-
እናቶች—ከኤውንቄ ምሳሌ ተማሩመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ሚያዝያ
-
-
ልጆቻችሁን በምግባር አስተምሩ
12. በ2 ጢሞቴዎስ 1:5 መሠረት ኤውንቄ ለጢሞቴዎስ ምን ምሳሌ ትታለታለች?
12 ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 1:5ን አንብብ። ኤውንቄ ለጢሞቴዎስ ጥሩ ምሳሌ ሆናለታለች። እውነተኛ እምነት በሥራ መገለጽ እንዳለበት አስተምራው መሆን አለበት። (ያዕ. 2:26) ጢሞቴዎስ እናቱ ማንኛውንም ነገር የምታደርገው ለይሖዋ ባላት ጠንካራ ፍቅር ተነሳስታ እንደሆነ ማየቱ አይቀርም። እናቱ ይሖዋን ማገልገሏ ደስታ እንዳስገኘላት አስተውሎ መሆን አለበት። የኤውንቄ ምሳሌነት በጢሞቴዎስ ላይ ምን ውጤት አምጥቷል? ሐዋርያው ጳውሎስ እንደገለጸው ጢሞቴዎስ እንደ እናቱ ጠንካራ እምነት ነበረው። ይህ እንዲሁ በአጋጣሚ የመጣ ነገር አይደለም። ጢሞቴዎስ የእናቱን ምሳሌነት አስተውሏል፤ እንዲሁም እንደ እሷ ለመሆን ተነሳስቷል። በተመሳሳይም በአሁኑ ጊዜ ብዙ እናቶች “ያለቃል” የቤተሰባቸውን አባሎች ልብ መንካት ችለዋል። (1 ጴጥ. 3:1, 2) እናንተም እንዲሁ ማድረግ ትችላላችሁ። እንዴት?
13. እናቶች ከይሖዋ ጋር ላላቸው ዝምድና ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው ለምንድን ነው?
13 ከይሖዋ ጋር ላላችሁ ዝምድና ቅድሚያ ስጡ። (ዘዳ. 6:5, 6) እንደ አብዛኞቹ እናቶች እናንተም ብዙ መሥዋዕት ትከፍላላችሁ። የልጆቻችሁን አካላዊ ፍላጎት ለማሟላት ጊዜያችሁን፣ ገንዘባችሁን፣ እንቅልፋችሁን እንዲሁም ሌሎች ነገሮችን መሥዋዕት ታደርጋላችሁ። ይሁንና ቤተሰባችሁን በመንከባከብ ከመጠመዳችሁ የተነሳ ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና መሥዋዕት እንዳታደርጉ መጠንቀቅ ይኖርባችኋል። ብቻችሁን ለመጸለይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን በግላችሁ ለማጥናት እንዲሁም በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት አዘውትራችሁ ጊዜ መድቡ። እንዲህ ካደረጋችሁ የራሳችሁን መንፈሳዊነት ታጠናክራላችሁ፤ እንዲሁም ለቤተሰባችሁ አልፎ ተርፎም ለሌሎች ጥሩ ምሳሌ ትሆናላችሁ።
-
-
እናቶች—ከኤውንቄ ምሳሌ ተማሩመጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022 | ሚያዝያ
-
-
16. የእናቶች ምሳሌ በሌሎች ላይ ምን ተጽዕኖ ሊያሳድር ይችላል?
16 እናቶች፣ መልካም ምሳሌነታችሁ በሌሎች ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አስታውሱ። እንዴት? የኤውንቄ ምሳሌ በሐዋርያው ጳውሎስ ላይ ምን ተጽዕኖ እንዳሳደረ ልብ በሉ። ግብዝነት የሌለበት የጢሞቴዎስ እምነት “በመጀመሪያ . . . በኤውንቄ ዘንድ” እንደነበር ጳውሎስ ተናግሯል። (2 ጢሞ. 1:5) ጳውሎስ የኤውንቄን እምነት መጀመሪያ ላይ ያስተዋለው መቼ ነው? ጳውሎስ ከሎይድና ከኤውንቄ ጋር በልስጥራ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኘው በመጀመሪያ ሚስዮናዊ ጉዞው ወቅት ሳይሆን አይቀርም፤ ምናልባትም ክርስቲያን እንዲሆኑ የረዳቸው እሱ ሊሆን ይችላል። (ሥራ 14:4-18) የሚገርመው ከ15 ዓመታት ገደማ በኋላ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ ደብዳቤ በጻፈበት ወቅት የኤውንቄን ታማኝነት አስታውሶ ነበር። እንዲሁም እምነቷ ሊኮረጅ የሚገባው እንደሆነ ገልጿል። የኤውንቄ ምሳሌነት ሐዋርያው ጳውሎስንና በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ በርካታ ክርስቲያኖችን አበረታቶ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም። እናንተም ልጆቻችሁን የምታሳድጉት ብቻችሁን ወይም በሃይማኖት በተከፋፈለ ቤተሰብ ውስጥ ከሆነ የታማኝነት ምሳሌያችሁ በዙሪያችሁ ያሉትን እንደሚያጠናክርና እንደሚያነቃቃ አትዘንጉ።
-