የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 4/15 ገጽ 32
  • ‘ከሕፃንነትህም ጀምረህ አውቀሃል’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ከሕፃንነትህም ጀምረህ አውቀሃል’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 4/15 ገጽ 32

‘ከሕፃንነትህም ጀምረህ አውቀሃል’

በቅርብ የተደረጉ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሕፃናትን ማናገር የማሰብ፣ የማገናዘብና ችግሮችን የመፍታት ችሎታቸውን መጠቀም እንዲጀምሩ ስለሚያደርግ ለአእምሮአቸው እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። ይህ በተለይ ከተወለዱ ጀምሮ እስከ አንድ ዓመት ድረስ ያለውን ጊዜ ያመለክታል። ኢንተርናሽናል ሄራልድ ትሪቢዩን የተባለው ጋዜጣ “ሕፃኑ በየቀኑ የሚሰማቸው ቃላት ቁጥር የወደፊት የማሰብ ችሎታውን፣ በትምህርቱ ስኬታማ የመሆን ወይም በማኅበራዊ ሕይወት የሚኖረውን ብቃት የሚያመለክቱ ወሳኝ የሆኑ ነገሮች ናቸው” ብለው አንዳንድ ተመራማሪዎች እንደሚያምኑ ዘግቧል።

ይሁን እንጂ ሕፃኑ እነዚህን ቃላት በቀጥታ ከሰው መስማት አለበት። ቴሌቪዥን ወይም ራዲዮ ምትክ ሊሆኑ አይችሉም።

በዩ ኤስ ኤ ሲያትል በዋሽንግተን ዩንቨርሲቲ ያሉ አንዲት የነርቭ ሳይንቲስት እንዲህ ብለዋል:- “የነርቭ አውታሮች መያያዝ የሚጀምሩት ወዲያው ሕፃኑ እንደተወለደ መሆኑንና ይህ ነርቫዊ ትይይዝ እንዲካሄድ የሕፃኑን አንጎል የሚቀሰቅሰው ነገር መኖር እንዳለበት አሁን ደርሰንበታል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ይህ ሂደት መቼ እንደሚጀምር አናውቅም ነበር። ለምሳሌ ሕፃናት የተወለዱበትን ቋንቋ ድምፅ በስድስት ወር ዕድሜ ውስጥ ያውቃሉ።”

ሕፃናት አእምሯቸው እንዲዳብር የሚያስፈልጋቸው ነገር በቂ ፍቅር ማግኘት ነው የሚለው ሰፊ ተቀባይነትን ያገኘ አመለካከት በቅርብ ጊዜያት ከተደረጉ ጥናቶች ተቃውሞ ገጥሞታል። በተጨማሪም ለልጁ እድገት ወላጆች ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ አጉልተዋል።

ይህም ሐዋርያው ጳውሎስ በመንፈስ አነሳሽነት ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ የተናገረውን ያስታውሰናል:- “ከሕፃንነትህም ጀምረህ፣ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉትን ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል።” (በሰያፍ የጻፍነው እኛ ነን።) ጢሞቴዎስ ከሕፃንነቱ ጀምሮ አማኝ ከሆኑት እናቱና አያቱ ከቅዱሳን መጻሕፍት የተነገረው ቃል ብቁ የአምላክ አገልጋይ እንዲሆን ከፍተኛ እርዳታ እንዳደረገለት ጥርጥር የለውም።​—⁠2 ጢሞቴዎስ 1:​5፤ 3:​15

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ