የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ጥር
    • 3. በ2 ጢሞቴዎስ 3:2-5 ላይ የተዘረዘሩትን ባሕርያት የሚያንጸባርቁት ሁሉም ሰዎች ናቸው?

      3 ሐዋርያው ጳውሎስ “በመጨረሻዎቹ ቀናት ለመቋቋም የሚያስቸግር በዓይነቱ ልዩ የሆነ ዘመን እንደሚመጣ” ጽፏል። ከዚያም በዚህ ዘመን በሚኖሩ ሰዎች ላይ የሚታዩ 19 መጥፎ ባሕርያትን ዘርዝሯል። እዚህ ላይ የተጠቀሱት ባሕርያት በሮም 1:29-31 ላይ ከተዘረዘሩት ጋር ተመሳሳይ ናቸው፤ እርግጥ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በጻፈው ደብዳቤ ላይ በሌሎች የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ የማይገኙ ተጨማሪ መጥፎ ባሕርያትን ጠቅሷል። ጳውሎስ የዘረዘራቸውን ባሕርያት የሚያንጸባርቁት ሁሉም ሰዎች አይደሉም። የክርስቲያኖች ባሕርይ ከዚህ በጣም የተለየ ነው።—ሚልክያስ 3:18⁠ን አንብብ።

  • አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ጥር
    • 4. በኩራት የተወጠሩ ሰዎችን እንዴት ትገልጻቸዋለህ?

      4 ጳውሎስ በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ ሰዎች ራሳቸውንና ገንዘብን የሚወዱ እንደሚሆኑ ከገለጸ በኋላ ብዙዎች ጉረኞች፣ ትዕቢተኞች እና በኩራት የተወጠሩ እንደሚሆኑ ተናግሯል፤ አንድ ሰው እነዚህን ባሕርያት የሚያሳየው በችሎታው፣ በመልኩ፣ በሀብቱ አሊያም በማኅበረሰቡ ውስጥ ባለው ቦታ የተነሳ ከሌሎች እንደሚበልጥ አድርጎ የሚያስብ ከሆነ ነው። እንዲህ ዓይነት ሰዎች፣ ሁልጊዜ ሌሎች እንዲያደንቋቸውና ከፍ ያለ ቦታ እንዲሰጧቸው ይፈልጋሉ። አንድ ምሁር፣ እብሪተኛ ስለሆነ ሰው ሲናገሩ “በልቡ ውስጥ ትንሽ መሠዊያ ሠርቶ ለራሱ ተንበርክኮ ይሰግዳል” ብለዋል። ከልክ ያለፈ ኩራት በጣም የሚጠላ ባሕርይ በመሆኑ፣ ኩሩ የሆኑ ሰዎችም እንኳ እንዲህ ያለ ባሕርይ ያላቸውን ሰዎች እንደማይወዱ አንዳንዶች ሲናገሩ ይሰማል።

  • አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ጥር
    • 8. (ሀ) በዛሬው ጊዜ አንዳንዶች ለወላጆች አለመታዘዝን እንዴት ይመለከቱታል? (ለ) ቅዱሳን መጻሕፍት ለልጆች ምን ምክር ይሰጣሉ?

      8 ጳውሎስ በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ስለሚኖራቸው ግንኙነት ተናግሯል። በመጨረሻዎቹ ቀናት ልጆች ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ እንደሚሆኑ ጽፏል። በምንኖርበት ዘመን እንዲህ ያለው ምግባር በመጻሕፍት፣ በፊልሞችና በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ላይ ምንም ችግር እንደሌለው እንዲያውም ተቀባይነት እንዳለው ተደርጎ የሚቀርብበት ጊዜ አለ፤ ይሁንና ለወላጆች አለመታዘዝ የማኅበረሰቡ መሠረት የሆነውን የቤተሰብ ሕይወት ያናጋል። ለወላጆች አለመታዘዝ በቤተሰብ ሕይወት ውስጥ ችግር እንደሚፈጥር ቀደም ባሉት ዘመናትም ይታወቅ ነበር። በጥንቷ ግሪክ ወላጆቹን የሚመታ ሰው በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉትን መብቶች በሙሉ ያጣ ነበር፤ በሮም ሕግ መሠረት ደግሞ አባትን መምታት ከግድያ የማይተናነስ ወንጀል ነበር። የዕብራይስጥም ሆነ የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲያከብሩ ይመክራሉ።—ዘፀ. 20:12፤ ኤፌ. 6:1-3

  • አምላክን በሚያገለግለውና በማያገለግለው መካከል ያለውን ልዩነት አስተውሉ
    መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2018 | ጥር
    • 10, 11. (ሀ) በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ ሰዎች እርስ በርስ ፍቅር እንደማይኖራቸው የሚያሳዩት የትኞቹ ባሕርያት ናቸው? (ለ) እውነተኛ ክርስቲያኖች እነማንን ጭምር ይወዳሉ?

      10 ጳውሎስ የዘረዘራቸው ሌሎች መጥፎ ባሕርያትም በመጨረሻው ዘመን የሚኖሩ ሰዎች አንዳቸው ለሌላው ፍቅር እንደማይኖራቸው ያሳያሉ። ሐዋርያው፣ ልጆች “ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ” እንደሚሆኑ ከተናገረ በኋላ የማያመሰግኑ ግለሰቦች እንደሚኖሩ መጥቀሱ ተገቢ ነው፤ ምክንያቱም ሰዎች እንዲህ ያለ ባሕርይ የሚያንጸባርቁት ሌሎች ላሳዩአቸው ደግነት አድናቆት ስለሚጎድላቸው ነው። ጳውሎስ አክሎም አንዳንዶች ታማኝ እንደማይሆኑ ተናግሯል። በተጨማሪም ለመስማማት ፈቃደኞች ያልሆኑ ሰዎች ይኖራሉ፤ በሌላ አባባል ከሌሎች ጋር ለመታረቅ እንቢተኞች ይሆናሉ። ከዚህም ሌላ ተሳዳቢዎች እና ከዳተኞች ይሆናሉ፤ ይህም ሰዎችን ሌላው ቀርቶ አምላክን እንኳ እንደሚተቹና የሚያዋርድ ቃል እንደሚናገሩ የሚያሳይ ነው። ጳውሎስ ስም አጥፊ የሆኑ ሰዎች እንደሚኖሩም ተናግሯል፤ እንዲህ ያሉት ግለሰቦች የሌሎችን መልካም ስም የሚያጎድፍ ወሬ ያናፍሳሉ።a

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ