የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • የይሖዋ ሕዝብ “ከክፋት ይራቅ”
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | ሐምሌ 15
    • 9. ‘የማይረባና ትርጉም የለሽ የሆነ ክርክር’ በጥንቱ የክርስቲያን ጉባኤ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?

      9 የአምላክ ቃል፣ ክርስቲያኖች ሊርቋቸው የሚገቡ አንዳንድ ክፉ ነገሮችን ለይቶ ይጠቅሳል። ለምሳሌ ያህል፣ በ⁠2 ጢሞቴዎስ 2:19 ዙሪያ ባለው ሐሳብ ላይ ጳውሎስ ‘ስለ ቃላት መነታረክ’ ተገቢ እንዳልሆነ እንዲሁም ‘ከከንቱ ንግግሮች መራቅ’ እንደሚገባው ለጢሞቴዎስ ነግሮታል። (2 ጢሞቴዎስ 2:14, 16⁠ን አንብብ።) በዚያ ወቅት አንዳንድ የጉባኤው አባላት የክህደት ትምህርቶችን እያስፋፉ ነበር። ሌሎች ደግሞ አከራካሪ ሐሳቦችን ያመጡ የነበረ ይመስላል። እነዚህ አከራካሪ ሐሳቦች ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በቀጥታ የማይጋጩ ቢሆኑም እንኳ ክፍፍል ይፈጥራሉ። ይህ ደግሞ በቃላት ላይ መነታረክንና መጨቃጨቅን ስለሚያስከትል በጉባኤው ውስጥ ጤናማ መንፈሳዊ ሁኔታ እንዳይኖር ያደርጋል። ጳውሎስ “ከማይረባና ትርጉም የለሽ ከሆነ ክርክር [የመራቅን]” አስፈላጊነት ጎላ አድርጎ የገለጸው ለዚህ ነው።—2 ጢሞ. 2:23 አ.መ.ት

      10. ከሃዲዎች ሲያጋጥሙን ምን ማድረግ ይኖርብናል?

      10 በዛሬው ጊዜ ባለው የይሖዋ ሕዝቦች ጉባኤ ውስጥ በአብዛኛው ክህደት አያጋጥምም። ያም ቢሆን ከየትም ይምጣ ከየት ቅዱስ ጽሑፋዊ ያልሆነ ትምህርት ካጋጠመን ቆራጥ በመሆን እንዲህ ካለው ትምህርት ወዲያውኑ መራቅ ይኖርብናል። ከከሃዲዎች ጋር ፊት ለፊት በመነጋገርም ሆነ ድረ ገጻቸው ላይ አስተያየት በማስፈር አሊያም በሌላ መንገድ ክርክር መግጠም የጥበብ አካሄድ አይደለም። እንዲህ ያለ ውይይት የምናደርገው ግለሰቡን ለመርዳት አስበን ቢሆንም እንኳ ይህን ማድረግ እስከ አሁን ከተመለከትነው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያ ጋር የሚጋጭ ነው። በመሆኑም የይሖዋ ሕዝቦች እንደመሆናችን መጠን ከከሃዲዎች ሙሉ በሙሉ እንርቃለን።

      ከሃዲዎች የይሖዋ ምሥክሮችን ክርክር ውስጥ ለማስገባት ሲሞክሩ

      ከከሃዲዎች ጋር ከመከራከር ተቆጠቡ (አንቀጽ 10⁠ን ተመልከት)

      ከሃዲዎች የይሖዋ ምሥክሮችን ክርክር ውስጥ ለማስገባት ሲሞክሩ

      ከከሃዲዎች ጋር ከመከራከር ተቆጠቡ (አንቀጽ 10⁠ን ተመልከት)

      11. ‘የማይረባና ትርጉም የለሽ የሆነ ክርክር’ እንዲነሳ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ምንድን ነው? ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጥሩ ምሳሌ መሆን የሚችሉት እንዴት ነው?

      11 ከክህደት በተጨማሪ የጉባኤውን ሰላም ሊያደፈርሱ የሚችሉ ሌሎች ነገሮችም አሉ። ለምሳሌ ያህል፣ ከመዝናኛ ምርጫ ጋር በተያያዘ የአመለካከት ልዩነት መኖሩ ‘የማይረባና ትርጉም የለሽ የሆነ ክርክር’ ሊያስከትል ይችላል። እርግጥ ነው፣ አንዳንድ ክርስቲያኖች የይሖዋን የሥነ ምግባር መሥፈርቶች የሚጥሱ መዝናኛዎችን የሚያበረታቱ ከሆነ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጭቅጭቅ ላለመፍጠር በማሰብ እንዲህ ያለውን ድርጊት በቸልታ ማለፍ የለባቸውም። (መዝ. 11:5፤ ኤፌ. 5:3-5) በሌላ በኩል ደግሞ ሽማግሌዎች የራሳቸውን አመለካከት እንዳያራምዱ መጠንቀቅ አለባቸው። ለክርስቲያን የበላይ ተመልካቾች የተሰጠውን የሚከተለውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ማሳሰቢያ በታማኝነት መከተል ይኖርባቸዋል፦ “በአደራ የተሰጣችሁን የአምላክ መንጋ ጠብቁ፤ . . . የአምላክ ንብረት በሆኑት ላይ ሥልጣናችሁን በማሳየት ሳይሆን ለመንጋው ምሳሌ በመሆን ጠብቁ።”—1 ጴጥ. 5:2, 3፤ 2 ቆሮንቶስ 1:24⁠ን አንብብ።

  • የይሖዋ ሕዝብ “ከክፋት ይራቅ”
    መጠበቂያ ግንብ—2014 | ሐምሌ 15
    • 13 እስከ አሁን ያየናቸው የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የሚሠሩት በመዝናኛ ምርጫ ረገድ ብቻ አይደለም። እንደ አለባበስና አጋጌጥ፣ ጤንነትና አመጋገብ እንዲሁም እነዚህን ከመሳሰሉ ሌሎች የግል ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ያለን አመለካከትም ክርክር ሊያስነሳ ይችላል። እንግዲያው ቅዱስ ጽሑፋዊ መመሪያዎች እስካልተጣሱ ድረስ የይሖዋ ሕዝቦች እንዲህ ባሉ ጉዳዮች ላይ ከመከራከር መራቃቸው ጥበብ ነው፤ ምክንያቱም “የጌታ ባሪያ . . . ሊጣላ አይገባውም፤ ከዚህ ይልቅ ለሰው ሁሉ ገር [ዘዴኛ፣ NW የ2013 እትም የግርጌ ማስታወሻ]፣ . . . ሊሆን ይገባዋል።”—2 ጢሞ. 2:24

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ