የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • ምዕራፍ 1. የተከፈተ መጽሐፍ ቅዱስ

      ምዕራፍ 01

      መጽሐፍ ቅዱስን መማርህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

      ሁላችንም ስለ ሕይወት፣ ስለ ሞትና ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተለያዩ ጥያቄዎችን እናነሳለን፤ እንዲሁም መከራ የሚደርስብን ለምን እንደሆነ ማወቅ እንፈልጋለን። በተጨማሪም በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚያጋጥሙን ጉዳዮች ያስጨንቁናል፤ ለምሳሌ ለኑሮ የሚያስፈልጉንን ነገሮች ማግኘት ወይም የቤተሰባችንን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የምንችልበት መንገድ ያሳስበናል። ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስ በአእምሯቸው ውስጥ ለሚፈጠሩ ትላልቅ ጥያቄዎች መልስ እንደሚሰጥ ብቻ ሳይሆን ለዕለት ተዕለት ሕይወታቸው የሚጠቅም ምክር እንደያዘም አስተውለዋል። ታዲያ ሁሉም ሰው መጽሐፍ ቅዱስን ቢማር ጠቃሚ አይመስልህም?

      1. መጽሐፍ ቅዱስ ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል?

      መጽሐፍ ቅዱስ ለሚከተሉት ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል፦ ሕይወት ያገኘነው እንዴት ነው? የተፈጠርንበት ዓላማ ምንድን ነው? ጥሩ ሰዎች መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው? ሰው ሲሞት ምን ይሆናል? ሰዎች ሰላም ሰፍኖ ማየት ቢፈልጉም ጦርነት ይህን ያህል የበዛው ለምንድን ነው? ወደፊት ምድር ትጠፋ ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ላሉ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ጥረት እንድናደርግ ያበረታታናል። ደግሞም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለጥያቄዎቻቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ መልስ ማግኘት ችለዋል።

      2. መጽሐፍ ቅዱስ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ደስተኛ እንድንሆን የሚረዳን እንዴት ነው?

      መጽሐፍ ቅዱስ ጠቃሚ ምክሮች ይዟል። ለምሳሌ ያህል፣ የቤተሰብን ሕይወት አስደሳች ማድረግ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ያስተምራል። ጭንቀትን መቋቋምና በምንሠራው ሥራ ደስተኛ መሆን ስለምንችልበት መንገድ ምክር ይሰጣል። ይህን ጽሑፍ ተጠቅመህ መወያየትህን ስትቀጥል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እነዚህ ጉዳዮች ምን እንደሚያስተምር ትረዳለህ። ይህም ‘ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ [በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት ሐሳቦች በሙሉ] ጠቃሚ’ እንደሆኑ እንድትገነዘብ ያደርግሃል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

      ይህ ጽሑፍ መጽሐፍ ቅዱስን የሚተካ አይደለም። ከዚህ ይልቅ መጽሐፍ ቅዱስን አንተው ራስህ እንድትመረምር ለመርዳት ታስቦ የተዘጋጀ ነው። በመሆኑም በምዕራፉ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች አውጥተህ እንድታነብና ከምትማረው ነገር ጋር እንድታነጻጽር እናበረታታሃለን።

      ጠለቅ ያለ ጥናት

      መጽሐፍ ቅዱስ ብዙዎችን የረዳቸው እንዴት እንደሆነ፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነና መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ለመረዳት የሌሎች እገዛ የሚያስፈልግህ ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።

      3. መጽሐፍ ቅዱስ አስተማማኝ መመሪያ ይሰጠናል

      መጽሐፍ ቅዱስ ልክ እንደ ደማቅ መብራት ነው። ጥሩ ውሳኔዎችን እንድናደርግ እንዲሁም ከፊታችን የሚጠብቀን ነገር ፍንትው ብሎ እንዲታየን ይረዳናል።

      መዝሙር 119:105⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • የዚህ ጥቅስ ጸሐፊ ለመጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት ነበረው?

      • አንተስ ለመጽሐፍ ቅዱስ ምን አመለካከት አለህ?

      አመሻሹ ላይ በአንድ ሐይቅ ዳርቻ በሚገኝ ድንጋያማ አካባቢ መንገዱ ላይ የእጅ ባትሪ እያበራ የሚጓዝ ሰው

      4. መጽሐፍ ቅዱስ ለጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጠናል

      አንዲት ሴት ለበርካታ ዓመታት ሲያስጨንቋት ለነበሩ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ መልስ አግኝታለች። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ ፈጽሞ ተስፋ አትቁረጡ! (1:48)

      • በቪዲዮው ላይ የታየችው ሴት ምን ጥያቄዎች ነበሯት?

      • መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቷ የጠቀማት እንዴት ነው?

      መጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችን እንድንጠይቅ ያበረታታናል። ማቴዎስ 7:7⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለየትኛው ጥያቄህ መልስ ማግኘት ትፈልጋለህ?

      5. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ ትችላለህ

      ብዙ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ያስደስታቸዋል። እንዲህ በማድረጋቸውም የተለያዩ ጥቅሞች እያገኙ ነው። ቪዲዮውን ተመልከቱ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ (2:05)

      • በቪዲዮው ላይ የታዩት ወጣቶች፣ በአጠቃላይ ስለ ንባብ ምን አመለካከት አላቸው?

      • መጽሐፍ ቅዱስን ስለ ማንበብ ግን የተለየ አመለካከት ያላቸው ለምንድን ነው?

      መጽሐፍ ቅዱስ፣ በውስጡ የያዘው ሐሳብ መጽናኛና ተስፋ እንደሚሰጠን ይናገራል። ሮም 15:4⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው ማጽናኛና ተስፋ ይበልጥ ማወቅ ትፈልጋለህ?

      6. መጽሐፍ ቅዱስን በደንብ ለመረዳት የሌሎች እርዳታ ያስፈልገናል

      ብዙዎች መጽሐፍ ቅዱስን በግላቸው ከማንበብ በተጨማሪ ከሌሎች ጋር መወያየቱን ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል። የሐዋርያት ሥራ 8:26-31⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት ምን ያስፈልገናል?—ቁጥር 30 እና 31⁠ን ተመልከት።

      1. ወንጌላዊው ፊልጶስ ለኢትዮጵያዊው ሰው ቅዱሳን መጻሕፍትን ሲያብራራለት 2. አንዲት የይሖዋ ምሥክር ሁለት ልጆች ከያዘች እናት ጋር ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስትወያይ

      ኢትዮጵያዊው ሰው የሚያነበውን ነገር ለመረዳት እርዳታ አስፈልጎት ነበር። በዛሬው ጊዜ በርካታ ሰዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ጋር መወያየታቸው ጠቃሚ እንደሆነ ይሰማቸዋል

      አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጊዜ ማባከን ነው።”

      • አንተስ ምን ትላለህ?

      ማጠቃለያ

      መጽሐፍ ቅዱስ ለዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚጠቅም ምክር ይሰጣል፣ ለምናነሳቸው ወሳኝ ጥያቄዎች መልስ ይዟል እንዲሁም ማጽናኛና ተስፋ ይሰጠናል።

      ክለሳ

      • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ምን ምክሮች እናገኛለን?

      • መጽሐፍ ቅዱስ ለየትኞቹ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል?

      • ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ስለ ምን መማር ትፈልጋለህ?

      ግብ

      ምርምር አድርግ

      የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮች ለዘመናችን ጠቃሚ የሆኑት እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

      “ዘመን የማይሽራቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች” (መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2018)

      መጽሐፍ ቅዱስ ከልጅነቱ ጀምሮ ከአሉታዊ ስሜት ጋር ሲታገል የኖረን ሰው የረዳው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

      በሕይወቴ ደስተኛ ሆንኩ (2:53)

      መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን ለቤተሰብ ሕይወት ጠቃሚ የሆነ ምክር አንብብ።

      “ቤተሰብ ስኬታማ እንዲሆን የሚረዱ 12 ወሳኝ ነገሮች” (ንቁ! ቁጥር 2 2018)

      መጽሐፍ ቅዱስ የዚህን ዓለም ገዢ በተመለከተ የያዘው ሐሳብ ከብዙዎች አመለካከት የሚለየው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

      መጽሐፍ ቅዱስን መማር የሚኖርብን ለምንድን ነው?—ሙሉው ቪዲዮ (3:14)

  • መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 1. መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ የአምላክ ቃል ነው ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?

      መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት 40 የሚሆኑ ሰዎች ናቸው፤ የተጻፈውም ከ1513 ዓ.ዓ. እስከ 98 ዓ.ም. ድረስ ባሉት 1,600 ዓመታት ገደማ ውስጥ ነው። ጸሐፊዎቹ የተለያየ አስተዳደግና የኑሮ ደረጃ ያላቸው ናቸው። ያም ቢሆን ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች እርስ በርስ ይስማማሉ። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ስለሆነ ነው። (1 ተሰሎንቄ 2:13⁠ን አንብብ።) ጸሐፊዎቹ የመዘገቡት የራሳቸውን ሐሳብ አይደለም። ከዚህ ይልቅ ‘ከአምላክ የተቀበሉትን በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው ተናግረዋል።’a (2 ጴጥሮስ 1:21) አምላክ ሰዎች የእሱን ሐሳብ እንዲጽፉ ለመምራት ወይም ለማነሳሳት መንፈስ ቅዱስን ተጠቅሟል።—2 ጢሞቴዎስ 3:16

  • መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 4. መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ስለ መጽሐፉ ባለቤት ማወቅ እንችላለን

      ቪዲዮውን ተመልከቱ። ከዚያም 2 ጢሞቴዎስ 3:16⁠ን አንብቡና በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ባለቤት ማን ነው?—ተቀንጭቦ የተወሰደ (2:48)

      • መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች ከሆኑ የአምላክ ቃል ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?

      • አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን ለጻፉት ሰዎች ሐሳቡን አስተላልፏል ብሎ ማመን ምክንያታዊ ይመስልሃል?

      አንድ አለቃ ለጸሐፊው መልእክቱን ሲነግረውና ጸሐፊው መልእክቱን ሲጽፍ

      አንድ ጸሐፊ፣ አለቃው የነገረውን መልእክት ተቀብሎ ደብዳቤ ሊጽፍ ይችላል፤ ሆኖም የመልእክቱ ባለቤት ጸሐፊው ሳይሆን አለቃው ነው። በተመሳሳይም መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት፣ ሰዎች ቢሆኑም የመልእክቱ ምንጭ አምላክ ነው

  • መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ