የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢየሱስ በአምላክ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተውን ልዩ ሚና ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ታኅሣሥ 15
    • “ሊቀ ካህናት”

      15. ኢየሱስ ሊቀ ካህናት በመሆን የሚጫወተው ሚና ቀደም ሲል ሊቀ ካህናት በመሆን ካገለገሉት ወንዶች ሁሉ የተለየ የሆነው በምን መንገድ ነው?

      15 በጥንት ጊዜያት በርካታ ወንዶች ሊቀ ካህናት ሆነው ያገለገሉ ቢሆንም ኢየሱስ ሊቀ ካህናት በመሆን የሚጫወተው ሚና ልዩ ነው። እንዴት? ጳውሎስ እንዲህ ሲል መልሱን ሰጥቶናል፦ “እርሱም እንደ ሌሎቹ ሊቃነ ካህናት፣ መጀመሪያ ስለራሱ ኀጢአት ከዚያም ስለ ሕዝቡ ኀጢአት በየቀኑ መሥዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ራሱን በሰጠ ጊዜ፣ ስለ ኀጢአታቸው ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መሥዋዕት አቅርቦአልና። ሕጉ ደካማ የሆኑትን ሰዎች ሊቃነ ካህናት አድርጎ ይሾማልና፤ ከሕግ በኋላ የመጣው መሐላ ግን ለዘላለም ፍጹም የሆነውን ልጅ ሾሞአል።”—ዕብ. 7:27, 28a

      16. የኢየሱስ መሥዋዕት ልዩ የሆነው ለምንድን ነው?

      16 ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነበር፤ ይህም ሲባል አዳም ኃጢአት ከመሥራቱ በፊት የነበረው ዓይነት ፍጹም ሕይወት ነበረው ማለት ነው። (1 ቆሮ. 15:45) በመሆኑም ፍጹምና የተሟላ መሥዋዕት ማለትም በድጋሚ መቅረብ የማያስፈልገው መሥዋዕት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት የነበረው ሰው ኢየሱስ ብቻ ነው። የሙሴ ሕግ በየቀኑ መሥዋዕቶች እንዲቀርቡ ያዝዝ ነበር። ሆኖም እነዚህ ሁሉ መሥዋዕቶች እንዲሁም የክህነት አገልግሎቱ ኢየሱስ ለሚያከናውነው ነገር ጥላ ነበሩ። (ዕብ. 8:5፤ 10:1) ኢየሱስ ከሌሎቹ ሊቀ ካህናት የበለጠ ነገር በማከናወኑና ሊቀ ካህናት በመሆን የሚያቀርበው አገልግሎት ዘላቂ በመሆኑ በዚህ ረገድ የሚጫወተው ሚና በእርግጥም ልዩ ነው።

  • ኢየሱስ በአምላክ ዓላማ ውስጥ የሚጫወተውን ልዩ ሚና ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ
    መጠበቂያ ግንብ—2008 | ታኅሣሥ 15
    • a አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር እንደተናገሩት “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ” ተብሎ የተተረጎመው ቃል በጣም አስፈላጊ የሆነ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ይገልጻል፤ ይህ ቃል “የክርስቶስ ሞት የማይደገም፣ ልዩ ወይም በዓይነቱ ብቸኛ መሆኑን ያመለክታል።”

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ