የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • “የተመረጡ ዕቃዎች” የይሖዋን ቤት እየሞሉት ነው
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥር 15
    • 9. ኢየሱስ ሰው ሆኖ ወደ ሰማይ ሊገባ ያልቻለው ለምንድን ነበር? ይህስ ሁኔታ መፍትሄ ያገኘው እንዴት ነው?

      9 ኢየሱስ በመንፈስ የተቀባ የአምላክ ልጅ ቢሆንም እንኳ ሰብዓዊ አካል ይዞ ሰማያዊ ሕይወት ማግኘት አይችልም ነበር። ለምን? ምክንያቱም ሥጋና ደም የአምላክን ሰማያዊ መንግሥት መውረስ አይችልም። (1 ቆሮንቶስ 15:​44, 50) ኢየሱስ ወደ ሰማይ እንዳይገባ ያገደው ሰብዓዊ ሥጋው በጥንቱ የአምላክ ቤተ መቅደስ ቅድስቱን ከቅድስተ ቅዱሳኑ በሚለየው መጋረጃ መመሰሉ የተገባ ነበር። (ዕብራውያን 10:​20) ሆኖም ኢየሱስ በሞተ በሦስተኛው ቀን አምላክ መንፈስ አድርጎ አስነሳው። (1 ጴጥሮስ 3:​18) አሁን ወደ አምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን ማለትም በቀጥታ ወደ ሰማይ መግባት ይችላል። የተፈጸመውም ነገር ይኸው ነበር። ጳውሎስ እንደሚከተለው ሲል ጽፏል:- “ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች፣ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት [ቅድስተ ቅዱሳንን ለማመልከት ሳይሆን አይቀርም] አልገባምና፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ይታይ ዘንድ ወደ እርስዋ ወደ ሰማይ ገባ።”​—⁠ዕብራውያን 9:​24

      10. ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲመለስ ምን አደረገ?

      10 ኢየሱስ የደመ ሕይወቱን ቤዛዊ ዋጋ ለይሖዋ በማቅረብ መሥዋዕት በመሆን ያፈሰሰውን ደም በሰማይ ረጭቷል። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ከዚህም የበለጠ ነገር አድርጓል። ከመሞቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ለተከታዮቹ “ስፍራ አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ፣ እኔ ባለሁበት እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኋለሁ” ብሏቸው ነበር። (ዮሐንስ 14:​2, 3) ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ወይም ወደ ሰማይ የመግባት መብት በማግኘት ሌሎችም ወደዚያ መግባት የሚችሉበት በር ከፍቷል። (ዕብራውያን 6:​19, 20) ቁጥራቸው 144, 000 የሆኑት እነዚህ ግለሰቦች በአምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ዝግጅት ውስጥ የበታች ካህናት ሆነው ያገለግላሉ። (ራእይ 7:​4፤ 14:​1፤ 20:​6) የእስራኤል ሊቀ ካህን በቅድሚያ የካህናቱን ኃጢአት ለማስተሰረይ የወይፈኑን ደም ይዞ ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ ይገባ እንደነበረ ሁሉ የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ዋጋ በቅድሚያ ጥቅም ላይ የዋለው ለእነዚህ 144, 000 የበታች ካህናት ነበር።b

  • “የተመረጡ ዕቃዎች” የይሖዋን ቤት እየሞሉት ነው
    መጠበቂያ ግንብ—2000 | ጥር 15
    • b ኢየሱስ እንደ እስራኤል ሊቀ ካህን ማስተሰረያ የሚያስፈልገው የራሱ ኃጢአት የለውም። ሆኖም አብረውት ካህናት የሚሆኑት ሰዎች ኃጢአተኛ ከሆነው የሰው ዘር የተዋጁ ስለሆኑ ኃጢአት አለባቸው።​—⁠ራእይ 5:​9, 10

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ