-
ቤታችሁ አስተማማኝ የእረፍት ቦታ እንዲሆን አድርጉንቁ!—2007 | ጥቅምት
-
-
“ፍቅር የሌላቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ ‘የመጨረሻው ዘመን’ ተብሎ በሚጠራው በእኛ ዘመን የሚኖሩ ብዙ ሰዎች የሚያሳዩትን ባሕርይ የሚገልጸው በዚህ መንገድ ነው። (2 ጢሞቴዎስ 3:1, 3, 4) በቤተሰብ ውስጥ እንደ ወረርሽኝ ተዛምቶ የሚገኘው ልጆችን የማስነወር ድርጊት ይህ ትንቢት እውነት ለመሆኑ ጉልህ ማስረጃ ነው። እንዲያውም “ፍቅር የሌላቸው” ተብሎ የተተረጎመው አስቶርጎስ የሚለው የግሪክኛ ቃል በቤተሰብ አባላት በተለይም በወላጆችና በልጆች መካከል ሊኖር የሚገባው ፍቅር መጥፋቱን የሚያመለክት ነው።a ብዙውን ጊዜም ልጆች የሚነወሩት በቤተሰባቸው አባል ወይም በዘመዳቸው ነው።
-
-
ቤታችሁ አስተማማኝ የእረፍት ቦታ እንዲሆን አድርጉንቁ!—2007 | ጥቅምት
-
-
a ይህ ጥንታዊ ግሪክኛ ቃል “ለዘመዶች ወይም ለቤተሰብ ደንታ ቢስ መሆን” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። በመሆኑም አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ይህን ጥቅስ “ለቤተሰቦቻቸው የተፈጥሮ ፍቅር የሌላቸው” በማለት አስቀምጦታል።
-