-
ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው?የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
-
-
ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ገንዘብ መጥፎ ነገር እንደሆነ አይገልጽም፤ ገንዘብ የክፉ ነገሮች ሁሉ መንስኤ እንደሆነም አይናገርም። ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተወሰደ የሚነገርለት “ገንዘብ የክፋት ሁሉ ሥር ነው” የሚለው የተለመደ አባባል የጥቅሱን የተሟላ ሐሳብ ያልያዘና የተሳሳተ መልእክት የሚያስተላልፍ ነው። ትክክለኛው የጥቅሱ ሐሳብ “ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ነው”a የሚል ነው።—1 ጢሞቴዎስ 6:10 የ1954 ትርጉም፤ ጎላ አድርገን የጻፍነው እኛ ነን።
-