

13 ጳውሎስ ‘የእኔን አርአያ ተከተሉ’ ብሏል። የእሱን አርአያ የምንከተለው በምን መንገድ ነው? አንዱ መንገድ በማንኛውም ሁኔታ ሥር ራሳችንን ችለን በመኖር ነው። ጳውሎስ ቢያገኝም ቢያጣም በአምላክ አገልግሎት በደስታና በቅንዓት ለመቀጠል ሲል ሳያጉረመርም ከሁኔታዎች ጋር ራሱን ማላመድን ተምሯል። ሁላችንም ልክ እንደ ጳውሎስ ለታመኑ ወንድሞቻችን ጥልቅ ፍቅር ማሳየት ይገባናል። ጳውሎስ የጢሞቴዎስንና የአፍሮዲጡን አገልግሎት አስመልክቶ ሲናገር ከፍቅር በመነጨ ደስታ ተሞልቶ ነበር! እንዲሁም ጳውሎስ “የምወዳችሁና የምናፍቃችሁ፣ ወንድሞቼ ደስታዬና አክሊሌ የሆናችሁ” ብሎ የጠራቸው በፊልጵስዩስ ይኖሩ የነበሩት ወንድሞቹ የቅርብ ወዳጆቹ እንደሆኑ ይሰማው ነበር!—3:17፤ 4:1, 11, 12፤ 2:19-30

14 ጳውሎስን መምሰል የምንችልበት ሌላው መንገድ ምንድን ነው? በፊታችን ወዳለው ‘ግብ በመፍጠን’ ነው! ‘ክቡር ለሆኑ’ ነገሮች ትኩረት የሚሰጡ ሰዎች ‘ምላስ ሁሉ ለእግዚአብሔር አብ ክብር ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ እንደሆነ በሚመሰክርበት’ በሰማይና በምድር ይሖዋ ስላደረገው አስደናቂ ዝግጅት ይበልጥ ለማወቅ ይጓጓሉ። በፊልጵስዩስ መልእክት ውስጥ የሚገኘው ግሩም ምክር በአምላክ መንግሥት ለዘላለም ለመኖር ተስፋ የሚያደርጉ ሁሉ ይህን ግብ መከታተላቸውን እንዲቀጥሉ ያበረታታቸዋል። ይሁን እንጂ ለፊልጵስዩስ ሰዎች የተላከው ደብዳቤ በተለይ የተጻፈው ‘አገራቸው በሰማይ’ ለሆኑትና ‘የክርስቶስን ክቡር አካል እንዲመስል የተዋረደው ሥጋቸው የሚለወጥበትን’ ጊዜ በጉጉት ለሚጠባበቁት ነው። እነዚህ ሰዎች ‘በአምላክ የመጠራትን ሽልማት’ ማለትም በሰማያዊ መንግሥት ያላቸውን ክብራማ ውርሻ እንዲያገኙ ‘ከኋላቸው ያለውን እየረሱ በፊታቸው ያለውን’ ለመያዝ በመጣር ሐዋርያው ጳውሎስን ይመስሉት ዘንድ እንመኛለን!—4:8፤ 2:10, 11፤ 3:13, 14, 20, 21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ