የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 3. አንድ ሰው ለጥምቀት ብቁ እንዲሆን ምን ማድረግ ይኖርበታል?

      ከመጠመቅህ በፊት ስለ ይሖዋ መማርና በእሱ ላይ ጠንካራ እምነት መገንባት ይኖርብሃል። (ዕብራውያን 11:6⁠ን አንብብ።) እውቀትህና እምነትህ እያደገ ሲሄድ ለይሖዋ ያለህ ፍቅርም ይጨምራል። ይህ ደግሞ ስለ እሱ ለመስበክና እሱ ባወጣቸው መሥፈርቶች ለመመራት እንድትነሳሳ ያደርግሃል። (2 ጢሞቴዎስ 4:2፤ 1 ዮሐንስ 5:3) አንድ ሰው ‘ለይሖዋ በሚገባ ሁኔታ መመላለስና እሱን ሙሉ በሙሉ ማስደሰት’ ሲችል ሕይወቱን ለአምላክ ለመስጠትና ለመጠመቅ መወሰኑ አይቀርም።—ቆላስይስ 1:9, 10a

  • ጥምቀት—ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ግብ!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • a አንድ ሰው ከዚህ በፊት በሌላ ሃይማኖት ውስጥ ተጠምቆ የነበረ ቢሆንም እንኳ እንደገና መጠመቅ ያስፈልገዋል። ለምን? ምክንያቱም ቀደም ሲል የተጠመቀበት ሃይማኖት የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት አያስተምርም።—የሐዋርያት ሥራ 19:1-5⁠ን እና ምዕራፍ 13⁠ን ተመልከት።

  • ለመጠመቅ ዝግጁ ነህ?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 1. ከመጠመቅህ በፊት ምን ያህል እውቀት ሊኖርህ ይገባል?

      ለመጠመቅ “የእውነትን ትክክለኛ እውቀት” ማግኘት ያስፈልግሃል። (1 ጢሞቴዎስ 2:4) እንዲህ ሲባል ግን ከመጠመቅህ በፊት፣ ሰዎች ለሚያነሷቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች በሙሉ ምን መልስ መስጠት እንዳለብህ ልታውቅ ይገባል ማለት አይደለም። ከተጠመቁ ብዙ ዓመት የሆናቸው ክርስቲያኖችም እንኳ መማራቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋል። (ቆላስይስ 1:9, 10) ይሁንና መሠረታዊ የሆኑትን የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች ማወቅህ አስፈላጊ ነው። የጉባኤ ሽማግሌዎች በቂ እውቀት ይኖርህ እንደሆነና እንዳልሆነ ማወቅ እንድትችል ይረዱሃል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ