የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “በትዕግሥት የመጠበቅ ዝንባሌ” ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ኅዳር 15
    • 9-11. አንደኛ ተሰሎንቄ 5:3 ፍጻሜውን አግኝቷል? አብራራ።

      9 አንደኛ ተሰሎንቄ 5:1-3⁠ን አንብብ። በቅርቡ ብሔራት “ሰላምና ደኅንነት ሆነ!” ብለው ያውጃሉ። በዚህ አዋጅ እንዳንዘናጋ ‘ነቅተን መኖርና የማመዛዘን ችሎታችንን መጠበቅ’ ያስፈልገናል። (1 ተሰ. 5:6) በመንፈሳዊ ንቁ ሆነን ለመኖር እንዲረዳን ይህ ከፍተኛ ትርጉም ያዘለ አዋጅ እንዲታወጅ መንገድ እየጠረጉ ያሉትን ክንውኖች በአጭሩ እንመልከት።

      10 ከሁለቱም የዓለም ጦርነቶች በኋላ ብሔራት ሰላም ለማስፈን ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። አንደኛው የዓለም ጦርነት ካበቃ በኋላ በምድር ላይ ሰላም ያሰፍናል በሚል ተስፋ የመንግሥታት ቃል ኪዳን ማኅበር ተቋቋመ። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ደግሞ የተባበሩት መንግሥታት በምድር ላይ ሰላም ያሰፍናል የሚል ታላቅ ተስፋ ተጣለበት። የመንግሥትም ሆነ የሃይማኖት መሪዎች እነዚህ ድርጅቶች ለሰው ዘር ሰላም ያመጣሉ የሚል ተስፋ ሰንቀው ነበር። ለምሳሌ ያህል፣ የተባበሩት መንግሥታት 1986⁠ን ዓለም አቀፍ የሰላም ዓመት ብሎ በመሰየም ጉዳዩ በሰፊው እንዲወራ አድርጎ ነበር። በዚያ ዓመት ከበርካታ አገሮችና ሃይማኖቶች የተሰባሰቡ መሪዎች ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መሪ ጋር በመሆን ስለ ሰላም ለመጸለይ በጣሊያን በምትገኘው የአሲሲ ከተማ ተሰብስበው ነበር።

      11 ይሁን እንጂ ሰላምና ደኅንነት ተብሎ የታወጀው ይህ አዋጅም ሆነ ሌሎች ተመሳሳይ አዋጆች በ1 ተሰሎንቄ 5:3 ላይ የተመዘገበው ትንቢት ፍጻሜ አልነበሩም። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? “ድንገት ይመጣባቸዋል” የተባለው ጥፋት ገና ያልመጣ በመሆኑ ነው።

      12. “ሰላምና ደኅንነት ሆነ!” የሚለውን አዋጅ በተመለከተ ምን የምናውቀው ነገር አለ?

      12 “ሰላምና ደኅንነት ሆነ!” የሚለውን ትልቅ ትርጉም ያዘለ አዋጅ የሚያውጀው ማን ነው? በዚህ ረገድ ሕዝበ ክርስትናም ሆነ የሌሎች ሃይማኖቶች መሪዎች ምን ሚና ይኖራቸዋል? የተለያዩ መንግሥታት መሪዎች ከዚህ አዋጅ ጋር በተያያዘ ተሳትፎ የሚኖራቸው እንዴት ነው? ቅዱሳን መጻሕፍት የሚገልጹልን ነገር የለም። ልፈፋው በምንም መልኩ ይቅረብ ወይም ምንም ያህል አሳማኝ ይሁን፣ በእርግጠኝነት የምናውቀው ነገር ቢኖር አዋጁ ከወሬ አያልፍም። ይህ አሮጌ ሥርዓት በሰይጣን ቁጥጥር ሥር እንዳለ ይቀጥላል። ሥርዓቱ ከላይ እስከ ታች በስብሷል፤ ደግሞም አይሻሻልም። ማናችንም ብንሆን ይህን ሰይጣናዊ ፕሮፓጋንዳ አምነን ክርስቲያናዊ የገለልተኝነት አቋማችንን ብንጥስ ምንኛ አሳዛኝ ይሆናል!

  • “በትዕግሥት የመጠበቅ ዝንባሌ” ማዳበር የምንችለው እንዴት ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—2013 | ኅዳር 15
    • 14. የታላቂቱ ባቢሎን ፍጻሜ መቅረቡን የሚጠቁመው ምንድን ነው?

      14 የዓለም የሐሰት ሃይማኖት ግዛት የሆነችው ታላቂቱ ባቢሎን የሚገባትን ቅጣት ታገኛለች። ‘ወገኖች፣ ሕዝቦች፣ ብሔራትና ቋንቋዎች’ አመርቂ ድጋፍ ሊሰጧት አይችሉም። አሁንም እንኳ ፍጻሜዋ መቅረቡን የሚጠቁሙ ነገሮች እያየን ነው። (ራእይ 16:12፤ 17:15-18፤ 18:7, 8, 21) እንዲያውም መገናኛ ብዙኃን በሃይማኖትና በሃይማኖት መሪዎች ላይ እየሰነዘሩ ያሉት ትችት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያየለ መሄዱ በአሁኑ ጊዜም እንኳ ድጋፍ እያጣች መሆኑን ያሳያል። ያም ሆኖ የታላቂቱ ባቢሎን መሪዎች ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማይደርስባቸው ይሰማቸዋል። ይሁንና እጅግ ተሳስተዋል! “ሰላምና ደኅንነት ሆነ!” የሚለውን አዋጅ ተከትሎ በሰይጣን ሥርዓት ውስጥ ያሉ የፖለቲካ ኃይሎች በሐሰት ሃይማኖት ላይ በድንገት ተነስተው ጠራርገው ያጠፏታል። ከዚህ በኋላ ታላቂቱ ባቢሎን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ትጠፋለች! እንዲህ ያሉ ጉልህ ስፍራ የሚሰጣቸው ክንውኖች የሚፈጸሙበትን ጊዜ በትዕግሥት መጠባበቅ ፈጽሞ አያስቆጭም።—ራእይ 18:8, 10

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ