የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ሕሊናህ የሚነግርህን ተግባራዊ አድርግ
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | ጥቅምት 15
    • ሕሊናህ የሚነግርህን ተግባራዊ አድርግ

      “ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም።”—ቲቶ 1:15

      1. ጳውሎስ በቀርጤስ ከነበሩት ጉባኤዎች ጋር ምን ግንኙነት ነበረው?

      ሐዋርያው ጳውሎስ ሦስተኛ ሚስዮናዊ ጉዞውን ካጠናቀቀ በኋላ ታሰረ፤ ጥቂት ቆይቶም ለሁለት ዓመታት ያህል በእስር ወደቆየባት ወደ ሮም ተወሰደ። ጳውሎስ ከእስር ሲፈታ ምን አደረገ? ከእስር ከተፈታ ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ከቲቶ ጋር ወደ ቀርጤስ ደሴት ሄደ። ከቲቶ ከተለየ በኋላም እንዲህ ሲል ጽፎለታል:- “አንተን በቀርጤስ የተውሁህ ገና ያልተስተካከለውን ነገር እንድታስተካክልና ባዘዝሁህ መሠረት በየከተማው ሽማግሌዎችን እንድትሾም ነው።” (ቲቶ 1:5) ቲቶ የተጣለበት ኃላፊነት ሕሊናን የሚመለከቱ ጉዳዮችን ማየትን ይጨምር ነበር።

      2. ቲቶ በቀርጤስ ደሴት ባሉ ጉባኤዎች ውስጥ ለምን ዓይነት ችግሮች መፍትሔ መስጠት ነበረበት?

      2 ጳውሎስ የጉባኤ ሽማግሌዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ብቃቶችን በሚመለከት ለቲቶ ከነገረው በኋላ፣ በዚያ “ዐመፀኞች፣ ለፍላፊዎችና አታላዮች የሆኑ ብዙ ሰዎች” እንዳሉ ጠቁሞታል። እነዚህ ሰዎች “ማስተማር የማይገባቸውን ነገር በማስተማር ቤተ ሰብን ሁሉ በመበከል ላይ” ነበሩ። በመሆኑም ቲቶ ‘አጥብቆ ሊገሥጻቸው’ ይገባ ነበር። (ቲቶ 1:10-14፤ 1 ጢሞቴዎስ 4:7) ጳውሎስ ቀለም ነክቶት ያደፈን ጥሩ ጨርቅ የሚያመለክት ቃል በመጠቀም የእነዚህ ሰዎች አእምሮና ሕሊና ‘እንደረከሰ’ ተናግሯል። (ቲቶ 1:15) ከእነዚህ ሰዎች መካከል አንዳንዶቹ የግዝረትን ሥርዓት ይጠብቁ ስለነበር አይሁዳውያን ሳይሆኑ አይቀሩም። እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ያላቸው ሰዎች በዛሬው ጊዜ ባሉ ጉባኤዎች ውስጥ ተጽዕኖ አያሳድሩ ይሆናል። እንደዚያም ሆኖ ጳውሎስ ሕሊናን አስመልክቶ ለቲቶ ከሰጠው ምክር ብዙ የምንማረው ቁም ነገር አለ።

      ሕሊናቸው የረከሰ ሰዎች

      3. ጳውሎስ ለቲቶ ሕሊናን በተመለከተ ምን ጽፎለታል?

      3 ጳውሎስ ስለ ሕሊና እንዲናገር ያነሳሳው ምን እንደሆነ ልብ በል። “ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውና ኅሊናቸው የረከሰ ነው። እግዚአብሔርን እናውቃለን ይላሉ፤ ዳሩ ግን በተግባራቸው ይክዱታል።” በግልጽ መረዳት እንደሚቻለው በጊዜው የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ጤናማ ወይም “ትክክለኛ እምነት እንዲኖራቸው” ማስተካከያዎች ማድረግ ነበረባቸው። (ቲቶ 1:13, 15, 16) እነዚህ ሰዎች ንጹሕ የሆነውንና ያልሆነውን የመለየት ችግር ነበረባቸው፤ ይህ ደግሞ ከሕሊና ጋር የተያያዘ ጉዳይ ነው።

      4, 5. በቀርጤስ ጉባኤ የነበሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች ምን ችግር ነበረባቸው? ይህስ ተጽዕኖ ያሳደረባቸው እንዴት ነው?

      4 ይህ ከመሆኑ ከአሥር ዓመት በፊት የክርስቲያኖች የበላይ አካል፣ እውነተኛ የይሖዋ አምላኪ ለመሆን የግድ መገረዝ እንደማያስፈልግ የወሰነ ሲሆን ይህንንም ጉባኤዎች እንዲያውቁት አድርጓል። (የሐዋርያት ሥራ 15:1, 2, 19-29) ያም ሆኖ በቀርጤስ የሚኖሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች ‘የግዝረትን ሥርዓት ይከተሉ ነበር።’ እነዚህ ሰዎች “ማስተማር የማይገባቸውን ነገር በማስተማር” የበላይ አካሉን በግልጽ ተቃውመዋል። (ቲቶ 1:10 [የታረመው የ1980 ትርጉም], 11) አስተሳሰባቸው ስለተዛባ በሕጉ ውስጥ የሚገኙትን ስለ መብልና ስለ መንጻት ሥርዓት የሚናገሩ ደንቦች ይከተሉና ሌሎችም እንደዚያ እንዲያደርጉ ያበረታቱ ነበር። ከዚህም በላይ በኢየሱስ ዘመን እንደነበሩት ፈሪሳውያን በሕጉ ላይ የራሳቸውን አስተሳሰብ ይጨምሩ ብሎም የአይሁድን ተረትና የሰውን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።—ማርቆስ 7:2, 3, 5, 15፤ 1 ጢሞቴዎስ 4:3

      5 እንዲህ ያለው አስተሳሰብ በማመዛዘን ችሎታቸው እንዲሁም ትክክልና ስህተት የሆነውን በመለየት ችሎታቸው ማለትም በሕሊናቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል። ጳውሎስ “ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም” ሲል ጽፏል። የእነዚህ ሰዎች ሕሊና በመዛባቱ ምክንያት ለድርጊቶቻቸውም ሆነ ለውሳኔዎቻቸው አስተማማኝ መመሪያ ሊሆናቸው አልቻለም። ከዚህም በላይ እያንዳንዱ ክርስቲያን የተለያየ ውሳኔ ሊያደርግ በሚችልባቸው የግል ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የእምነት አጋሮቻቸውን ይነቅፉ ነበር። በዚህ መንገድ የቀርጤስ ክርስቲያኖች ርኩስ ያልሆነውን ነገር ርኩስ አድርገው ይመለከቱት ነበር። (ሮሜ 14:17፤ ቈላስይስ 2:16) እነዚህ ሰዎች አምላክን እናውቀዋለን ቢሉም በተግባራቸው ግን ክደውታል።—ቲቶ 1:16

      “ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው”

      6. ጳውሎስ እንዴት ስላሉ ሁለት ዓይነት ሰዎች ተናግሯል?

      6 ጳውሎስ ለቲቶ ከጻፈለት መልእክት ምን ትምህርት እናገኛለን? እስቲ በሚከተለው ሐሳብ ውስጥ የቀረበውን ንጽጽር ልብ በል:- “ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሮአቸውና ኅሊናቸው የረከሰ ነው።” (ቲቶ 1:15) ጳውሎስ በሥነ ምግባር ንጹሕ ለሆነ ክርስቲያን ሁሉ ነገር ንጹሕና የተፈቀደ ነው ማለቱ እንዳልነበር ግልጽ ነው። ምክንያቱም ጳውሎስ በሌላ ደብዳቤው ላይ ዝሙት፣ ጣዖት አምልኮ፣ መናፍስታዊ ድርጊትና የመሳሰሉትን የሚፈጽሙ ሰዎች ‘የአምላክን መንግሥት እንደማይወርሱ’ ተናግሯል። (ገላትያ 5:19-21) ስለሆነም ጳውሎስ ስለ ሁለት ዓይነት ሰዎች ይኸውም በሥነ ምግባርም ሆነ በመንፈሳዊ ንጹሕ ስለሆኑና ስላልሆኑ ሰዎች እየተናገረ ነበር ብለን መደምደም እንችላለን።

  • ሕሊናህ የሚነግርህን ተግባራዊ አድርግ
    መጠበቂያ ግንብ—2007 | ጥቅምት 15
    • የተለያየ ሕሊና፣ የተለያየ ውሳኔ

      9. ‘ሁሉም ነገር ንጹሕ ከሆነ’ ሕሊና የሚኖረው ሚና ምንድን ነው?

      9 ታዲያ ጳውሎስ “ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው” ሲል ምን ማለቱ ነው? ጳውሎስ እየተናገረ ያለው አስተሳሰባቸውን እንዲሁም ትክክል የሆነውንና ያልሆነውን የመለየት ችሎታቸውን በመንፈስ አነሳሽነት በተጻፈው ቃል ውስጥ ከምናገኛቸው የአምላክ የአቋም ደረጃዎች ጋር ስላስማሙ ክርስቲያኖች ነው። እነዚህ ክርስቲያኖች በቀጥታ ያልተከለከሉ በርካታ ጉዳዮችን በተመለከተ አንዳቸው ከሌላው የተለየ አመለካከት ሊኖራቸው እንደሚችል ይገነዘባሉ። በመሆኑም ሌሎችን ከመንቀፍ ይልቅ አምላክ ያላወገዛቸውን ነገሮች “ንጹሕ” እንደሆኑ አድርገው ይመለከቷቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ ቀጥተኛ መመሪያ በማይሰጥባቸው የኑሮ ዘርፎች ላይ ሌሎች እነሱ ያላቸው ዓይነት አመለካከት እንዲኖራቸው አይጠብቁም። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ እንዴት ሊከሰት እንደሚችል የሚያሳይ ምሳሌ እስቲ እንመልከት።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ