-
‘ስጦታ የሆኑ ወንዶችን’ ማድነቅመጠበቂያ ግንብ—1999 | ሰኔ 1
-
-
“ከመጠን ይልቅ አክብሯቸው”
14, 15. (ሀ) በ1 ተሰሎንቄ 5:12, 13 መሠረት ለሽማግሌዎች አሳቢነት ልናሳያቸው የሚገባን ለምንድን ነው? (ለ) ሽማግሌዎች ‘በመካከላችን ይደክማሉ’ ሊባል የሚችለው ለምንድን ነው?
14 ‘ስጦታ ለሆኑ ወንዶች’ አሳቢ በመሆን ለእነርሱ ያለንን አድናቆት ልናሳይ እንችላለን። ጳውሎስ በተሰሎንቄ ለሚገኘው ጉባኤ ሲጽፍ የጉባኤውን አባላት እንዲህ በማለት መክሯል:- “በመካከላችሁ የሚደክሙትን በጌታም የሚገዙአችሁን የሚገሥጹአችሁንም . . . በፍቅር ከመጠን ይልቅ [አክብሯቸው።]” (1 ተሰሎንቄ 5:12, 13) “የሚደክሙትን” የሚለው አገላለጽ ራሳቸውን ምንም ሳይቆጥቡ ለእኛ የሰጡትን ሽማግሌዎች ጥሩ አድርጎ የሚገልጽ አይደለምን? እነዚህ የተወደዱ ወንድሞች የተሸከሙትን ከባድ ሸክም እስቲ ለአንድ አፍታ እንመልከት።
-
-
‘ስጦታ የሆኑ ወንዶችን’ ማድነቅመጠበቂያ ግንብ—1999 | ሰኔ 1
-
-
16. ለሽማግሌዎች ያለንን አሳቢነት ልናሳይ የምንችልባቸውን መንገዶች ግለጽ።
16 አሳቢነታችንን ልናሳይ የምንችለው እንዴት ነው? አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ “ቃልም በጊዜው ምንኛ መልካም ነው!” በማለት ይናገራል። (ምሳሌ 15:23፤ 25:11) ከልብ በመነጨ ስሜት የምንገልጽላቸው የአድናቆትና የማበረታቻ ቃላት የሚያከናውኑትን ትጋት የተሞላበት ሥራ እንዲሁ በቀላሉ እንደማንመለከተው ሊያሳይ ይችላል። በተጨማሪም ከእነርሱ በምንጠብቀው ነገር ረገድ ምክንያታዊ መሆን ይገባል። እርግጥ ከእነርሱ እርዳታ ለማግኘት ያለ ምንም ፍርሃት በነፃነት ልንቀርባቸው ይገባናል። ‘ልባችን የሚናወጥበትና’ የአምላክን ቃል ‘በማስተማር በኩል ብቃቱ ካላቸው’ ወንድሞች ቅዱስ ጽሑፋዊ ማበረታቻ፣ መመሪያ ወይም ምክር ማግኘት የሚያስፈልገን ወቅት ሊኖር ይችላል። (መዝሙር 55:4፤ 1 ጢሞቴዎስ 3:2) በአንጻሩ ደግሞ አንድ ሽማግሌ ቤተሰቡም ሆነ ጉባኤው የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች ችላ ብሎ ማለፍ ስለማይችል ለእኛ ሊኖረው የሚችለው ጊዜ በጣም ውስን እንደሆነ ማስታወስ ይኖርብናል። ብዙ ለሚደክሙት ለእነዚህ ወንድሞች ያዳበርነው ‘የወንድማማች ፍቅር’ ከመጠን በላይ እንዳንጠብቅባቸው ያደርገናል። (1 ጴጥሮስ 3:8) ከዚያ ይልቅ ምክንያታዊ ሆነው የሚሰጡን ጊዜም ሆነ ትኩረት ምንም ያክል ይሁን ምን አድናቂዎች እንሁን።—ፊልጵስዩስ 4:5
17, 18. ሽማግሌ ባል ያላቸው ሚስቶች ምን ዓይነት መሥዋዕቶችን ይከፍላሉ? እነዚህ ታማኝ እህቶች የሚከፍሉትን መሥዋዕት አንደቀላል እንደማንቆጥረው እንዴት ልናሳይ እንችላለን?
17 ስለ ሽማግሌ ሚስቶችስ ምን ለማለት ይቻላል? ለእነርሱስ ቢሆን አሳቢነት ልናሳያቸው አያስፈልግምን? ጉባኤው ባሎቻቸውን ይጋራባቸዋል። ይህም የራሳቸውን ጥቅም መሥዋዕት እንዲያደርጉ ይጠይቅባቸዋል። አልፎ አልፎ ሽማግሌዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር ሊያሳልፉት የሚችሉትን ምሽት ለጉባኤ ጉዳዮች እንዲያውሉ የሚገደዱበት ጊዜ አለ። በብዙ ጉባኤዎች የሚገኙ የታመኑ ክርስቲያን ሴቶች እንዲህ ያለውን መሥዋዕት ለመክፈል ፈቃደኞች በመሆናቸው ምክንያት ባሎቻቸው የይሖዋን በጎች እንዲንከባከቡ አስችሏቸዋል።—ከ2 ቆሮንቶስ 12:15 ጋር አወዳድር።
18 እነዚህ ታማኝ ክርስቲያን እህቶች የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ እንደ ቀላል እንደማንመለከተው እንዴት ልናሳይ እንችላለን? በትንሹም በትልቁም ባሎቻቸውን ባለማስቸገር እንደሚሆን ግልጽ ነው። ጥቂት የአድናቆት ቃላት መሰንዘሩም ያለውን ኃይል አቅልለን መመልከት አይኖርብንም። ምሳሌ 16:24 እንዲህ ይላል:- “ያማረ ቃል የማር ወለላ ነው፤ ለነፍስ ጣፋጭ ለአጥንትም ጤና ነው።” አንድ ምሳሌ ተመልከቱ። ከአንድ ክርስቲያናዊ ስብሰባ በኋላ አንድ ባልና ሚስት ወደ አንድ ሽማግሌ ቀርበው በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ ስለሚገኝ ልጃቸው ሊያነጋግሩት እንደሚፈልጉ ይነግሩታል። ሽማግሌው ከባልና ሚስቱ ጋር እየተነጋገረ ሳለ ባለቤቱ ፈንጠር ብላ ትጠብቀው ነበር። ውይይቱ እንዳበቃ እናትየው ወደ ሽማግሌው ሚስት ቀርባ “ባለቤትሽ ቤተሰቤን ለመርዳት ሲል ለወሰደው ሰዓት ላመሰግንሽ እፈልጋለሁ” አለቻት። እነዚህ ቀላልና አስደሳች የአድናቆት ቃላት የሽማግሌውን ሚስት ልብ በእጅጉ ነክተዋል።
-