የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ‘መዳናችሁ እየቀረበ ነው’!
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | ሐምሌ 15
    • 14, 15. የማጎጉ ጎግ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረ በኋላ የትኛው የመሰብሰብ ሥራ ይከናወናል? ይህ የመሰብሰብ ሥራስ ምን ያካትታል?

      14 የማጎጉ ጎግ በአምላክ ሕዝቦች ላይ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረ በኋላ ምን ይከናወናል? የማቴዎስና የማርቆስ ዘገባዎች ተመሳሳይ ሐሳብ ይዘዋል፦ “[የሰው ልጅ] መላእክቱን ልኮ ከአራቱ ነፋሳት፣ ከምድር ዳርቻ እስከ ሰማይ ዳርቻ ለእሱ የተመረጡትን ይሰበስባል።” (ማር. 13:27፤ ማቴ. 24:31) እዚህ ላይ የተገለጸው መሰብሰብ፣ ቅቡዓኑ መቀባት የጀመሩበትን ጊዜም ሆነ በምድር የቀሩት ታማኝ ቅቡዓን የመጨረሻው ማኅተም የሚደረግባቸውን ጊዜ አያመለክትም። (ማቴ. 13:37, 38) ይህ ማኅተም የሚደረግባቸው ታላቁ መከራ ከመጀመሩ በፊት ነው። (ራእይ 7:1-4) ታዲያ ኢየሱስ የጠቀሰው የመሰብሰብ ሥራ ምንድን ነው? ከ144,000ዎቹ መካከል የቀሩት በሰማይ ሽልማታቸውን ስለሚያገኙበት ጊዜ መናገሩ ነበር። (1 ተሰ. 4:15-17፤ ራእይ 14:1) ይህ ክንውን የሚፈጸመው የማጎጉ ጎግ ጥቃት መሰንዘር ከጀመረ በኋላ ነው። (ሕዝ. 38:11) ከዚያም ኢየሱስ “በዚያ ጊዜ ጻድቃን በአባታቸው መንግሥት እንደ ፀሐይ ደምቀው ያበራሉ” በማለት የተናገረው ሐሳብ ይፈጸማል።—ማቴ. 13:43b

      15 ይህ ሲባል ታዲያ ቅቡዓን ክርስቲያኖች “ይነጠቃሉ” ማለት ነው? ብዙ የሕዝበ ክርስትና አባላት “መነጠቅ” የሚለው ትምህርት ክርስቲያኖች ሥጋዊ አካላቸውን እንደለበሱ ከምድር መወሰዳቸውን እንደሚያመለክት ያምናሉ። ከዚያም ኢየሱስ በሚታይ መንገድ በመመለስ ምድርን እንደሚገዛ ይጠብቃሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ “የሰው ልጅ ምልክት በሰማይ” እንደሚታይ እንዲሁም ኢየሱስ “በሰማይ ደመና” እንደሚመጣ በግልጽ ይናገራል። (ማቴ. 24:30) ሁለቱም አገላለጾች የሚያመለክቱት በዓይን የማይታይ ሁኔታን ነው። በተጨማሪም “ሥጋና ደም የአምላክን መንግሥት አይወርስም።” በመሆኑም ወደ ሰማይ የሚወሰዱ ሰዎች “የመጨረሻው መለከት በሚነፋበት ወቅት ድንገት፣ በቅጽበተ ዓይን [መለወጥ]” ይኖርባቸዋል።c (1 ቆሮንቶስ 15:50-53⁠ን አንብብ።) በምድር የቀሩት ታማኝ ቅቡዓን በቅጽበት ወደ ሰማይ ይሰበሰባሉ።

  • ‘መዳናችሁ እየቀረበ ነው’!
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | ሐምሌ 15
    • c በዚያ ጊዜ በሕይወት ያሉት ቅቡዓን ሥጋዊ አካላቸውን ይዘው ወደ ሰማይ አይሄዱም። (1 ቆሮ. 15:48, 49) የኢየሱስ አካል እንደተወገደ ሁሉ የእነሱም አካል ሳይወገድ አይቀርም።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ