-
‘በኋላችሁ ያሉትን ነገሮች’ አትመልከቱመጠበቂያ ግንብ—2012 | መጋቢት 15
-
-
12. ጳውሎስ ወደኋላ ስለተዋቸው ነገሮች ምን ተሰምቶት ነበር?
12 ሐዋርያው ጳውሎስ የኢየሱስ ተከታይ ለመሆን ሲል ብዙ ነገሮችን ትቷል። (ፊልጵ. 3:4-6) ታዲያ ወደኋላው ስለተዋቸው ነገሮች ምን ተሰምቶት ነበር? “ለእኔ ትርፍ የነበረውን ነገር ሁሉ ለክርስቶስ ስል እንደ ኪሳራ ቆጥሬዋለሁ” ብሏል። እንደዚህ የተሰማው ለምንድን ነው? ቀጥሎ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “ስለ ጌታዬ ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ ከሚገልጸው የላቀ ዋጋ ያለው እውቀት የተነሳ ሁሉንም ነገር እንደ ኪሳራ እቆጥረዋለሁ። ለእሱ ስል ሁሉንም ነገር አጥቻለሁ፤ ያጣሁትንም ነገር ሁሉ እንደ ጉድፍ እቆጥረዋለሁ፤ ይህም ክርስቶስን አገኝ ዘንድ [ነው]።”a (ፊልጵ. 3:7, 8) አንድ ሰው ቆሻሻ ወይም ጥራጊ ከደፋ በኋላ ባልጣልኩት ብሎ እንደማያዝን ሁሉ ጳውሎስም በዓለም ውስጥ ሊያገኛቸው የሚችላቸውን አጋጣሚዎች ወደኋላ በመተዉ በፍጹም አልተጸጸተም። እነዚህን አጋጣሚዎች አንዴ ከተዋቸው በኋላ፣ ዋጋ እንዳላቸው በመቁጠር እነሱን ፍለጋ አልተመለሰም።
13, 14. የጳውሎስን ምሳሌ መከተል የምንችለው እንዴት ነው?
13 እንዳመለጡን አድርገን ስለምናስባቸው አጋጣሚዎች ማውጠንጠን ጀምረን ከሆነ ምን ሊረዳን ይችላል? የጳውሎስን ምሳሌ መከተል ይኖርብናል። እንዴት? አሁን ያሉህ ነገሮች ምን ያህል ዋጋ እንዳላቸው አስብ። ከይሖዋ ጋር ውድ የሆነ ዝምድና መሥርተሃል፤ እንዲሁም ታማኝ በመሆን ረገድ በእሱ ዘንድ ጥሩ ስም አትርፈሃል። (ዕብ. 6:10) ይህ ዓለም፣ አሁንም ሆነ ወደፊት ከምናገኛቸው መንፈሳዊ በረከቶች ጋር ሊወዳደር ቀርቶ ጫፉ ጋ እንኳ ሊደርስ የሚችል ምን ቁሳዊ ነገር ሊሰጠን ይችላል?—ማርቆስ 10:28-30ን አንብብ።
-
-
‘በኋላችሁ ያሉትን ነገሮች’ አትመልከቱመጠበቂያ ግንብ—2012 | መጋቢት 15
-
-
a “ጉድፍ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል “ለውሾች የሚሰጥ” ነገር፣ “አዛባ” እና “ዓይነ ምድር” የሚል ትርጉምም አለው። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁር እንደተናገሩት ጳውሎስ ይህን ቃል የተጠቀመበት “ከማይረባ እንዲሁም ከሚያጸይፍ ነገር መሸሽን እንዲሁም ወደዚያ ነገር ድርሽ አለማለትን” ለማመልከት ነው።
-