የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን መማርና ማስተማር
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • 13. (ሀ) መጽሐፍ ቅዱስ ሥነ ምግባርን በሚመለከት የሚረዳን እንዴት ነው? (ለ) በ1 ተሰሎንቄ 4:​3-7 ላይ የሚገኘው ምክር ፍሬ ነገር ምንድን ነው?

      13 ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን መጠበቅ ወይም አለመጠበቅ ሌሎች ሰዎችንም ይነካል። ይህንን ለመረዳት እርሱ ያወጣውን የሥነ ምግባር መሥፈርት ተግባራዊ ማድረግ የሚያስገኘውን ጥቅምና ችላ ማለት የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ ከአምላክ ቃል ውስጥ አንዳንድ ምሳሌዎችን መመልከት ትችላለህ። (ዘፍጥረት 39:​1-9, 21፤ ኢያሱ 7:​1-25) እንዲሁም ሥነ ምግባርን አስመልክቶ የሚከተለውን ግልጽ ምክር ታገኛለህ:- “ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፣ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፣ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ . . . ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል [“የወንድሙን መብት አይጋፋ፣” NW ]። ለርኩሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።”​​—⁠⁠1 ተሰሎንቄ 4:​3-7

      14. በአንደኛ ተሰሎንቄ 4:​3-7 ላይ የሚገኘውን ምክር በሚመለከት ራስህን ምን ብለህ መጠየቅ ትችላለህ?

      14 ይህን ጥቅስ ያነበበ ማንኛውም ሰው የጾታ ብልግና መፈጸም ክርስቲያናዊውን የሥነ ምግባር ሕግ እንደሚያስጥስ በቀላሉ መገንዘብ ይችላል። ሆኖም ጥቅሱን ይበልጥ ሰፋ አድርገህ መገንዘብ ትችላለህ። አንዳንዶቹ ቁጥሮች ተጨማሪ ምርምር ለማድረግና ይበልጥ ለማሰላሰል ስለሚያስችሉ ጥልቅ ማስተዋል ያስገኛሉ። ለምሳሌ ያህል እንዲህ እያልክ መጠየቅ ትችላለህ:- ጳውሎስ አንድ ሰው ዝሙት መፈጸሙ ‘ወንድሙን ማታለሉና የወንድሙንም መብት መጋፋቱ’ እንደሆነ ሲናገር ምን ማለቱ ነው? እዚህ ላይ የተጠቀሰው መብት ምን ነገሮችን ያጠቃልላል? ይህን ጉዳይ በሚገባ መረዳትህ ክርስቲያናዊ የሥነ ምግባር አቋምህን ጠብቀህ እንድትኖር ተጨማሪ ጥንካሬ የሚሰጥህ እንዴት ነው? እንዲህ ያለ ምርምር ማድረግህ ሌሎችን ለማስተማር የተሻለ ብቃት እንዲኖርህና አምላክን እንዲያከብሩ እንድትረዳቸው የሚያስችልህ እንዴት ነው?

  • ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን መማርና ማስተማር
    መጠበቂያ ግንብ—2002 | ሰኔ 15
    • 16, 17. (ሀ) በ1 ተሰሎንቄ 4:​6 ላይ የተጠቀሰውን መብት በሚመለከት ተጨማሪ እውቀት ማግኘት የምትችለው ከየት ነው? (ለ) ዝሙት የሚፈጽም ሰው የሌሎችን መብት የሚጋፋው እንዴት ነው?

      16 እስቲ ከላይ የተጠቀሰውን የ1 ተሰሎንቄ 4:​3-7 ጥቅስ እንደ ምሳሌ እንውሰድ። መብትን በተመለከተ ጥያቄ ተነስቷል። ስለ ማን መብት? ይህ መብት ሊጣስ የሚችለው እንዴት ነው? ከላይ በተጠቀሱት የማጥኛ መሣሪያዎች አማካኝነት በእነዚህ ቁጥሮች ሌላው ቀርቶ ጳውሎስ በጠቀሰው የመብት ጉዳይ ላይ እውቀት የሚጨምሩ በርካታ ማብራሪያዎችን ማግኘት ትችላለህ። እነዚህን ማብራሪያዎች ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ጥራዝ 1፣ ገጽ 863-4፤ እውነተኛ ሰላምና ደኅንነት​​—⁠⁠እንዴት ማግኘት ትችላለህ? ገጽ 145 እና ከኅዳር 15, 1989 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 31 ላይ ማንበብ ትችላለህ። (በእንግሊዝኛ የሚገኙ ናቸው።)

      17 ጥናትህን ስትቀጥል ጳውሎስ የተናገራቸው ቃላት ምን ያህል ትክክል መሆናቸውን ከእነዚያ ጽሑፎች ትገነዘባለህ። ዝሙት የሚፈጽም ሰው በአምላክ ላይ ኃጢአት ከመሥራቱም በላይ ራሱን ለበሽታ ያጋልጣል። (1 ቆሮንቶስ 6:​18, 19፤ ዕብራውያን 13:​4) አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋር ዝሙት ሲፈጽም የተለያዩ መብቶችን እንደሚያሳጣት መገንዘብ አለበት። ንጹሕ የሥነ ምግባር አቋምና በጎ ሕሊና እንድታጣ ያደርጋታል። ያላገባች ከሆነ ክብረ ንጽሕናዋን ጠብቃ ትዳር ለመመሥረት ያላትን መብት የሚያሳጣት ከመሆኑም በላይ ወደፊት ባልዋ የሚሆነው ሰው ንጽሕናዋን እንደጠበቀች የማግኘት መብቱንም ይጋፋዋል። ባለ ትዳር ከሆነች ደግሞ የሴትዮዋን ወላጆችና የባለቤትዋን ስሜት ይጎዳል። የጾታ ብልግና የፈጸመው ሰው የቤተሰቡን መልካም ስም ያጎድፋል። የክርስቲያን ጉባኤ አባል ከሆነ ደግሞ የጉባኤውን ስም በማጥፋት ነቀፋ ያስከትልበታል።​​—⁠⁠1 ቆሮንቶስ 5:​1

      18. ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን በሚመለከት ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

      18 መብትን አስመልክቶ የተሰጡት እነዚህ ማብራሪያዎች ስለ 1 ተሰሎንቄ 4:​3-7 ያለህን ማስተዋል ይበልጥ አላሰፋልህም? እንዲህ ያለው ጥናት ከፍተኛ ጥቅም እንደሚያስገኝ ምንም ጥርጥር የለውም። በጥናቱ በገፋህ መጠን ራስህን እያስተማርህ ትሄዳለህ። የአምላክ ቃል እውነት እንደሆነና ኃይል እንዳለው ያለህ ግንዛቤ ያድጋል። ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥምህ ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባርን ለመጠበቅ ያደረግኸውን ቁርጥ ውሳኔ ያጠናክርልሃል። እንዲሁም በአስተማሪነትህ ምን ያህል ውጤታማ ልትሆን እንደምትችል አስብ! ለምሳሌ ያህል መጽሐፍ ቅዱስ የያዘውን እውነት ለሌሎች በምታስተምርበት ጊዜ 1 ተሰሎንቄ 4:​3-7ን በደንብ ልታብራራላቸውና ለክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ያላቸው ማስተዋልና አድናቆት እንዲጨምር ልትረዳቸው ትችላለህ። ስለሆነም የምታደርገው ጥናት አንተም ሆንክ ሌሎች ሰዎች አምላክን እንድታከብሩ ሊረዳችሁ ይችላል። ጳውሎስ ለተሰሎንቄ ክርስቲያኖች ከጻፈው ደብዳቤ ላይ እዚህ ላይ የጠቀስነው አንድ ምሳሌ ብቻ ነው። ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ሌሎች ብዙ ገጽታዎችም አሉት። ምርምር ልታደርግባቸው፣ በሥራ ልታውላቸውና ለሌሎች ልታስተምራቸው የምትችላቸው ከዚህ ጋር ተዛማጅነት ያላቸው ሌሎች ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌዎችና ምክሮች አሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ