የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • ምዕራፍ 10. አንድ ሰው በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ ተገኝቶ፤ አንድ ወንድም እየተነበበ ያለውን ጥቅስ አውጥቶ እያሳየው ነው

      ምዕራፍ 10

      በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘትህ የሚጠቅምህ እንዴት ነው?

      በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ እንድትገኝ ተጋብዘህ ታውቃለህ? ከዚህ በፊት ተገኝተህ የማታውቅ ከሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ በስብሰባቸው ላይ መገኘት ያስፈራህ ይሆናል። ‘በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ምን ይከናወናል? እነዚህን ስብሰባዎች ማድረግ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? እኔስ መገኘት ያለብኝ ለምንድን ነው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ፣ ከሌሎች ጋር አብረህ መሰብሰብህ ወደ አምላክ ለመቅረብ የሚያስችልህና በግል ሕይወትህ የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን።

      1. አብረን የምንሰበሰብበት ዋነኛው ምክንያት ምንድን ነው?

      አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ ከሌሎች ጋር መሰብሰብ አስፈላጊ የሆነበትን ዋነኛ ምክንያት ሲገልጽ “በታላቅ ጉባኤ መካከል ይሖዋን አወድሳለሁ” ብሏል። (መዝሙር 26:12) በዛሬው ጊዜም የይሖዋ ምሥክሮች አብረው መሰብሰብ በጣም ያስደስታቸዋል። በዓለም ዙሪያ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች አምላክን ለማወደስ፣ ለመዘመርና ለመጸለይ በየሳምንቱ አብረው ይሰበሰባሉ። በተጨማሪም በዓመት ውስጥ ለተወሰኑ ጊዜያት ትላልቅ ስብሰባዎችን በማድረግ አምልኮ ያቀርባሉ።

      2. በስብሰባዎቻችን ላይ ምን ትማራለህ?

      በስብሰባዎቻችን ላይ የሚሰጠው ትምህርት በሙሉ በአምላክ ቃል ላይ ያተኮረ ነው፤ የአምላክን ቃል ‘በግልጽ የሚያብራራና ትርጉሙ ምን እንደሆነ’ የሚገልጽ ትምህርት ይቀርባል። (ነህምያ 8:8⁠ን አንብብ።) በስብሰባዎቻችን ላይ ስትገኝ ስለ ይሖዋና ድንቅ ስለሆኑት ባሕርያቱ የመማር አጋጣሚ ታገኛለህ። ይሖዋ ለአንተ ስላለው ፍቅር ይበልጥ ባወቅክ መጠን ወደ እሱ እየቀረብክ ትሄዳለህ። በተጨማሪም በስብሰባዎቻችን ላይ፣ አምላክ አስደሳች ሕይወት እንድትመራ የሚረዳህ እንዴት እንደሆነ ትማራለህ።—ኢሳይያስ 48:17, 18

      3. በስብሰባዎቻችን ላይ ከሌሎች ጋር መገናኘትህ ምን ጥቅም ያስገኝልሃል?

      ይሖዋ ‘እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድትችሉ አንዳችሁ ለሌላው ትኩረት ስጡ፤ . . . መሰብሰባችሁን ቸል አትበሉ’ የሚል ምክር ሰጥቶናል። (ዕብራውያን 10:24, 25) በስብሰባዎቻችን ላይ እርስ በርስ ከልብ የሚተሳሰቡና ልክ እንደ አንተ ስለ አምላክ ይበልጥ ማወቅ የሚፈልጉ ሰዎችን ታገኛለህ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያገኟቸውን የሚያበረታቱ ሐሳቦች ሲናገሩ ትሰማለህ። (ሮም 1:11, 12⁠ን አንብብ።) በተጨማሪም በሕይወት ውስጥ ያጋጠሟቸውን ችግሮች በተሳካ ሁኔታ እየተወጡ ካሉ ያላገቡም ሆኑ ትዳር የመሠረቱ ሰዎች ጋር የመጨዋወት አጋጣሚ ታገኛለህ። ይሖዋ አዘውትረን እንድንሰበሰብ ከሚፈልግባቸው ምክንያቶች መካከል እነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው።

      ጠለቅ ያለ ጥናት

      በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች ላይ ምን እንደሚከናወንና በእነዚህ ስብሰባዎች ላይ ለመገኘት የምታደርገው ጥረት አያስቆጭም የምንለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።

      4. የይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች

      በመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ለይሖዋ አምልኮ ለማቅረብ አዘውትረው ይሰበሰቡ ነበር። (ሮም 16:3-5) ቆላስይስ 3:16⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች ለይሖዋ አምልኮ የሚያቀርቡት እንዴት ነበር?

      በዛሬው ጊዜም የይሖዋ ምሥክሮች በአምልኮ ቦታዎቻቸው አዘውትረው ይሰበሰባሉ። ስብሰባዎቻቸው ምን እንደሚመስሉ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ። ከዚያም ቪዲዮውንና የጉባኤ ስብሰባ ሲደረግ የሚያሳየውን ሥዕል ተጠቅማችሁ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      ቪዲዮ፦ በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? (2:12)

      • በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ በቆላስይስ 3:16 ላይ የተጠቀሱት የትኞቹ ነገሮች እንደሚከናወኑ አስተውለሃል?

      • በቪዲዮው ወይም በሥዕሉ ላይ ሌላ ትኩረትህን የሳበው ነገር አለ?

      ሁለተኛ ቆሮንቶስ 9:7⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባዎች ላይ ገንዘብ የማይጠየቀው ለምንድን ነው?

      በዚህ ሳምንት ስብሰባ ላይ ምን ትምህርቶች እንደሚቀርቡ ከአስተማሪህ ጋር ተወያዩ።

      • በስብሰባው ላይ ከሚቀርቡት ትምህርቶች መካከል የአንተን ትኩረት የሳበው ወይም ሊጠቅምህ እንደሚችል የተሰማህ የትኛው ነው?

      ይህን ታውቅ ነበር?

      jw.org ላይ በዓለም ዙሪያ ስብሰባዎቻችን የሚደረጉበትን አድራሻና ሰዓት ማግኘት ትችላለህ።

      በስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ከስብሰባ በፊት፣ በስብሰባ ወቅትና ከስብሰባ በኋላ የሚከናወኑትን ነገሮች የሚያሳዩ ሥዕሎች። ከሀ እስከ መ ያሉት ሥዕሎች ይህንኑ የሚያሳዩ ናቸው ሀ. አንድ የይሖዋ ምሥክር ከመድረክ ላይ ሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንግግር ሲሰጥ ለ. በአድማጮች መሃል ያለች አንዲት የይሖዋ ምሥክር በጥያቄና መልስ በሚቀርብ ክፍል ላይ ሐሳብ ስትሰጥ ሐ. አንድ የይሖዋ ምሥክር ስብሰባ ካለቀ በኋላ ከአንድ ቤተሰብ ጋር ሲያወራ መ. አንድ የይሖዋ ምሥክር ወደ አዳራሹ እየገባ ላለ በዕድሜ የገፋ ሰው በሩን ከፍቶ ይዞለት
      1. ሀ. በስብሰባዎቻችን ላይ ንግግሮችና ቪዲዮዎች ይቀርባሉ፤ እንዲሁም ለመስበክና ለማስተማር የሚረዱ ሥልጠናዎች ይሰጣሉ። ስብሰባዎቻችን የሚጀመሩትና የሚደመደሙት በመዝሙርና በጸሎት ነው

      2. ለ. በአንዳንድ የስብሰባው ክፍሎች ላይ አድማጮች ሐሳብ እንዲሰጡ ይጋበዛሉ

      3. ሐ. ቤተሰቦችን፣ ያላገቡ ሰዎችን፣ አረጋውያንንና ልጆችን ጨምሮ ማንም ሰው በስብሰባዎቻችን ላይ መገኘት ይችላል

      4. መ. በስብሰባዎቻችን ላይ ገንዘብ አንጠይቅም። የይሖዋ ምሥክሮች የመግቢያ ክፍያ አይጠይቁም ወይም እየዞሩ ከተሰብሳቢዎች ገንዘብ አይቀበሉም

      5. በስብሰባዎች ላይ መገኘት ጥረት ይጠይቃል

      የኢየሱስ ቤተሰቦች በዚህ ረገድ የተዉትን ምሳሌ ተመልከት። በየዓመቱ በሚከበር አንድ በዓል ላይ ለመገኘት ከናዝሬት እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ያለውን 100 ኪሎ ሜትር ገደማ የሚሆን ተራራማ መንገድ መጓዝ ነበረባቸው። ሉቃስ 2:39-42⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • ወደ ኢየሩሳሌም የሚያደርጉት ይህ ጉዞ መሥዋዕትነት መክፈል የሚጠይቅ ይመስልሃል?

      • በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ምን መሥዋዕትነት መክፈል ሊጠይቅብህ ይችላል?

      • በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ጥረት በማድረግህ እንደምትጠቀም ይሰማሃል? እንዲህ ብለህ የመለስከው ለምንድን ነው?

      ዮሴፍ፣ ማርያም፣ ኢየሱስና ከኢየሱስ ታናናሾች አንዱ ለጉዞ ሲዘጋጁ የሚያሳዩ ሥዕሎች፦ 1. ዮሴፍ ዕቃ የያዙ ከረጢቶችን አህያ ላይ ሲጭንና ማርያም ስንቅ የሚሆኑ ነገሮችን ስታዘገጃጅ 2. ከናዝሬት ወደ ኢየሩሳሌም የሚወስደውን መንገድ የሚያሳይ ካርታ

      መጽሐፍ ቅዱስ ለአምልኮ አንድ ላይ መሰብሰብ በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ይናገራል። ዕብራውያን 10:24, 25⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በስብሰባዎች ላይ አዘውትረን መገኘት ያለብን ለምንድን ነው?

      አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “ከሌሎች ጋር መሰብሰብ አያስፈልግህም። በግልህ መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ በቂ ነው።”

      • ይሖዋ በዚህ ረገድ ያለውን አመለካከት ለማወቅ የሚረዳን የትኛው ጥቅስ ወይም የመጽሐፍ ቅዱስ ምሳሌ ነው?

      ማጠቃለያ

      በስብሰባዎች ላይ መገኘትህ ስለ ይሖዋ ይበልጥ ለማወቅ፣ ከእሱ ጋር ያለህን ወዳጅነት ለማጠናከርና ከሌሎች ጋር አብረህ አምልኮ ለማቅረብ ይረዳሃል።

      ክለሳ

      • ይሖዋ ከሌሎች ጋር እንድንሰበሰብ የሚያበረታታን ለምንድን ነው?

      • በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ ምን ትማራለህ?

      • በስብሰባዎች ላይ መገኘትህ ሌላስ ምን ጥቅም የሚያስገኝልህ ይመስልሃል?

      ግብ

      ምርምር አድርግ

      በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘት ቢያስፈራህስ? በአንድ ወቅት እንዲህ ይሰማው የነበረ ሰው በኋላ ላይ ስብሰባዎቻችንን መውደድ የጀመረው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

      የተደረገልንን አቀባበል መቼም ቢሆን አንረሳውም (4:16)

      አንድ ወጣት በስብሰባዎች ላይ መገኘት የሚወደው ለምን እንደሆነና በቋሚነት መሰብሰቡን ለመቀጠል ምን እንዳደረገ ተመልከት።

      በስብሰባዎች ላይ መገኘት በጣም ያስደስተኝ ነበር! (4:33)

      አንዳንድ ሰዎች በስብሰባዎች ላይ ስለመገኘት የሰጡትን አስተያየት አንብብ።

      “በስብሰባ አዳራሽ በሚደረጉ ስብሰባዎች ላይ መገኘት ያለብኝ ለምንድን ነው?” (ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ)

      ዓመፀኛና የወሮበሎች ቡድን አባል የነበረ አንድ ሰው በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ መገኘቱ ለውጥ እንዲያደርግ የረዳው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

      “መሣሪያዬ ምንጊዜም ከእኔ አይለይም ነበር” (መጠበቂያ ግንብ ሐምሌ 1, 2014)

  • የአምላክ መንግሥት መግዛት ጀምሯል!
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
    • 5. ከ1914 ወዲህ የዓለም ሁኔታ ተቀይሯል

      ቪዲዮውን ተመልከቱ።

      ቪዲዮ፦ ከ1914 ወዲህ የዓለም ሁኔታ ተቀይሯል (1:10)

      ኢየሱስ እሱ ንጉሥ ከሆነ በኋላ በዓለም ላይ የሚታዩትን ሁኔታዎች አስቀድሞ ተናግሯል። ሉቃስ 21:9-11⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • እዚህ ጥቅስ ላይ ከተጠቀሱት ነገሮች መካከል አንተ ያየኸው ወይም የሰማኸው የትኞቹን ነው?

      ሐዋርያው ጳውሎስ የሰው ልጆች አገዛዝ ከመደምደሙ በፊት ባሉት ‘የመጨረሻዎቹ ቀናት’ ሰዎች ምን ዓይነት ባሕርይ እንደሚኖራቸው ገልጿል። ሁለተኛ ጢሞቴዎስ 3:1-5⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • በዛሬው ጊዜ ሰዎች የትኞቹን ባሕርያት ሲያንጸባርቁ ተመልክተሃል?

      በመጨረሻዎቹ ቀናት በዓለም ላይ የሚታየውን ሁኔታ የሚያሳዩ ምስሎች፦ 1. አንድ ወታደራዊ መሪ መድረክ ላይ ቆሞ እጁን ወደ ላይ እያነሳ ሲጮኽ 2. ከመሬት መንቀጥቀጥ በኋላ የፈራረሱ ሕንፃዎች 3. ወታደራዊ አውሮፕላኖች 4. የፊት ማስክ ያደረጉ ሰዎች መንገድ ላይ ሲጓዙ 5. ኒው ዮርክ ውስጥ መንታዎቹ ሕንፃዎች በሽብር ጥቃት ምክንያት በእሳት ሲጋዩ 6. ዕፅ የሚወስድ ሰው 7. ሚስቱ ላይ እየጮኸና ለመማታት እየሞከረ ያለ ባል 8. የተለያዩ ዕፆችና የአልኮል መጠጦች 9. ዘመን አመጣሽ ልብሶችን የለበሱና ጌጣጌጥ ያደረጉ ሴቶች ፎቶ ሲነሱ 11. አንድ ረብሸኛ ቦምብ ሲወረውር

      6. የአምላክ መንግሥት እየገዛ መሆኑን ማወቃችን ለተግባር ያነሳሳናል

      ማቴዎስ 24:3, 14⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

      • የአምላክ መንግሥት በመግዛት ላይ መሆኑን የሚያሳየው የትኛው አስፈላጊ ሥራ መከናወኑ ነው?

      • በዚህ ሥራ መሳተፍ የምትችለው እንዴት ነው?

      የአምላክ መንግሥት አሁን በመግዛት ላይ ይገኛል፤ በቅርቡ ደግሞ መላዋን ምድር በቁጥጥሩ ሥር ያደርጋል። ዕብራውያን 10:24, 25⁠ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

      • “ቀኑ እየቀረበ መምጣቱን ስናይ” እያንዳንዳችን ምን ማድረግ አለብን?

      1. አንዲት የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ላይ ተገኝታ 2. ያቺው ሴት ለምታውቃት ሴት ስትሰብክ

      አንድ ነገር ሌሎችን ሊጠቅምና ሕይወታቸውን ሊያድን እንደሚችል ስታውቅ ምን ለማድረግ ትነሳሳለህ?

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ