የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ጥር
    • 9. ልጆች ለወላጆቻቸው እንዲታዘዙ ምን ሊረዳቸው ይችላል?

      9 ልጆች፣ ወላጆቻቸው ስላደረጉላቸው ነገሮች ማሰባቸው በዓለም ላይ የሚታየው ያለመታዘዝ ዝንባሌ እንዳይጋባባቸው ለመከላከል ይረዳቸዋል። በተጨማሪም ልጆች፣ የሁላችንም አባት የሆነው ይሖዋ ለወላጆቻቸው እንዲታዘዙ እንደሚጠብቅባቸው ማስታወሳቸው የመታዘዝን አስፈላጊነት እንዲገነዘቡ ያደርጋቸዋል። ልጆች ስለ ወላጆቻቸው መልካም ነገር መናገራቸው፣ እኩዮቻቸውም ለራሳቸው ወላጆች አክብሮት እንዲኖራቸው ሊያደርጋቸው ይችላል። እርግጥ ነው፣ ወላጆች ለልጆቻቸው ተፈጥሯዊ ፍቅር ከሌላቸው ልጆቹ ከልባቸው መታዘዝ ይከብዳቸው ይሆናል። በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ልጅ ወላጆቹ ከልባቸው እንደሚወዱት የሚሰማው ከሆነ መመሪያቸውን ለመጣስ በሚፈተንበት ጊዜም እንኳ እነሱን ለማስደሰት ሲል ይታዘዛቸዋል። ኦስተን የተባለ ወጣት እንዲህ ብሏል፦ “ትክክል ያልሆነ ነገር ለማድረግ የምፈተንበት ጊዜ እንዳለ አልክድም። ሆኖም ወላጆቼ የሚያወጡት መመሪያ የማያፈናፍን አይደለም፤ ደግሞም መመሪያዎቹን ለምን እንዳወጡ ያስረዱኛል፤ እኔም ሐሳቤን ስገልጽ ያዳምጡኛል። ይህም እንድታዘዛቸው ያነሳሳኛል። ወላጆቼ እንደሚወዱኝ አልጠራጠርም፤ ይህ ደግሞ እነሱን ለማስደሰት እንድጥር ያደርገኛል።”

      10, 11. (ሀ) በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ፍቅር እንደማይኖራቸው የሚያሳዩት የትኞቹ ባሕርያት ናቸው? (ለ) እውነተኛ ክርስቲያኖች እነማንን ጭምር ይወዳሉ?

      10 ጳውሎስ የዘረዘራቸው ሌሎች መጥፎ ባሕርያትም በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ ሰዎች አንዳቸው ለሌላው ፍቅር እንደማይኖራቸው ያሳያሉ። ሐዋርያው፣ ልጆች “ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ” እንደሚሆኑ ከተናገረ በኋላ የማያመሰግኑ ግለሰቦች እንደሚኖሩ መጥቀሱ ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች እንዲህ ያለ ባሕርይ የሚያንጸባርቁት ሌሎች ላሳዩአቸው ደግነት አድናቆት ስለሚጎድላቸው ነው። ጳውሎስ አክሎም አንዳንዶች ታማኝ እንደማይሆኑ ተናግሯል። በተጨማሪም ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ ሰዎች ይኖራሉ፤ በሌላ አባባል ከሌሎች ጋር ለመታረቅ እንቢተኞች ይሆናሉ። ከዚህም ሌላ ተሳዳቢዎች እና ከዳተኞች ይሆናሉ፤ ይህም ሰዎችን ሌላው ቀርቶ አምላክን እንኳ እንደሚተቹና የሚያዋርድ ቃል እንደሚናገሩ የሚያሳይ ነው። ጳውሎስ ስም አጥፊ የሆኑ ሰዎች እንደሚኖሩም ተናግሯል፤ እንዲህ ያሉት ግለሰቦች የሌሎችን መልካም ስም የሚያጎድፍ ወሬ ያናፍሳሉ።a

  • አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ጥር
    • a “ስም አጥፊ” ወይም “ከሳሽ” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ዲያቦሎስ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህ ቃል የአምላክን ስም ያጠፋው የሰይጣን መጠሪያ ሆኖ ተሠርቶበታል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ