-
መጽሐፍ ቅዱስ የአምላክ ቃል ነው?መጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 1
-
-
“ቅዱስ መጽሐፉ ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው፤ እንዲሁም ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ነገሮችን ለማቅናትና በጽድቅ ለመምከር ይጠቅማል፤ ይኸውም የአምላክ ሰው ለማንኛውም መልካም ሥራ በሚገባ በመታጠቅ ሙሉ በሙሉ ብቁ ሆኖ እንዲገኝ ነው።”—2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17
ሐዋርያው ጳውሎስ መጽሐፍ ቅዱስ ያለውን ላቅ ያለ ዋጋ ለመግለጽ የተጠቀመበት እንዴት ያለ ግሩም ሐሳብ ነው! እርግጥ ነው፣ ጳውሎስ ይህን ሐሳብ የተናገረው በዚያ ዘመን ይገኝ የነበረውንና በአሁኑ ጊዜ ሰዎች አንዳንድ ጊዜ ብሉይ ኪዳን ብለው የሚጠሩትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለማመልከት ነው። ይሁን እንጂ ሐሳቡ በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት የኢየሱስ ታማኝ ደቀ መዛሙርት የጻፏቸውን ጨምሮ ለ66ቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ ይሠራል።
አንተስ መጽሐፍ ቅዱስን ልክ እንደ ጳውሎስ ከፍ አድርገህ ትመለከተዋለህ? መጽሐፍ ቅዱስን የጻፉት ሰዎች በአምላክ መንፈስ ተመርተው ጽፈውታል ብለህ ታምናለህ? በመጀመሪያው መቶ ዘመን ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያኖች እንዲህ ያለ አመለካከት ነበራቸው። ከዚያ በኋላ በነበሩት ዘመናትም እውነተኛ ክርስቲያኖች ተመሳሳይ እምነት ነበራቸው። ለምሳሌ ያህል፣ በአሥራ አራተኛው መቶ ዘመን የኖረው ጆን ዊክሊፍ የተባለ እንግሊዛዊ ቄስ መጽሐፍ ቅዱስን “ፈጽሞ ስህተት የማይገኝበት የእውነት ሕግ” እንደሆነ አድርጎ ተመልክቶታል። ዘ ኒው ባይብል ዲክሽነሪ ከላይ ያለውን የጳውሎስ ሐሳብ አስመልክቶ አስተያየት ሲሰጥ በመለኮታዊ “መሪነት [መጻፉ] መጽሐፍ ቅዱስ የያዛቸው ነገሮች በሙሉ እውነት ለመሆናቸው ዋስትና ይሰጣል” ብሏል።
-
-
መጽሐፍ ቅዱስ በእርግጥም በመንፈስ መሪነት የተጻፈ የአምላክ ቃል ነውመጠበቂያ ግንብ—2010 | መጋቢት 1
-
-
ሐዋርያው ጳውሎስ፣ መጽሐፍ ቅዱስ “በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው” ብሎ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር? (2 ጢሞቴዎስ 3:16) ጳውሎስ ይህን የጻፈው በግሪክኛ ሲሆን ይህ ሐሳብ ቃል በቃል ሲተረጎም “አምላክ የተነፈሰበት” የሚል ትርጉም አለው። ጳውሎስ ይህን ሲል አምላክ በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች እሱ የሚፈልገውን ሐሳብ ብቻ እንዲጽፉ መርቷቸዋል ማለቱ ነበር።
-