-
ማዘን ስህተት ነውን?ንቁ!—2001 | መስከረም 8
-
-
“ነገር ግን፣ ወንድሞች ሆይ፣ ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች ደግሞ እንዳታዝኑ፣ አንቀላፍተው ስላሉቱ ታውቁ ዘንድ እንወዳለን።”—1 ተሰሎንቄ 4:13
መጽሐፍ ቅዱስ የሞቱ ሰዎች ስላላቸው ተስፋ ይናገራል። ኢየሱስ ያከናወናቸው ትንሣኤዎችም ሆኑ የሰጣቸው ትምህርቶች የሞቱ ሰዎች ወደ ሕይወት ስለሚመለሱበት ጊዜ ይጠቁማሉ። (ማቴዎስ 22:23-33፤ ማርቆስ 5:35, 36, 41, 42፤ ሉቃስ 7:12-16) ታዲያ ይህ ተስፋ እኛን ሊነካን የሚገባው እንዴት ነው? ከላይ የተጠቀሱት የሐዋርያው ጳውሎስ ቃላት እንደሚያሳዩት አንድ የምትወደው ሰው ሲሞት ይህ ተስፋ ሊያጽናናህ ይችላል።
የምትወደውን ሰው በሞት አጥተህ ከሆነ እንዲህ ያለው አሳዛኝ ሁኔታ የሚያስከትለውን የስሜት ስቃይ እንደቀመስክ ምንም አያጠራጥርም። ቴሬዛ ለ42 ዓመታት አብራው የኖረችው ባሏ የልብ ቀዶ ሕክምና ከተደረገለት በኋላ ብዙም ሳይቆይ ሲሞት እንዲህ ብላለች:- “በጣም አስደንጋጭ ነበር! በመጀመሪያ ከፍተኛ ድንጋጤ ተሰማኝ። ይህንን ተከትሎም እየተባባሰ የሚሄድ ኃይለኛ ሕመም ይሰማኝ ጀመር። ብዙ አለቀስኩ።” እንዲህ ዓይነቱ ምላሽ ይሖዋ ሙታንን ለማስነሳት በገባው ቃል ላይ እምነት ማጣትን ያመለክታል? የጳውሎስ ቃላት ማዘን ስህተት ነው የሚል መልእክት ያስተላልፋሉን?
ማዘናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸ ምሳሌዎች
ማዘናቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጹትን ምሳሌዎች ስንመረምር ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ እናገኛለን። በብዙ ታሪኮች ላይ እንደተገለጸው አንድ ቅርብ የቤተሰብ አባል ሲሞት ቤተሰቡ ለተወሰነ ጊዜ ያዝናል። (ዘፍጥረት 27:41፤ 50:7-10፤ መዝሙር 35:14) ብዙውን ጊዜም ከኃዘኑ ጋር ተያይዘው የሚመጡት ስሜቶች በጣም ጥልቅ ናቸው።
-
-
ማዘን ስህተት ነውን?ንቁ!—2001 | መስከረም 8
-
-
እንደ ማንኛውም ክርስቲያን የምንወደው ሰው ሲሞት ማዘናችን ባይቀርም “ተስፋ እንደሌላቸው እንደ ሌሎች” አናዝንም። (1 ተሰሎንቄ 4:13) ሙታን ስለሚገኙበት ሁኔታ ያለን አመለካከት ጥርት ያለ በመሆኑ ኃዘናችንን ስንገልጽ ከልክ ወዳለፈ ጽንፍ አንሄድም። ሙታን በስቃይ ወይም በጭንቀት ላይ እንዳልሆኑ ይልቁንም ድብን ያለ እንቅልፍ የወሰዳቸው ያህል በሰላም እንዳንቀላፉ እናውቃለን። (መክብብ 9:5፤ ማርቆስ 5:39፤ ዮሐንስ 11:11-14) በተጨማሪም “ትንሣኤና ሕይወት” የሆነው ኢየሱስ ‘በመቃብር ያሉትን ሙታን’ ለማስነሳት የገባውን ቃል እንደሚፈጽም እርግጠኞች ነን።—ዮሐንስ 5:28, 29፤ 11:24, 25
-