የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • መንጋውን በእረኝነት የሚጠብቁ የበላይ ተመልካቾች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
    • 11 የበላይ ተመልካች ሆነው ለመሾም የሚበቁ ወንዶች ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙነትም ሆነ በልማዳቸው ልከኛ ናቸው። ጽንፈኞች አይደሉም። ከዚህ ይልቅ በአኗኗራቸው ሚዛናዊና ራሳቸውን የሚገዙ ናቸው። በመብል፣ በመጠጥ፣ በመዝናኛ፣ በትርፍ ጊዜ በሚሠሩ ነገሮችና እነዚህን በመሳሰሉ ሁኔታዎች ልከኛ መሆናቸውን ያሳያሉ። ሰካራም ተብለው እንዳይከሰሱ በአልኮል መጠጥ ረገድ ልከኛ ይሆናሉ። የሚያሰክር መጠጥ ወስዶ ስሜቱ የደነዘዘበት ሰው ራሱን መግዛት ያቅተዋል፤ ስለዚህ ለጉባኤው መንፈሳዊ ጉዳዮች ተገቢውን ትኩረት መስጠት አይችልም።

  • መንጋውን በእረኝነት የሚጠብቁ የበላይ ተመልካቾች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
    • 14 ከዚህም ሌላ በጉባኤው ውስጥ የበላይ ተመልካች ሆኖ ለማገልገል የሚሾም ሰው ጤናማ አስተሳሰብ ያለው መሆን ይኖርበታል። ይህም ማለት ለመፍረድ የማይቸኩል አስተዋይ ሰው ይሆናል ማለት ነው። ይሖዋ ያወጣቸው መሠረታዊ ሥርዓቶች ምን እንደሆኑና እንዴት በሥራ ላይ እንደሚውሉ ጥሩ ግንዛቤ አለው። ጤናማ አስተሳሰብ ያለው ሰው ምክርና መመሪያ ሲሰጠው በትሕትና ይቀበላል። እንዲሁም ግብዝ አይደለም።

  • መንጋውን በእረኝነት የሚጠብቁ የበላይ ተመልካቾች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
    • 15 ጳውሎስ አንድ የበላይ ተመልካች ጥሩ የሆነውን ነገር የሚወድ መሆን እንዳለበት ቲቶን አሳስቦታል። ጻድቅ እና ታማኝ መሆን አለበት። ከሌሎች ጋር ባለው ግንኙነት እንዲሁም ትክክልና ጥሩ ለሆነው ነገር በሚወስደው ጽኑ አቋም እነዚህን ባሕርያት ያንጸባርቃል። ምንጊዜም ለይሖዋ ያደረ ከመሆኑም ሌላ ከጽድቅ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጎን በታማኝነት ይቆማል። ሚስጥር ጠባቂም ነው። በተጨማሪም ራሱንም ሆነ ንብረቱን በፈቃደኝነት ለሌሎች ጥቅም በመስጠት ከልቡ እንግዳ ተቀባይ መሆኑን ያሳያል።—ሥራ 20:33-35

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ