የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የሃይማኖት ምሁራንን ግራ ያጋባ ጉዳይ
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | መጋቢት 1
    • ካቴኪዝም ኦቭ ዘ ካቶሊክ ቸርች የተባለው ጽሑፍ እንዲህ ይላል፦ “ከክርስቶስ ጋር ለመነሣት ከክርስቶስ ጋር መሞት አለብን፤ ማለትም ‘ከሥጋ መለየትና ከጌታ ጋር መሆን አለብን።’ [2 ቆሮንቶስ 5:8] በዚህ ‘መለየት’ ማለትም ሞት ነፍስ ከሥጋ ትለያለች። [ፊልጵስዩስ 1:23] በሙታን ትንሣኤ ወቅት ነፍስ ከሥጋ ጋር እንደገና ትዋሃዳለች።” ይሁን እንጂ እዚህ ላይ በተጠቀሱት ጥቅሶች ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ነፍስ ሥጋ ሲሞት ሳትሞት ከሥጋ ጋር ለመዋሃድ “የመጨረሻውን ፍርድ” ትጠባበቃለች ብሏልን?

  • የሃይማኖት ምሁራንን ግራ ያጋባ ጉዳይ
    መጠበቂያ ግንብ—1995 | መጋቢት 1
    • ጳውሎስ በፊልጵስዩስ 1:21, 23 ላይ እንደ 1980 ትርጉም “ለእኔ ሕይወት ማለት፣ በክርስቶስ መኖር ነው፤ ሞትም ማለት፣ ጥቅም የሚገኝበት ነገር ነው። በእነዚህ በሁለቱ አሳቦች መካከል ተይዣለሁ፤ በአንድ በኩል ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆን እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም ከክርስቶስ ጋር መሆን ከሁሉ የሚበልጥ ነገር ስለሆነ ነው” ብሏል። ጳውሎስ እዚህ ላይ የጠቀሰው ‘በሞትና በትንሣኤ መካከል ያለውን ሁኔታ’ ነውን? አንዳንዶች እንደዚያ ይሰማቸዋል። ይሁን እንጂ ጳውሎስ የተናገረው ሁለት ነገሮች ሊያጋጥሙት ማለትም ሊኖር ወይም ሊሞት እንደሚችል ነው። “በአንድ በኩል ከዚህ ሕይወት ተለይቼ ከክርስቶስ ጋር መሆን እፈልጋለሁ” ሲል በማከል ሦስተኛውን አማራጭ ጠቀሰ። ወዲያውኑ ‘ከዚህ ሕይወት እንደ ተለየ’ ከክርስቶስ ጋር ይሆናል ማለት ነው? ጳውሎስ ታማኝ የሆኑ ቅቡዕ ክርስቲያኖች በክርስቶስ መገኘት ወቅት እንደሚነሡ እንደሚያምን ከዚህ በፊት አይተናል። ስለዚህ በዚያን ወቅት የሚፈጸሙ ነገሮችን መናገሩ መሆን አለበት።

      ይህንንም በፊልጵስዩስ 3:20, 21 እና በ1 ተሰሎንቄ 4:16 ላይ ከሚገኙት ከራሱ ቃላት ማየት ይቻላል። በክርስቶስ መገኘት ወቅት የሚፈጸመው ይህ “ከዚህ ሕይወት መለየት” ጳውሎስ አምላክ ያዘጋጀለትን ሽልማት እንዲቀበል ያስችለዋል። ይህን ተስፋ እንደሚያደርግ ለወጣቱ ጢሞቴዎስ ከጻፈለት ከሚከተሉት ቃላት መረዳት ይቻላል፦ “ወደ ፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፣ ይህንም ጻድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፣ ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም።”—2 ጢሞቴዎስ 4:8

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ