የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ምንጊዜም በይሖዋ ታመኑ!
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | ሚያዝያ 15
    • 2 ሐዋርያው ጳውሎስ በሮም ለሁለተኛ ጊዜ የታሰረው እንዲህ ያለ ያልተረጋጋ ሁኔታ በሰፈነበት ወቅት ሳይሆን አይቀርም። ታዲያ ሌሎች ክርስቲያኖች ሊረዱት ይመጡ ይሆን? ጳውሎስ መጀመሪያ ላይ ይህ ጉዳይ ሳያሳስበው አልቀረም፤ ምክንያቱም ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ “የመጀመሪያ መከላከያዬን ባቀረብኩበት ወቅት ሁሉም ትተውኝ ሄዱ እንጂ ከእኔ ጎን የቆመ ማንም አልነበረም፤ አምላክ ይህን አይቁጠርባቸው” ብሏል። ያም ሆኖ ጳውሎስ ምንም እርዳታ አላገኘም ማለት አይደለም። “ጌታ አጠገቤ ቆሞ ኃይል ሰጠኝ” በማለት ጽፏል። በእርግጥም፣ ጌታ ኢየሱስ ለጳውሎስ የሚያስፈልገውን ኃይል ሰጥቶታል። ለመሆኑ ይህ መለኮታዊ እርዳታ ምን ያህል ጠቅሞታል? ጳውሎስ ‘ከአንበሳ አፍ ዳንኩ’ በማለት ውጤቱን ነግሮናል።—2 ጢሞ. 4:16, 17a

      3 ጳውሎስ ይህን ሁኔታ ማስታወሱ፣ በዚያ ወቅት ያጋጠሙትንም ሆነ ወደፊት የሚደርሱበትን ፈተናዎች በጽናት እንዲወጣ ይሖዋ ሊያጠናክረው የሚችል መሆኑን እንዲተማመን በማድረግ አበረታትቶት መሆን አለበት። እንዲያውም “ጌታ ከክፉ ሥራ ሁሉ ይታደገኛል” በማለት አክሎ ተናግሯል። (2 ጢሞ. 4:18) በእርግጥም ጳውሎስ፣ ከሰዎች የሚገኘው እርዳታ ውስን በሚሆንበት ጊዜም እንኳ ይሖዋና ልጁ በሚሰጡን እርዳታ መተማመን እንደሚቻል ተምሯል።

  • ምንጊዜም በይሖዋ ታመኑ!
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | ሚያዝያ 15
    • “ከአንበሳ አፍ”

      10-12. (ሀ) በጠና የታመመ የቤተሰቡን አባል የሚንከባከብ አንድ ክርስቲያን ሁኔታዎች በጣም ተፈታታኝ ሊሆኑበት የሚችሉት እንዴት ነው? (ለ) አንድ ክርስቲያን አስቸጋሪ ሁኔታ ሲያጋጥመው በይሖዋ መታመኑ ከእሱ ጋር ያለውን ዝምድና የሚነካው እንዴት ነው? ምሳሌ ስጥ።

      10 ከባድ ፈተና ሲያጋጥምህ አንተም ልክ እንደ ጳውሎስ “አንበሳ አፍ” ውስጥ እንደገባህ ወይም ልትገባ እንደተቃረብክ ያህል ሊሰማህ ይችላል። በይሖዋ መታመን በጣም አስቸጋሪ ሆኖም በጣም አስፈላጊ የሚሆነው በዚህ ጊዜ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ በጠና የታመመ የቤተሰብህን አባል እየተንከባከብክ ይሆናል። ምናልባትም ይሖዋ ጥበብና ብርታት እንዲሰጥህ ጸልየህ ሊሆን ይችላል።b ታዲያ በዚህ ረገድ የምትችለውን ሁሉ ካደረግህ በኋላ፣ የይሖዋ ዓይን በአንተ ላይ እንደሆነና በታማኝነት ለመጽናት የሚያስፈልግህን ነገር እሱ እንደሚሰጥህ በማወቅህ ውስጥህ አይረጋጋም?—መዝ. 32:8

  • ምንጊዜም በይሖዋ ታመኑ!
    መጠበቂያ ግንብ—2015 | ሚያዝያ 15
    • a ጳውሎስ ‘ከአንበሳ አፍ ዳንኩ’ ሲል ቃል በቃል አሊያም በምሳሌያዊ መንገድ እየተናገረ ሊሆን ይችላል።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ