-
የምታሳዩት መንፈስ ምን ዓይነት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥቅምት 15
-
-
“የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እናንተ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን።”—ፊል. 25
-
-
የምታሳዩት መንፈስ ምን ዓይነት ነው?መጠበቂያ ግንብ—2012 | ጥቅምት 15
-
-
1. ጳውሎስ ለእምነት ባልንጀሮቹ በጻፈው ደብዳቤ ላይ ለእነሱ ምን ምኞት እንዳለው ገልጿል?
ሐዋርያው ጳውሎስ ለእምነት ባልንጀሮቹ በጻፋቸው ደብዳቤዎች ላይ ጉባኤዎቹ የሚያሳዩት መንፈስ በአምላክና በክርስቶስ ፊት ተቀባይነት ያገኝ ዘንድ ምኞቱን ደጋግሞ ገልጿል። ለምሳሌ ያህል፣ ለገላትያ ክርስቲያኖች ሲጽፍ “ወንድሞች፣ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን። አሜን” ብሏል። (ገላ. 6:18) ጳውሎስ “ከምታሳዩት መንፈስ ጋር” ሲል ምን ማለቱ ነበር?
2, 3. (ሀ) ጳውሎስ “መንፈስ” የሚለውን ቃል አንዳንድ ጊዜ የተጠቀመበት ምንን ለማመልከት ነው? (ለ) እኛ የምናሳየውን መንፈስ በተመለከተ ራሳችንን ምን ብለን መጠየቅ እንችላለን?
2 ጳውሎስ በዚህ አገባቡ “መንፈስ” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት፣ በሆነ መንገድ እንድንናገር ወይም የሆነ ነገር እንድናደርግ የሚገፋፋንን ኃይል ለማመልከት ነው። ለምሳሌ አንድ ሰው ደግ፣ አሳቢ፣ ገር፣ ለጋስ ወይም ይቅር ባይ ሊሆን ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ “ጭምትና ገር መንፈስ” እንዲሁም ‘የረጋ መንፈስ’ ማንጸባረቅ ጥሩ እንደሆነ ይናገራል። (1 ጴጥ. 3:4፤ ምሳሌ 17:27) በሌላ በኩል ደግሞ አንድ ሰው አሽሙረኛ፣ ቁሳዊ ነገሮችን የሚወድ፣ በቀላሉ ስሜቱ የሚጎዳ ወይም በራስ የመመራት ዝንባሌ የተጠናወተው ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም ብልሹ የሆነ መንፈስ እንዲሁም የእምቢተኝነትና የዓመፀኝነት መንፈስ የሚያሳዩ ሰዎች አሉ።
3 በመሆኑም ጳውሎስ ‘ጌታ ከምታሳዩት መንፈስ ጋር ይሁን’ የሚሉትን ዓይነት አገላለጾች ሲጠቀም ወንድሞቹ ከአምላክ ፈቃድ ጋር የሚስማማና እንደ ክርስቶስ ያለ ስብዕና እንዲያሳዩ ማበረታታቱ ነበር። (2 ጢሞ. 4:22፤ ቆላስይስ 3:9-12ን አንብብ።) እኛም ራሳችንን እንዲህ እያልን መጠየቃችን የተገባ ነው፦ ‘የማሳየው መንፈስ ምን ዓይነት ነው? ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ አምላክን የሚያስደስት መንፈስ ማሳየት የምችለው እንዴት ነው? በጉባኤው ውስጥ ለሰፈነው ጥሩ መንፈስ ይበልጥ አስተዋጽኦ ማበርከት የምችለው እንዴት ነው?’ ለምሳሌ ያህል፣ በሱፍ አበቦች በተሸፈነ መስክ ላይ እያንዳንዱ አበባ ያለው ውበት መስኩ በአጠቃላይ አምሮ እንዲታይ የራሱን አስተዋጽኦ ያበረክታል። እኛስ እንደነዚህ “አበቦች” ለአጠቃላዩ የጉባኤው ውበት የበኩላችንን አስተዋጽኦ እናበረክታለን? በእርግጥም አስተዋጽኦ ለማበርከት ጥረት ማድረግ አለብን። አምላክን የሚያስደስት መንፈስ ለማሳየት ምን ማድረግ እንደምንችል እስቲ እንመልከት።
-