-
ይሖዋ ይደግፍሃልመጠበቂያ ግንብ—2015 | ታኅሣሥ 15
-
-
13. ከጤና ጋር በተያያዘ የሚሰጡ አስተያየቶችን በተመለከተ ምን ዓይነት ሚዛናዊ አመለካከት መያዝ ተገቢ ነው?
13 በዛሬው ጊዜ አንድ ክርስቲያን ‘በመፈወስ ስጦታ’ ተጠቅሞ ከሕመማችን ሊያድነን አይችልም። ይሁንና አንዳንድ ወንድሞች ምክር ባንጠይቃቸውም እንኳ በአሳቢነት ተነሳስተው ከጤና ጋር የተያያዙ አስተያየቶችን ይሰጣሉ። በእርግጥ አንዳንዶች የሚሰጡት ሐሳብ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ጢሞቴዎስ በአካባቢው ያለው ውኃ በመበከሉ የተነሳ ሳይሆን አይቀርም፣ ሆዱን ባመመው ጊዜ ጳውሎስ እንዲህ ዓይነት ምክር ሰጥቶታል።a (1 ጢሞቴዎስ 5:23ን አንብብ።) ይህ ግን የእምነት ባልንጀራችን፣ አንዳንድ ዕፀዋትን ወይም መድኃኒቶችን እንዲወስድ አሊያም አንድን የአመጋገብ ሥርዓት እንዲከተል ለማሳመን ከመሞከር በጣም የተለየ ነው፤ ምናልባትም ይህ ዓይነቱ ሕክምና ውጤታማ ላይሆን እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። አንዳንድ ጊዜ የጤና ምክር የሚሰጡ ሰዎች ‘አንድ ዘመዴ እንዲህ ዓይነት ሕመም ነበረበት፤ . . . ሲወስድ ግን ተሻለው’ እንደሚለው ዓይነት ሐሳብ ሲሰነዝሩ ይሰማል። ምክሩ የተሰጠው በአሳቢነት ሊሆን ይችላል፤ ያም ቢሆን በሰፊው የሚሠራበት መድኃኒትም ሆነ የሕክምና ዓይነት እንኳ ጉዳት ሊያስከትል እንደሚችል ማስታወስ ይኖርብናል።—ምሳሌ 27:12ን አንብብ።
-
-
ይሖዋ ይደግፍሃልመጠበቂያ ግንብ—2015 | ታኅሣሥ 15
-
-
a ዚ ኦሪጅንስ ኤንድ ኤንሸንት ሂስትሪ ኦቭ ዋይን የተባለው መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ “የታይፎይድ በሽታ አምጪ ተሕዋስያንን እና ሌሎች አደገኛ የሆኑ በዓይን የማይታዩ ሕይወት ያላቸው ነገሮችን የወይን ጠጅ ወዲያውኑ እንደሚገድላቸው በቤተ ሙከራ ማረጋገጥ ተችሏል።”
-