የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሐምሌ 15
    • “ወንድሞች ሆይ፣ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ . . . እናዛችኋለን። እናንተ ግን፣ ወንድሞች ሆይ፣ መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ። በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፣ ይህን ተመልከቱት [“ምልክት አድርጉበት፣” NW]፣ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ። ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።”​—⁠2 ተሰሎንቄ 3:​6, 13-15

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሐምሌ 15
    • ‘በሥርዓት የማይሄዱ’ ሰዎችን በተመለከተ በ2 ተሰሎንቄ ላይ የተብራራው ጉዳይ ከላይ ከተጠቀሱት ሦስት ሁኔታዎች የተለየ ነገርን ያካትታል። ጳውሎስ እነዚህ ሰዎች አሁንም ‘ወንድሞች’ እንደሆኑና ተግሣጽ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲሁም እንደ ወንድሞች መያዝ እንዳለባቸው ጽፏል። በመሆኑም ‘በሥርዓት የማይሄዱ’ ወንድሞችን በሚመለከት የተከሰተው ችግር በክርስቲያኖች መካከል የተፈጠረ የግል ጉዳይ ተደርጎ የሚታይም ሆነ በቆሮንቶስ ከተከሰተው ሥነ ምግባር ከጎደለው ሁኔታ ጋር በተያያዘ ጳውሎስ እንዳደረገው የጉባኤ ሽማግሌዎች የውገዳ እርምጃ ለመውሰድ ጣልቃ እንዲገቡ የሚያስገድድ ክብደት ያለው ጉዳይም አይደለም። ‘በሥርዓት የማይሄዱት’ ወንድሞች በቆሮንቶስ የተወገደው ሰው የፈጸመውን ያህል የከፋ ኃጢአት አልፈጸሙም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    መጠበቂያ ግንብ—1999 | ሐምሌ 15
    • በተጨማሪም በግለሰብ ደረጃ ክርስቲያኖች በሥርዓት በማይሄዱ ሰዎች ላይ ‘ምልክት’ ማድረጋቸው ተገቢ መሆኑን ለጉባኤው አሳውቋል። ይህም ለጉባኤው በይፋ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠበት አኗኗር ጋር የእነማን ድርጊት እንደሚመሳሰል ግለሰቦች ማስተዋል አለባቸው ማለት ነው። ጳውሎስ “በሥርዓት ከማይሄድ ከማንኛውም ወንድም መራቅ” እንዳለባቸው መክሯቸዋል። ሆኖም ‘እንደ ወንድም መገሠጻቸውን መቀጠል’ ስለነበረባቸው ይህ አባባል ከእንዲህ ዓይነቱ ግለሰብ ሙሉ በሙሉ መራቅ አለባቸው ማለት እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በስብሰባዎችና ምናልባትም በአገልግሎት ላይ ክርስቲያናዊ ግንኙነት ማድረጋቸውን ይቀጥሉ ይሆናል። ወንድማቸው ለተሰጠው ተግሣጽ በጎ ምላሽ እንደሚሰጥና ሰላም የሚነሳ አካሄዱን እንደሚተው ተስፋ ሊያደርጉ ይችላሉ።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ